Sagalicha Dhiigicha Hafuurichaቃሉ ደሙ መንፈሱ |
|||||||
The Word the Blood the Spirit |
|||||||
|
ጥናት 17: 1ጢሞ.6፡13-21
በመጨረሻም የእግዚአብሄር ሰው ከገንዘብ ፍቅር መሸሽና በአንጻሩ ደግሞ ‹ጽድቅን፣ እግዚአብሔርን መምሰልን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ መጽናትንና የዋህነትን መተከታተል› (ቁ11) እንዳለበትና ከሁሉም አብልጦ በክርስቶስ ያገኘውን የዘላለምን ሕይወት መያዝ እንዳለበት አጥንተናል ፡፡ በዛረው ጥናት ደግሞ ለምንና እነዴት በእግዚአብሄር ፍት መመላለስ እንዳለብን፣ በሓብታች እንደት መመልከትና መጠቀም እንዳለብንና እውነተነውን እውቀት ለይተን መያዝ እንዳለበን እናጠናለን፡፡ የጥናቱ ክፍል 1ጢሞ.6፡13-21 2. የምንባቡን አጠቃላይ ኣላማ በአንድ አጭር ዐረፍተ ነገር ተናገር፡፡ 3. ‹‹ያለ እድፍና ያለነቀፋ ሆነህ ትእዛዙን ጠብቅ›› በሚለው ምክር ውስጥ፣ እድፍና ነቀፋ ምንድናቸው? 4. በ13-16 በተገለጠው መሠረት፣ ስለጌታችን ዳግሞ መገለጥና ስለእርሱ ማንነት መረዳት የዛሬውን ሕይወታችን በአግባቡ ለመኖርና አገልግሎታችንንም በተገቢው ሁኔታ ለማድረግ እንዴት ሊረዳን ይችላል? 5. በመጽሓፍ ቅዱስ መሠረት፣ አንድ የእግዚአብሄር ሰው ሓብታም መሆን የለበትም የሚል የለም፡፡ ነገር ግን በንብረቱን ላይ ሊኖረው ስለሚገባው አመለካከትና በአጠቃቀሙ ላይ ብዙ መመሪያዎችና ምክሮች አሉ፡፡ በዚህ ጥናት ይህንን በተመለከተ የተሰጡትን ምክሮች አንድ በአንድ አውጡና ተወያዩበት፡፡(ቁ 17-19)፡፡ 6. በቁ 20-21 ላይ የገጸው ‹‹እውቀት›› ምን ዓይነት እውቀት ነው፡፡ ዛሬ እኛን ልንሰማቸውና ሊንታለልባቸው በምንችል ተመሳሳይ ‹እውቀቶች› ላይ ተመካከሩ፡፡ 7. ከዛሬው ጥናት ምን ተማራችሁ?
ተክሉ ተ. ጉታ ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት
E-mail: [email protected]
|
Waaqayyo si jaallata
Ati Eessa? |
|||||