Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

የጥናት 1

1ጢሞ.1፡1-5


የጥናቱ መግብያ


ይህ ክፍል ስለጸኃፊውና ስለተጻፈለት ሰው ማንነትና ግንኙነት ያቀርበል፡፡ ጢሞቴዎስ በሚያገለግልበት ጊዜ ራሱንና አገልግሎቱን መጠበቅ ያለበት ገደብ (ፍሬምዎረክ) ቀርበዋል፡፡


የጥናቱ ዓላማ፡(ለአስጠኚ ብቻ)፡ ተሳታፊዎች አገልግሎታቸውንና ለእግዚአብሄር መታዘዛቸውን በፍቅር ድንበር ውስጥ እንዲጠብቁ ማሳሰብ፡፡
የጥናቱ ጥያቄዎች
1. 1ጢሞ.1፡1-5 ሁለት ጊዜ በመቀባበል አንብቡ፡፡


2. በክፍሉ ውስጥ የተነገረ ታሪክ/ ክስተት ካለ ለቡድንህ አስረዳ፡፡


3. የጢናቱ ክፍል ስለጸፍውና ስለጢሞቴዎስ ምን ምን መረጃዎች ይሰጠናል?


4. እነዚህ መረጃዎች ስለመልእክቱ ሥልጣንና ክብር ምን መልእክት ያስተላልፋሉ?


5. በጥናቱ ክፍል ውስጥ ኢየሱስ እንዴት ተገልጾአል?


6. በቁ.2 ላይ ‹‹…ጸጋና ምህረት ሰላምም ይሁን›› የሚል ሓረግ ይገኛል፡፡ ስለእነዚህ ነገሮች ልየነትና ግንኙነት ለቡድንህ አስረዳ፡፡

7. በቁ 3-4 መሠረት፣ ምን አይነት ነገሮች በወንደሞች ህብረት መሃከል ክርክርን ይፈጥራሉ? ለምን?

8. በ ቁ 5 መሠረት የትእዛዝ ፍጻሜ ሊሆን የሚችል ፍቅር ምን ኣይነት ባህሪይ ያለው ነው?

9. አንድ ክርስቲያን ጌታን ለማስደሰት ከፈለገ፣ የሚያደርገውን ሁሉ ከፍቅር ኣንጻር መቃኘት አለበት፡፡ ይህንን ሓሳብ ከ ‹‹አድሱ ትእዛዝ›› ጋር በማገናዘብ አስረዳ፡፡

10. ዛሬ ከዚህ ጥናት ምን ጠቃሚ ነገር ተማርክ/ሽ?

11. የራስህን/የራስሽን የፍቅርና የአገልግሎት ሕይወት መጣጣም እንዴት ትመዝናለህ/ሽ? (መልሱን ለራስህ መልስ፣ ከእግዚአብሄርም ጋር ተመካከርበት)፡፡

 

ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?