Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

የጥናት 3


የጥናት ክፍል 1ጢሞ.1፡18-20
የጥናቱ መግብያ

የአንድ ሰው ህልህናና እምነት በሰውየው ኑሮና ስከት ላይ ከፍተኛ ተጽህኖ ይኖራቸዋል፡፡ የአንድ ሰው ሕልና ሲጎዳና ሲቆሽሽ በዚያ ሰው እምነት ላይ ከፍተኛ የሆኔ አሉታዊ ተጽኖ ያመጣል፡፡ ስለዚህ ምእመናን ይህን በማወቅ በክርስቶስ ላይ ባላቸው እምነት መጽናትና ሕልናቸውንም መጠበቅ አለባቸው፡፡ እንደ ክርሰቲያንም ሆነ እነዴ ቤቴክርስቲያን በምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ እግዚአብሄርን ለማስከበርና ለነፍሳት መዳን (ለፍቅር) ከፍተኛ ትኩረት መስጠት ይጠበቅብናል፡፡ አንድ ጸኃፊ፣ ኅልና ብርናንን እንደሚያሰገባ መስኮት ነው ብሏል፡፡ መስኮቱ ንጹኽ ከሆነ፣ የጠራ ብርሃን ይገባል፣ ከቆሸሸ ደግሞ ብርሃኑ ይደበዝዛል፡፡ ሕሊና መልካምናና ክፉውን የሚንለይበት ውስጣዊ ‹‹ማወቂያ መሳሪያ›› ነው፡፡ጳውሎስ 23 ጊዜ መልእክቶቹ ውስጥ በዚህ ቃል ተጠቅሞአል፡፡

የጥናቱ ዓላማ፡(ለአስጠኚ ብቻ) ተሳታፊዎች በጎ ህልህን እንድጠብቁና በክርስቶስ ላይ ያለውን እምነት እንዲያጸኑ ማሳሰብና ማበረታታት ፡፡

የጥናቱ ጥያቄዎች

1. የጥናት ክፍሉን ቢያንስ ሁለት ጊዜ በጋራ አንቢቡ፡፡

2. በጥናት ክፍሉ ውስጥ ያለውን ሃሳብ በራስ አገላለፅ ለቡድንኅ ተናገር፡፡

3. ስለ ጢሞቴዎስ ‹‹የተነገረው ትንቢት›› ምን ሊሆን ይችላል?

4. ‹‹መልካም ጦሪነትን መዋጋት›› ማለት ምን ማለት ነው? እነማን ናቸው መልካም ጦርነትን መዋጋት የሚችሉት?

5. ቁ.18 ላይ ጳውሎስ ‹‹ይህችን እዕዛዝ አደራ እሰጣለሁ›› ቢሎ ሲናገር ስለየትኛው ትእዛዝ ይናገራል?

6. ስለ ጢሞቴዎስ የተነገረው ትንቢት እንዴት መልካም ጦርነትን መዋጋት አንዲችል ሊረዳው ይችላል?

7. ከመልእክቱ መረዳት አንደምንችለው፣ ጢሞቴዎስ ቀድሞውኑ አማኝ ነው፡፡ በ ቁ.19 ላይ ‹‹እምነትና በጎ ሕልና ይኑርህ›› የሚለውን አንዴት ትረደዋለህ? በዚህ ክፈል

መሠረት አንድ ሰው በጎ ሕልና እነዲኖረው ማድረግ የማን ድርሻ ነው?

8. ‹‹አንዳይሳደቡ ይማሩ ዘንድ ለሠይጣን አሳልፈ ሰጠኃቸው›› የሚለውን አንዴት ትረዳዋለህ? የዚህ ዓይነቱ እርምጃ መች ይወሰዳል፣ ዓላማውስ ምንድን ነው?

በተጨማሪም 1ጢሞ.2፡17-19፤2ጢሞ4.14-15፣ማቴ.18፡15-20፣1ቆሮ.5፡1-5፣2ተሰ.3፡14-15፣ ራእ 2፡2-5 (ጢሞቴዎስ የነበረውም

በኤፈሶን ነው)፤

9. በግልህ ከዚህ ጥናት ምንን ተማርክ/ሽ?

10. በዚህ ክፍል በተማረከው ነገር ላይ በመመርኮዝ በሚቀጥሉት ቀናት በእግዚአብሄ ፍት ራስህን/ራስሽን ለማቅተብ ሞክር፡፡

ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?