Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ጥናት 11: 1ጢሞ.4፡7-12


መግቢያ
1ጢሞቴዎስ ምእራፍ 4ን በምናጠናበት ጊዜ በአንድ የእግዚአብሄር አገልጋይ በአገልግሎት ሕይወቱ ውስጥ ያለማቋረጥ መደረግ የሚገባቸውን ሶስት ነገሮችን እንደምናጠና በጥናት 8 መግቢያ ላይ አንስተን ነበር፡፡ እነዚያም የእግዚአብሄርን ቃል ማካፈል፣ የእግዚአብሄርን ቃል በተግባር መለማመድና በቃሉ ማደግ ናቸው፡፡

በዚህ ጥናት ሁለተኛውን ነገር እንመረመራለን-- የእግዚአብሄርን ቃል በተግባር መለማመድ ፡፡ በተለይ በዚህ ጥናት ውስጥ ሓዋሪያው ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ሲጽፍ፣ እንዴት አድርጎ የሚገባውን (ከአገልግሎት ሕይወቱ ጋር የሚሄደውን) ለማድረግና የማይገባውን (ከእግዚአብሄር ፈቃድ ጋር የማይስማማውን) ደግሞ አለማድረግን መለማመድ እንዳለበት ይመክረዋል፡፡ ይህም ጢሞቴዎስንም ሁነ ከእርሱ የሚማሩት በክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት የሚያስክድ እየበዛ በሚሄድበት ዘመን እምነታቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ ይረዳቸዋል፡፡

የጥናቱ ዓላማ
ተሳታፊዎች አጥብቀው በክርስቶስ ላይ ያለውን እምነታቸውን እንዲይዙና ሌሎችንም በዚሁ አቅጣጫ እንድረዱ ማበረታታት፡፡
የጥናቱ ክፍል 1ጢሞ.4፡7-12

ማጥኛ ጥያቄዎች

1. የጥናት ክፍሉን ደጋግማችሁ አንቢቡት፡፡

2. ያነበባችሁትን ነገር በጭሩ በራስህ አገላለጽ ለቡድንህ ተናገር፡፡

3. በዚህ ክፍል ውስጥ ጢሞቴዎስ እንዲያደርጋቸው የታዘዙለት የእምነት ጽናት መርጃዎች ምን ምን ናቸው (ቁ.7፣11-12፤

4. በቁ.7u መሰረት፣ ‹‹ለአለም ከሚመችና የአሮግቶችን ሴቶች ጨወታ ከሚመስለው ተረት ራቅ›› የሚለውን ሃሳብ እንዴት ትረደዋለህ? (1ጢሞ.1:4; 6:20; 2ጢሞ.:2:16-25; 4:4) አሁን ባለንበት ጊዜና ሁኔታ ይንን ዓይነት እርምጃ አወሳሰድ እንዴት ተግባራዊ ልናደርግ እንችላለን?

5. በቁ.7ለ መሰረት፣ አንድ ሰው እግዚአብሄርን መምሰልን ራሱን ማስለመድ የሚችለው ምን ማድረግ ሲችል ነው? ይህ አይነቱ ነገር በእኛስ እንዴት መተግበር አለበት? (1ቆሮ.9፡ 24-27)

6. በቁ9 ላይ ‹‹ሁሉም መቀበል ይገባል›› የተባለው ሃሳብ ምንድን ነው? ሓሳቡን መቀበላችንስ በምን ይታወቃል?

7. በቁ 12 መሠረት፣ አንድ የእግዚአብሄር ሰው በሌሎች የሚናቀው መቼ ነው? እንዳይናቅስ በምን መከላከል ይችላል? (ለምሳሌ፡-የመርዶክዮስ ታርክ፤የዮሴፍ ታርክ፣)

8. ከላይ ያየናቸው ነገሮች በዘመናችን ካሉት የመጨረሻ ዘመን ስህተቶች አንዴት ሊጠብቁን እንደምችሉ ተወያዩበት፡፡

 

ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?