Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

የጥናት 2


የጥናት ክፍል 1ጢሞ.1፡6-17
የጥናቱ መግብያ፡

ይህ ክፍል ስለህግ አጠቃቀም ያስረዳል፡፡ ሕግ ከህግ በታች ላሉት ሁሉ ይሠራል፡፡ ሰው ግን በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት ባገኘው ጽድቅ ውስጥ ስኖር የህግ ተገዢ አድርጎ ራሱን ማየት የለበትም (ገላ.3፡10-14)፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ የዘላለም ሕይወት ማገና መንገድ ነው፡፡

የጥናቱ ዓላማ፡(ለአስጠኚ ብቻ) አማኞች በህግ መፈጸም ችሎታቸው ላይ ሳይሆን፣ በክርሰቶስ ኢየሱስ በማመን በሚገኘው ድነት ላይ እንድተማመኑ መርዳት፡፡ በተጨማሪም፣ ተሳታፊዎች ከህግ ጋር አያይዘው በሚያስተምሩት ትምህርትና በሚፈርዱት ፍርድ ላይ አግባባዊ የሆኑ ጥንቃቄ መውሰድ እንዳለባቸው ለማስገንዘብ፡፡

የጥናቱ ጥያቄዎች
1. የጥናቱን ክፍል በሚገባ ደጋግማችሁ አንብቡ፡፡

2. የጥናቱን ክፍል አጠቃላይ ሃሳብ በራስህ አገላለጽ ለቡድንህ አስረዳ፡፡

3. በቁ 6 መሠረት፣ የስህተት አስተማሪዎች ችግር ምኑ ጋ ነበር?

4. የህግ ጥቅሙ ምንድን ነው? ማንንስ ለመከልከል/ለማስጠንቀቅ ነው?

5. ከቁ 9-11 ባለው ምንባብ ውስጥ የተዘረዘሩ ነገሮች በአንድ ክርስቲያን ውስጥ ሊገኙ ይችላሉን? ከተገኙስ ያ ክርስቲያን ምን አይነት እርምጃ መውሰድ አለበት? (ተጨማሪ መረጃ፡- ከአስርቱ ትእዛዛት ከ5-9ያሉትን ያካትታል)፡፡ ሮሜ8፡1-4ንም ጨምራችሁ አንብቡ፡፡

6. ጳውሎስ ደጋግሞ በቁ 12ና17 ምስጋና ያቀረበው ስለምንድን ነበር? ምስጋናውስ በጳውሎ ሕይወት ስለተከናወነው ነገር ምንን ያመለክታል፡፡ (ብዙ ይቅር የተባለለት ብዙ ይወዳል)፡፡

7. በቁ.14 መሠረት፣ የጌታችን ጸጋ ከእምነትና ከፍቅር ጋር ምን አይነት ግንኙነት አለው?

8. በቁ 15 ላይ የተነገረውን ዋና ሓሳብ ለቡድንህ አብራራ፡፡

9. በዚህ ጥናት ውስጥ ጌታችን ኢየሱስን በተመለከተ የተጻፉትን ነገሮች አንድ በአንድ አውጥታችሁ ተነጋገሩበት፡፡

10. ዛሬ ከዚህ ጥናት ምን ጠቃሚ ነገር ተማርክ/ሽ?

11. ስለህግና ስለ ኃጢአትና ጽድቅ በገኘው ግንዛቤ ላይ በደንብ ከሰብከትበት በሃላ፣ በእግዚአብሄር ፍት የጸሎትና የምስጋና ጊዜ ውሰድ፡፡

ማስታወሻ፡- ሕግ ኃጢአትን የሚገልጽ፣ ኃጢአተኛንም ከጻድቁ የሚለይ እንጂ ስለኃጢአተኛ መዳን የሚናገር አይደልም፡፡ ወንጌል ደግሞ ኃጢአተኛ መዳን የሚችልበት መንገድን ያሳያል (ሮሜ 1፡16-19)፡፡

ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?