Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

የጥናት 4


የጥናት ክፍል 1ጢሞ.2፡1-4

የጥናቱ መግብያ
ቤቴክርስቲያን በክርስቶስ የተገለጠውን የእግዚአብሄርን ፍቅር ለዓለም ሁሉ (ለሚያምኑና ለማያምኑ) ለማሳየትና ለሰዎች መዳንም ምክንያት እንዲትሆን በምድር ላይ ትኖራለች፡፡ ይህንን የመኖር ዓላማዋን እውን ለማድረግ ከሚያስችሏት ነገሮች አንዱና ትልቁ የጸሎት ሕይወቷ ነው፡፡ ፀሎት ሥርዓትን መፈጸም ሳይሆን ከአምላክ ጋር ሃሳብን መለዋወጥ (መናገር፣ መጠየቅ፣ መለመን፣ ማመስገን፣ ማድነቅ፣ ማድመጥ፣ወዘተ. ያለበት) ነው፡፡ በዚህ የጥናት ክፍል ውስጥ ከሁለት ዓላማ አንጻር ጸሎት እንዲደረግ ይፈልጋል፡-1. ጥሪያችንን የሚያንጸባሪቅ ሕይወት (እግዚአብሄርን በመምሰልና በጭምተኝነት ሁሉ) እንድንኖር ማለትም ስለ ራሳችን 2. የሌሎች ማዳን ምክንያት እንድንሆን፡፡ በዚህ ክፍል ጳውሎስ በክርስቲያኖች ላይ ባደረጉት ክፋት ለታወቁ ለኔሮና ለባለሟሎቹ አንኳ ሳይቀር አንዲጸለይ ይጠይቃል፡፡ የኔሮ አይነት መሪዎች ክፋታቸው ቢጠላም፣ ለራሳችንንና ለሌሎች ደንነት ስባል፣ ለእነርሱ መጸለይ አስፈለገ፡፡

የጥናቱ ዓላማ፡(ለአስጠኚ ብቻ) ተሳታፊዎች የጸሎት ሕይወታቸውንና ይዘታቸውን በእግዚአብሄር ቃል እንዲመረምሩ ለመርዳት፡፡

የጥናቱ ጥያቄዎች

1. የጥናት ክፍሉን ቢያንስ ሁለት ጊዜ በጋራ አንብቡ፡፡

2. የጥናት ክፍሉን ሓሳብ በራስህ ቋንቋ ለቡድንህ ተናገር፡፡

3. ‹‹›ጸጥና ዝግ ብለን አንድንኖር› የሚለውን ሓረግ እንዴት ትረደዋለህ? የጸጥታና ዝግታ አለመኖር እንዴት አድርገው ‹‹(እግዚአብሄርን በመምሰልና በጭምተኝነት››

መኖርን ይከለክላሉ? (ኤር29፡7)

4. ‹‹ልመና፣ጸሎት፣ ምልጃና ምስጋና›› ምን ልየነትና ሕብረት አላቸው? የአንቴ ሕይወት የትኛው ምዛንን ይደፋል? ለምን?

5. ቤቴክርስቲያን ‹‹ስለ ሰዎች ሁሉ›› እንዴት ያገባታል? የእኛስ ቤቴክርስቲያን ስለ ሰዎች ሁሉ ትጸልያለችን? (ቁ.3-4፣2ጴጥ.3፡3-9፤ ከቤቴ/ያን ዕልሁና ዓላማ ጋር በማያያዝ ማየትም ይጠቅማል፡)

6. እግዚአብሄር ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁት የሚፈልገው ‹‹እውነት›› የትኛው ነው? (ኢሳ.53፡10-11፤ ዮሃ.14፡6፣

7. ከመዳንና እውነትን ከማወቅ የትኛው ይቀድማል? ስለዚህ የተቀመጠበት አሰላለፍ በቅደም ተከተል ላይ ወይስ በአብሮነታቸው ላይ የሚያተኩር ይመስልሃል?

8. በቁ.4 ላይ የተገለጠው ‹‹መዳን/ እንዲድኑ የሚለው ቃል›› ምን ማለት ነው? ከምን ይዳናል? አንድ ሰው ይህንን አይነቱን መዳን እንዴት ማግኘት ይችላል?(ተጨማሪ ቁ.3፣ኢሳ.45፡22፣ ሕዝ.18፡21-23፣33፡10-11፣ ዮሃ.3፡14-18፤ 2ቆሮ.5፡17-21፣የሓ.ሥ4፡8-12፤ሮም3፡10-26 አንብቡ)

9. በጥያቄ 8 ውስጥ ባደረጋችሁት ምርመራ፣ ስለራስህ መዳን እርግጠኛ መሆን ትችላለህን? ስለመዳንህ እርግጠኛ የሚያደርግህ ምን ነገር አገኘህ? (በተጨማሪም ዮሃ.10፡25-30፣ 1ዮሃ.5፡10-15፤1ጰጥ.1፡10-11 አንብቡ፡፡)

10. ከዚህ ጥናት ተነስተህ በጸሎት ሕይወትህና በጸሎትህ ይዘት ላይ ምን ለውጥ አንዲመጣ ትፈልጋለህ?

 


ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?