Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 
 

የቡድን መጽሓፍ ቅዱስ ጥናት

መግቢያ

 

መጽሃፍ ቅዱስን የምናጠናበት ዋነኛው ምክኒያት በምንኖረን የክርስቲና ሕይወት ውስጥ የአኗኗር መሪና መመሪያን ለማግኘትና፣ በማናቸውም የህይወት ሁኔታ ውስጥ ልንጠየቅ ለምንችለው ጥያቄዎች እንዴ እግዚአብሄር ፈቃድ መልስ መስጠት እንድንችል ይረዳን ዘንድ ነው፡፡

 

በመሆኑም በማናቸውም ጊዜ ለየብቻችንም ሆነ በህብረት መጽሓፍ ቅዱሳነችንን ስናጠና፣ የተለያዩ ጥያቄዎቸን በመጠየቅ፣ የምናጠናው ክፍል ወይም መጽሃፍ ለምንና ለማን፣ በማናቸው ሁኔታ ውስጥ እንደ ተጻፈና ዛሬ ደግሞ ለእኛ ምን ዓይነት ትርጉም እንደሚሠጠን ማጠን አስፈላጊ ነው፡፡ በመጨረሻም ከህይወታችን ጋር በማዛመድ፣ በግልም ሆነ በህብረት ምን ኣይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለብን ለይቶ ማውጣት ጥናቻችንን ውጤታማ ያደርገዋል፡፡

 

በዚህ ዲህረ-ገጽ ላይ እግዚአብሄር እንደ ረዳኝ የተለያዪ የመጽሓፍ ቅዱስ ክፍሎችን የማናቀርብ ሲሆን፣ የጥናቶቹ ክፍሎቹም የሚቀርቡት በማያመልክበት ሕብረት ውስጥ ከምመራው የመጽሓፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን ጋር ለማጥናት በማያደርጋቸው ዝግጅቶች ወቅት ነው፡፡

 

ስለዚህ በየጊዜው አንድትከታተሉ እየተጋበዛችሁ፣ ሌሎችም ሰዎች ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ወብሳይቱን በማቃበል ወገኖችን ድንድታበረታቱ በእግዚአብሄር ፍቅር ትጠየቃላችሁ፡፡

 

ለጊዜው የተዘጋጁና በቅርቡ በዚህ ድህረ-ገጽ ላይ ሊወጡ የሚችሉት ጥናቶች ቀጥለው የተዘረዘሩ ናቸው፡፡

እግዚአብሄር በጸጋው ስለረዳኝና ደግሞም ስለሚረዳኝ እያመሰገንሁ፣ ይህን ሥራ ለእርሱ ክብርና ለሕዝቡ ጥቅም መቀጠል አንዲችል በጸሎታችሁና ሀሳብ በመስት ከእኔ ጋር እንዲትቆሙ በእግዚአብሄር ፍቅር እለምናችሃለሁ፡፡

 

‹‹የሰማይ አምላክ ያከናዊንልናል፣ እኛም ባሮቹ ተነስተን እንሰራለን›› ነሀ.2፡20

 

ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?