Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ጥናት 14: 1ጢሞ.5፡17-25


መግቢያ
እንደማንኛውም ድርጅት ቤቴክርስቲያን በአግባቡ ተልእኮዋን እንድትወጣ የመሪዎች ምና ትልክ ነው፡፡ ሽማግሌዎች የቤቴክርስቲያን መሪነትን ከያዙት የአገልግሎት ዘርፎች ትልቁን ምና ይጫወታሉ፡፡ ስለዚህ በቤቴክስቲያን ውስት ባሉት ዘንድ ክብር ይገባቸዋል፣ በተለይ ደግሞ የተሠጣቸውን አመሪነት አገልግሎት ሌሎችን በሚያስተምርና በሚመክር መንገድ ለሚወጡት(1ጢሞ.5፡17)፡፡ ያ ማለት ግን በሽማለዎች ላይ ምንም ተቃዉሞ ማንም አይኖረውም ማለት አይደለም፡፡ ቃሉ በእውነት እግዚአብሄርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ይሰደዳሉ ስለሚል፣ እውነተኝነት የሌሌውን ክስ በሽማግለዎች ላይ ተቀብሎ እንዳያስተናግድ ሓዋሪያው ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ይመክረዋል፡፡ ሆኖም ግን ለሽማግለነት ከመሾሙ በፍት ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ፣ በሽማግለ ስልጣን ተጠቅመው ኃጢአት ማድረግን የሚለማመዱትን ግን ሌሎች ሊማሩበት በሚችሉ መልኩ ያለ ምንም አድልዎ እንድስጻቸው ይናገራል፡፡ በተለይ ደግሞ በሰዎች ሓጢአት እንዳይተባበር ይመክረዋል፡፡

የጥናቱ ዓላማ
ተሳታፊዎች በቤቴክርስቲያን ውስጥ መኖር ስላለበት ክርስቲያናው ጥንቃቀዎች (ሽማግለዎችን ማክበር፣ በሃጢአት የሚቀጥሉትን መገሰጽ፣ራስን በንጽሕና መጠበቅ) እንድማሩ መርዳት፡፡
የጥናቱ ክፍል 1ጢሞ.5፡17-25
ማጥኛ ጥያቄዎች
1. የጥናት ክፍሉን ደጋግማችሁ አንቢቡት፡፡

2. የምንባቡን አጠቃላይ ኣላማ በአንድ አጭር ዐረፍተ ነገር ተናገር፡፡

3. በጠቅላላው የመጽሓፍ ቅዱስ አስተምህሮት፣ ሽማግለዎች ክብር ይገባቸዋል፡፡ በቁ 17-18 መሠረት ደግሞ እጥፍ ክብር የሚገባቸው ሽማግሌዎች ተገልጸዋል፡፡ እጥፍ ክብር ማለት ምድን ነው? ለምን ተገባቸው?

4. በቁ 19-20 መሠረት ሽማግሌዎች የማይከሰሱበት ሁኔታና የሚገሰጹበት ሁኔታ ላይ ተነጋገሩ፡፡ (በተጨማሪም አንብቡ፡፡)

5. በቁ.21 ላይ የተገለጠው አድልዎ ምን አይነት ችግር ሊያመጣ ይችላል የሓዋሪው ምስክሮችን መጥራትስ ለምን አስፈላጊ የሆነ ይመስላችሃል፡፡

6. በሌሎች ኃጢአት መተባበር ማለት ምን ማለት ነው፡፡ በሰዉ ላይ ‹‹ፈጥኖ እጅ መጫንን›› ‹‹በኃጥአታቸው ከመተባበር›› ጋር እንዴት ይገናኛል?

7. በቁ 24-25 ምን መልክትን ያስተላልፋል?

8. ከዛሬው ጥናት በግልህ ምንን ተማርክ?

 

ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?