Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ጥናት 8: 1ጢሞ.3፡8-13


የጥናቱ መግብያ

የእግዚአብሄር በቴክርስተያን በምድር ላይ የሚትኖረው የእግዚአብሄርን ፈቃድና መንግስት ለሰዎች ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ሆኖም ግን፣ መንገዷንም ሆነ ትህምርቷን የሚቃወሙ፣ የሚያጥላሉና፣ መበረዝ የሚፈልጉ አካላት ደግሞ ሁልጊዜ ከጎኗ ነበሩ ዛሬም አሉ፡፡ ቤቴክርስቲያን ያንን ኣይነት ችግር ከምትቋቋምበት መንገዶች አንዱ፣ ‹‹ያለ ነቀፋ›› የሆነ የአኗኗርና የመሪነት ስርኣትን በመገንባት ነው፡፡

ቤቴክርስቲያን አገልጋዮዋና ምእመናን በሙሉ "ያለ ነቀፋ"መሆን ይፈለግባቸዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ደግሞ በቤቴ ክርስቲያን ዙሪያ ስለለው ገር ብቻ ሳይሆን ቤታቸውና ቤተሰቦቻቸው አካባቢ ባሉት ነገሮችም ላይ በመስራት እነርሱ የሚያመልኩትና የሚያገለግሉት አምላክም ሆነ ትምህርቱ እንዳይነቀፍ ያደርጋሉ፡፡ ቤተሰብ የክርስቶስና የቤቴ/ክርስቲያን ምሳሌ ከመሆኑም ባሻገር፣ በቤቴ/ክርስቴያን ግንባታ ውስጥ ወሳኝ መነሻ/መሠረት ነው፡፡


በዚህ ጥናት፣ ለዚህ አላማ እንዲሆን፣ ቤተክርሲቲያን ምን ዓይነት ሰዎችን በድቁና አገልግሎ ላይ መሾም እንዳለባት በሓዋሪያው ጳውሎስ አማካይነት የተሰጠንን መመሪያ እንፈትሻለን፡፡ አማኝ ሁሉ እግዚአብሄርንና ሕዝቡን በተሰጠው ሥጦታ ተጠቅሞ ሲያገለግል እነዚህን ብቃቶች/ኩዋሊቲዎች/ ማሳደግ ስላለበት ራሳንንና ጠቅላላ አማኝን እያስገባን እናጠናለን፡፡


የጥናቱ ዓላማ (ለአስጠኚ ብቻ) ፡
ተሳታፊዎች፣ በተሰጣቸው ማንኛውም ጸጋ በብቃት ማገልገል እንዲችሉ ለማዘጋጀት ፡፡


የጥናቱ ጥያቄዎች
1. የጥናት ክፍሉን ቢያንስ ሁለት ጊዜ በጋራ አንቢቡ፡፡


2. የጥናት ክፍሉን ሃሳብ በአጭሩ በራሳህ አገላለጽ ለተሳታፊዎች ተናገር፡፡


3. በዚህ ክፍል ‹‹ዲያቆን›› ማለት ምን ማለት ነው?


4. ከቁ 8-13 የተዘረዘሩትን የዲያቆናት ብቃት መለኪያዎች እንደ አስፈላጊነታቸው ነጥብ ብንሰጣቸው ፣ የትኛውን አሁን ላለንበት ቤተ/ያንና ህብረተሰብ ቅድሚያ ሠጥተን መገንባት/ማሳደግ ይጠበቅብናል? (የሚሰጣችሁን ሠንጠረዥ በመጠቀም፣ ጥያቄውን ለመመለስ ሞክሩ )


5. አንድ አማኝ እነዚህን የክርስቲያናዊ አገልጋይ መለኪያዎች ወደ ማሟላት ለመምጣት ምን ዓይነት ነገሮችን ማድረግ ይጠበቅበታል? ቤቴ/ያንስ ምን በማድረግ ማገዝ አለባት? (ሚሰጣችሁን ሠንጠረዥ በመጠቀም በውይይት መልሱ)

 


6. አንድ ሰው እግዚአብሄር በሚፈልገው መልኩ አገልግሎቱን ሲወጣ ምን ትርፍ ያገኛል? (ቁ13ን ተመልከቱ)


7. ከዚህ ጥናት ለራስህ ምን ተማትክ?

 

 

 

 

 

 

ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?