Sagalicha Dhiigicha Hafuurichaቃሉ ደሙ መንፈሱ |
|||||||
The Word the Blood the Spirit |
|||||||
|
ጥናት 15: 1ጢሞ.6፡1-5
አንዱ ሌላው ወንድሙን እየጨቆነና እየበዘበዘ ባለበት ወቅት፣ የራስን ነጻነት እየፈለጉ፣ የእግዚአብሄርንም ክብር ማስጠበቅ በቀላሉ የሚደረግ ነገር አይደለም፡፡ በዚህ ዓይነቱ ተግዳሮት ውስጥ ምዛኑን የጠበቀና በእግዚአብሄር ዘንድ ያለው ሕብረት እንዳይጎዳ፣ አንድ የእግዚአብሄር ሰው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጤናማ ትምህርት መመሪያው ማድረግና እግዚአብሄርን መምሰል የሚባለውን ልብስ መጎናጸፍ ያስፈልገዋል፡፡ የጥናቱ ዓላማ የጥናቱ ክፍል 1ጢሞ.6፡1-5 2. የምንባቡን አጠቃላይ ኣላማ በአንድ አጭር ዐረፍተ ነገር ተናገር፡፡ 3. በዚህ ክፍል መሠረት፣ የእግዚአብሄር ስምና ክብር በአማን ወንድሞችና እህቶች የሚሰደበው መቼ ነው (2ሳሙ.12፡13-14፣ኢሳ.52፡4-7፣ ሕዝ.36፡16-23፣ሮሜ 2፡17-27፣1ቆሮ.10፡31-33፣1ጴጥ.3፡15-18) 4. በቁ1 ላይ ‹ክብር ሁሉ እንደተገባቸው ይቁጠሩ› የሚለውን ሃሳብ እንዴት ተረዳላችሁ? የባሪነት ስነስርዓትን ያስቀጥሉ ማለት ነውን? (ዘፍ. 16፡4-9፣ሚል 1፡5-9፤1ቆሮ 7:21-24; ኤፌ.6፡ 6-9፣ገላ.5፡1፤ 5. በቁ2 መሠረት፣ አማኞች ክርስቲያን አስተዳዳሪዎችን ከሌሎች ይልቅ ማክበርና መታዘዝ ያለባቸውም ለምንድን ነው 6. በዚህ የጥናት ክፍል መሠረት፣ አንድ ሰው የሚያስተምረው ትምህርት ተቀባይነት የሚያገኘው በምን መለኪያ ተለክቶ ነው?(ሮሜ16፡17-18፣ገላ.1፡6-11፤1ጢሞ.1፡3-7) 7. በቁ.3-4 መሠረት፣ በእውቀት ማስተማሪን ‹በትዕብት ከመነፋት› ጋር የሚያመሳስለው ምን ዓይነት ሁኔታ ሲፈጠር ነው? (ቆላ.2፡16-19፣2ጴጥ.2፡4-16) 8. ራሳችሁን በጢሞቴዎስ ዘመን ጌቶቻቸውን ሲያገለግሉ ከነበሩት ባሮች ቦታ ቢታስቀምጡ፣ ይህ የጥናት ክፍል፣ እንዴት ሊጎዳችሁና ሊጠቅማችሁ ይችላል?
ተክሉ ተ. ጉታ ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት
E-mail: [email protected]
|
Waaqayyo si jaallata
Ati Eessa? |
|||||