Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ጥናት 9: 1ጢሞ.3፡15-16


ስለቤተክርስቲያንም ሆነ በእርሷ ውስጥ ስለሚካሄዱት አገልግሎቶች ስናስብ ስለ ማንነቷና በእግዚአብሄር ጋር ስላላት ግንኙነት መረዳት ጤናማ አገልግሎት አንድናገለግል እጅግ በጣም ይረዳናል፡፡ በዘልማድ ስለ ቤቴክርስቲያን በሰው ዓይምሮ ውስጥ የሚሳሉ ስእሎች በመጽሃፍ ቅዱስ ውሰጥ ስለእርሷ ከተጻፈው ጋር አይስማሙም፡፡ ይህ ደግሞ አብዛኞች በቤቴ/ያን ውስጥ ለሚፈጠሩ ችግርችና ልዩነቶች መንስሔ ከሚሆኑ ነገሮች ዋነኛ ነው፡፡

በዛሬው ጥናት፣ ‹ቤቴ ማን ናት፣ ቤቴ/ያንን የሚመሩ ሰዎችስ ምንን ማወቅ ይገባቸዋል?› ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ እናገኛለን፡፡
የጥናቱ ኣላማ፡


ተሳታፊዎች ስለቤቴ ክርስቲያንና በስለ አገልግሎታቸው ተገብውን መረዳት እንዲያገኙና፣ እግዚአብሄር የቤቱ ባለበት እንደ ሆነ እንዲያስተውሉ መርዳት

የጥናቱ መግብያ
1. የጥናት ክፍሉን ቢያንስ ሁለት ጊዜ በጋራ አንቢቡ፡፡


2. የጥናት ክፍሉን ሃሳብ በአጭሩ በራሳህ አገላለጽ ለተሳታፊዎች ተናገር፡፡


3. በቁ 15 መሠረት፣ ጳውሎስ ከቁ 2-13 የተዘረዘሩትን የቤተ/ያን ጠባቂና አገልጋዮችን መሾሚያ መመሪያ ስሰጥ ትልቁ ዓላማው ምንን ነበር?


4. በ ቁ.15 ላይ የተገለጸው ‹‹የእግዚአብሄር ማደሪያ ቤት›› ምንድ ነው? ይህ መረዳት እንዴት አድርጎ አገልግሎትንና የቤቴ/ያን መሪነትን ይቃኛል? (በተጨማሪ 3፡5፣ ሓ.ሥ. 20፡28፤1ቆሮ.3፡16፤2ቆሮ. 6፡16-18፤ ኤፌ.2፡21-22፤ ዕብ.3፡2-6፤ 1 ጴጥ.2፡4-10፤10፡19-25 አንብቡ፡፡) ‹ህያው እግዚአብሄር ነው እንጂ በኤፌሶን እንዳሉት፣ ሕዝቡ እንዴለመዱአቸው ግኡዛን አማልክት ቤተ/አምልኮ አይደለም.


5. በቁ. 15 ‹‹ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት›› የሚለው አገላለጽ ምንን የሚያስረዳ ነው? (በተጨማሪ ኤርም 1፡18፤ማቴ.16፡18-19፣18፡15-18፣ኤፈ.4፡20-30፣2ቆሮ.6፡3-10 አንብቡ፡፡) ይህንን ሓሳብ በትክክል የተረዳ ክርስቲያን ስለቤተ/ያንና በእርሷ ውስጥ ስለሚያደርገው አገልግሎት ምን አይነት ጥንቃቀዎችን ያደርጋል?


6. ‹‹እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው›› የሚለውን ሓሳብ ስታነብ እንዴት ተረዳዋለህ? (በተጨማሪም ኤፌ.1፡7-10፤ኤፈ.3፡2-13፤ አንብቡ)፡፡


7. በቁ. 16 ላይሓዋሪያው ጳውሎስ ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት አድርጎ ገለጸው፣ ከተዘረዘሩት አገላጾች የትኛው ለአንተ የበለጠ ሚስጥር ነው? ለምን?


8. ከዛሬው ጥናት በእግዚአብሄር ቤት ስለመመላለስና ስለአገልግሎቱ ምን ተማርክ?

 

 

 

ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?