Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ጥናት 13: 1ጢሞ.5፡1-16


መግቢያ
ቤቴክርስቲያን ወስጥ ያለው መንፈሳዊ አገልግሎት በህብረተሰብ ውስጥ ያለውን ማህበረሰባዊ ዕሴቶች፣ ከቃሉ ጋር እስካልተቃረነ ድረስ ያከብራል፡፡ በማንኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ከታወቁት ማህበረሰባዊ እሴቶች መካከል መበከባበርና ችግረኞችን መርዳት ይገኙበታል፡፡ አንድ የወንጌል አገልጋይ ሰው ሁሉ ከአገልግሎቱ እንዲጠቀምና የታላቁ እግዚአብሄር መንግስት ተካፋይ እንዲሆን ለማድረግ ከሚያደርጋቸው ነገሮች መካከል ሰዎችን የሚገባቸውን አክብሮት መስጠት ነው፡፡ በእርግጥ ይህ የተፈጥሮ ሕግም ነውና ያስፈልጋል፡፡
በዚህ ክፍል ሓዋሪያው ጳውሎ ወጣቱን ጢሞቴዎስን ሲመክር፣ክስቲያኖችን ሁሉ በቤተሳባዊ ፍቅር መቀበልና ማክበር እንደሚያስፈልጋቸው ይመክረዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ አሠራር፣ በመቻቻል አብሮ መኖርንና የወንጌልን ክብር አጉልቶ ያሳያል፡፡

የጥናቱ ዓላማ
ተሳታፊዎች በቤቴክርስቲያን ውስጥ ካሉት ሰዎች ሁሉ ጋር እንዴት መዛመድና መከባበር እንዳለባቸው መስተማር፡፡

የጥናቱ ክፍል 1ጢሞ.5፡1-16
ማጥኛ ጥያቄዎች
1. የጥናት ክፍሉን ደጋግማችሁ አንቢቡት፡፡

2. የምንባቡን አጠቃላይ ኣላማ በአንድ አጭር ዐረፍተ ነገር ተናገር፡፡

3. በቁ.1 ላይ የተገለጸው መገሰጽ ምን ትርጉም አለው? (ዘለዋ.19፡32 ገላ.2፡11-14)

4. በ ቁ 1-2 ላይ በተቀመጠው መሠረት፣ በክርስቲያኖች መካከል ቤቴ ሳባዊ አስተሳሰብ (የአባት፣ የእናት፣የእህትና የወንድማዊ ግንኝነቶች) መጎልበት ምን ጥቅም ይኖረዋል?

5. ባልተት ማለት ምን ማለት ነው? ባልቴቶች በምን መስፈርት በባልተትነት ይመዘገባሉ? ለምን? (ዘዳግ.10፡17-20፣ ሓ›ሥ 6፡1-6)

6. ቁ 8 ስታነብ እንዴት ትረደዋለህ? ቤቴሰዎችን መርዳትንና በሓይማኖት መጽናትን ምን ያገናኛቸዋል?

7. ቁ 11 ‹‹ባል የሞቴባትን ቆነጃጅት ግን አትቀበል›› የሚለውን ሃሳብ እንዴት ታብራረዋለህከቤቴ ክርስቲያን አገልግሎት ምን ይጠቀማሉ? ምንስ ያበረክታሉ? በምክንያቶቱ ላይ ተመካከሩበት፡፡

8. ይህንን የጥናት ክፍል እንዴት አድርገን በግልና በህብረት ከራሳቻችን ጋር ልናዛምድ እንችላለን?

 

ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?