Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

የጥናት 6  1ጢሞ.2፡8-15


የጥናቱ መግብያ


መግቢያ
በዚህን ቀደም ባደረግናቸው ጥናቶች የተለያዩ ጉዳዮችን ለመዳስ ችለናል፡፡ በመጀመሪያው ምእራፍ አማኞች እውነተኛውን ትምህርት እንዲማሩ መርዳት እንደሚያስፈልግ አየን፡፡ ቀጥሎም ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ የእግዚአብሄር ፈቃድና ዓላማ መሆኑን፣ ክርስቶስም ራሱን ቤዛ (መተኪያ) አድርጎ የሰጠው ለሰው ሁሉ መዳን መሆኑን አየን፡፡ ስለዚህ ደግሞ አማኞች ስለ ሰዎች ሁሉ በመጸለይ ከዚህ የእግዚአብሄር ፈቃድ ጋር መተባበር እንዳለባቸው አይተናል፡፡


የዛሬው ጥናት ደግሞ፣ ከማስተማርና (ም. 1) ከጸሎት (ም.2) በተጨማሪ፤ በዕለት ተዕለት ኑሮአችን፣ በሥራችንና በአኗኗራችን የእግዚአብሄርን ፈቃድ ማድረግ ወይም ከእርሱ ጋር መተባበራችንን የምናሳይበትን መንገድ የምንማርበት ክፍል ነው፡፡

የጥናቱ ዓላማ፡
ተሳታፊዎች በሚያደርጉት ማናቸውም ነገር እግዚአብሄርን ከማከበር ፊላጎትና ለሌሎች ሕይወት ከመጠንቀቅ አንጻር ወይም ሌሎች ወደ ድነት እንዲመጡ ከመርዳት አንጻር እንዲያደርጉ ማሳሰብ ነው፡፡

የጥናቱ ክፍል 2፡8-15

ማጥኛ ጥያቄዎች
1. የጥናት ክፍሉን ቢያንስ ሁለት ጊዜ በጋራ አንቢቡ፡፡

2. የጥናት ክፍሉን ሃሳብ በአጭሩ በራሳችሁ አገላለጽ ለተሳታፊዎች ተናገር፡፡

3. በዚህ ክፍል መሠረት፣ ጢሞቴዎስ እንዲያገለግላቸው በተጠራበት ማህበረሰብ ማካከል ምን ዓይነት ጾታን ማዕከላዊ ያደረጉ ችግሮች (ማለትም በወንዶች አከባቢና በሴቶች አከባቢ የሚታዩ ክርስቲያናዊ ያልሆኑ ልምምዶች) ይታዩ ነበር? እነዚያ ችግሮች እንዴት የአምልኮን ሕይወት ይጎዳሉ? (በተጨማሪም 1ነገ.3፡5-13 ማቴ. 5፡22-25፤21፡18-22፣ ያዕ.1፡5-8 1ጴጥ.3፡1-12 አንብቡ)፡፡

4. ሴቶች ራሳቸውን ቢሸላልሙ መጽሃፍ ቅዱስ አይከለክልም፡፡ ነገር ግን በቁ 9-10 ‹‹በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ›› ይላል፡፡ ‹‹ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር›› የሚለውን ሓሳብ እንዴት ትረዳለህ? (ለተጨማሪ መረጃ 1ሣሙ.16፡7 አንቢቡ)

5. ‹‹እግዚአብሄርን እንፈራለን የሚሉ ሴቶች›› ለምን ከሌሎች ሴቶች ይልቅ የፈለጉትን ከማድረግ ይከለከላሉ?(1ጴጥ.3፡4-6) (ማሳሰቢያ፡-ይህ ደግሞ እያንዳነዳችን ክርስቲያኖች በአኗኗራችን ከሌሎች በተለየ ሁኔታ በጥንቃቄና በመጠን በመኖር የምናስተመረውን/የምንመሰክረውን ወንጌልን ማሳየት እንዳለብን ያሳያል፡፡ ውቤትንም በአለማዊ ምዛን ሳይሆን በእግዚአብሄር ምዛን ማየት አለብን፡፡ ዓለም በውጫዊ ገጽታ ሲታይ፣እግዚእበሄር ግን ከልብ የሚወጣውን ሓሳብ ይመረምራል፡፡)

6. ጳውሎስ ከሰዎች ውድቀት ታሪክ ጋር በማያያዝ ሲናገር ዓላማው የሴቶችን ለአገልግሎት አለመብቃት ለማስተማሪ ይመስላችኃልን? (በተጨማም 2ጢሞ.3፡6-7፣ የሓሥ 18፡24-28፤ ቲቶ 2፡3-4፤2ጢሞ.1፡5፤3፡15) አንቢቡ)

7. ‹ክርስቲያኖች ሁሉ፣ ስለ ሌሎች መዳን ሲባል የራሳችውን ነጻነት መስዋእት ማድረግ ሊያስፈልጋቸው ይችላል› ብንል፣ከዚህ አባል ጋር ምን ያክል ትስማማለህ? (በተጨማሪ 1 ቆሮ.10፡31-33 አንቢቡ፡፡)

8. ከዛሬው ጥናት ምን የሚጠቅም ነገር አገኘህ?

 

ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?