Sagalicha Dhiigicha Hafuurichaቃሉ ደሙ መንፈሱ |
|||||||
The Word the Blood the Spirit |
|||||||
|
ጥናት 16: 1ጢሞ.6፡5-12
ጳውሎስ ደግሞ ጢሞቴዎስን ሲመክረው፣ ልቡን ሊያስቀምጥበት አስፈላጊ የሆነውን በመጠቆም፣ ሌሎችን ነገሮች ከመከተል እንድጠበቅ ይጠይቀዋል፡፡ ይህም የዘላለምን ሕይወት በመያዝ ነው ይለዋል፡፡ ጌታ ኢየሱስም በሚያስተምርበት ጊዜ፣ ሰው መዝገቡ ባለበት በዚያ ልቡ ደግሞ አለና፣ መዝገባችሁን በሰማይ ሰብስቡ ብሎአል፡፡ ጳውሎስም፣ ጢሞቴዎስ የዘላለምን ሕይወት ለመያዝ መከተል የሚገባቸውን የሕይወት ዘይቤያት ዘርዝሮ ይነግረዋል፡፡ በዚህ ጥናት እነዚያን ዝርዝሮችና በተቃራኒው ያሉትን ጥቅት ነገሮች እናጠናለን፡፡ የጥናቱ ዓላማ የጥናቱ ክፍል 1ጢሞ.6፡5-12 2. የምንባቡን አጠቃላይ ኣላማ በአንድ አጭር ዐረፍተ ነገር ተናገር፡፡ 3. ከቁ 6-8 ባለው ክፍል ውስጥ እንዴተገለጸው ‹‹ኑሮዬ እበቃኛል›› ማለት ምን ማለት ነው? ሰው እንዲህ ማለት የሚችለው መቼ ነው? ዘኁል.24፡10-14፤2ጴጥ.2፡15-16፣ማቴ.6፡25-33፤13፡22፣ፍል4፡11-13፣ ዕብ.13፡5-6) 4. ‹‹እግዚአብሄርን መምሰል ማትረፍያ ነው›› የሚለውን አገላለጽ እንዴት ተረዳላችሁ? 5. በቁ.9-10 ላይ እንደተገለጸው፣ የሕይወት ዓላማቸውን ‹‹ባለጠጎች የመሆን ፍላጎት ብቻ›› ላይ የመሠረቱትን ሰዎች ምን ምን ችግሮች ያጋጥሟቸዋል? በእያንዳነዳቸውን አንድ በአንድ ተነጋገሩበት፡፡ 6. ‹‹ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ስር ነው›› የሚለውን አገላለጽ እንደት ትረዱታለችሁ? ( 7. እኛስ ገንዘብን መውደዳችንንና አለመውደዳችንን እንዴት ልናውቅ እንችላለን? ገንዘብ ወዳጆች ሆነን ራሳችንን ከአገኘንስ አሁንና ከአሁን በኋላ ምን ማድረግ ይኖርብናል? (ቁ 11-12 ንም አገናዝቡ)፡፡
ተክሉ ተ. ጉታ ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት
E-mail: [email protected]
|
Waaqayyo si jaallata
Ati Eessa? |
|||||