Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

የጥናት 5


ጥናት 5: 1ጢሞ.2፡5-7
የጥናቱ መግብያ
በጥናት 4 ከሰዎች ሁሉ ድነት ጋር አያይዘን ስለጸሎት አጥንተናል፡፡ በዚህ ጥናት ደግሞ ፀሎት ወደ ማን መቅረብ እንዳለበት እናያለን፡፡ በምድራችን ላይ ብዙ የሚመለኩና የሚሰገድላቸው ነገሮች (መናፍስት፣ ሰዎች፣ የተለያዩ ፍጥረቶችም) አሉ፡፡ ሆኖም ግን አምልኮና ስግደትን መውሰድ የሚገባው አንዱ እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ ሰዎችን ከእግዚአብሄር ጋር ለማስታረቅ በመካከል ሊቆም የሚችለው (ብቃቱ ያለው) ሰውም አምላክም መሆን የቻለው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡
የጥናቱ ዓላማ (ለአስጠኚ ብቻ) ፡
እግዚአብሄርን ብቻ ማምለክ እንዲችሉና በእነርሱና በእግዚአብሄር ማካከል ለመቆም የቻለው ኢየሱስ ብቻውን በቂ እንደ ሆነ ለማስገንዘብ፡፡ ከዚህም የተነሳ በእነርሱና በእውነተኛ አምላክ መካከል ሌላ ማንንም መግባት እንዳይችል እንዲያውቁ መርዳት፡፡
የጥናቱ ጥያቄዎች
1. የጥናት ክፍሉን ቢያንስ ሁለት ጊዜ በጋራ አንቢቡ፡፡
2. የጥናት ክፍሉን ሃሳብ በአጭሩ በራሳችሁ አገላለጽ ለተሳታፊዎች ተናገር፡፡
3. ‹‹አንድ እግዚአብሄር አለ›› የሚለውን ሐረግ ስታነብ ወይም ስትሰማ ምን ትርጉም ይሰጥሃል ? (በተጨማሪም ዘዳ.5፡5-10፣6፡4፣ ማቴ. 12፡29-30፣1ቆሮ.8፡5-6፣ሮሜ.3፡30 አንቢቡ፡፡ ሌሎች ሁሉ አምላክ ሳይሆኑ የተሰየሙ/የተመለኩ ናቸው)
4. ‹‹መካከለኛ ›› ምንድን ነው? አንድ ሰው በሁለት ሰዎች መካከል መካከለኛ ለመኖን ምን ዓይነት መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርበታል? ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚያን መስፈርቶች አሟልቶ እንደሆነም ተወያዩበት፡፡ (ዘዳግ. 5፡5፣ኢዮ.9፡32 -34፣ኢሳ. 43፡25-28፤ዕብ.7፡18-28፤ 9፡11-17)
5. ክርስቶስ ራሱን ‹‹ለሁሉ ቤዛ ሠጠ›› የሚለውን ከቁ3-4 በማያያዝ አስረዳ (በተጨማሪም ኢሳ.53፤6፣ማቴ 20፡28፣ ዮሃ 6፡51፣ ፡፡
6. በቁ.7 ‹‹በእምነትና በእውነት›› አዋጅ ነጋሪና ሓዋሪያ መሆን ማለት ምን ማለት ነው?
7. ክርስቶስ ‹‹ራሱን ለሁሉ በዛ ሠጠ›› የሚለው ሓሳብ በግል ሕይወትህ ምን ትርጉም ይሰጥሃል? ይህ ትርጉም በዕለት ተዕለት ሕይወትህ ላይ ምን ዓይነት ተጽህኖ ሊያመጣ ችሎአል/ይችላል ወይም ማምጣት አለበት? (2ቆሮ.5፡14-21፣ 1ዮሃ 2፡1-2፣1ጴጥ.2፡24-25)

 


ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?