Sagalicha Dhiigicha Hafuurichaቃሉ ደሙ መንፈሱ |
|||||||
The Word the Blood the Spirit |
|||||||
|
የጥናት 7 1ጢሞ.3፡1-7
የእግዚአብሄር በቴክርስተያን በምድር ላይ የሚትኖረው የእግዚአብሄርን ፈቃድና መንግስት ለሰዎች ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ሆኖም ግን፣ መንገዷንም ሆነ ትህምርቷን የሚቃወሙ፣ የሚያጥላሉና፣ መበረዝ የሚፈልጉ ክፍሎች ደግሞ ሁልጊዜ ከጎኗ ነበሩ ዛሬም አሉ፡፡ ቤቴክርስቲያን ያንን ኣይነት ችግር ከምትቋቋምበት መንገዶች አንዱ፣ ‹‹ያለ ነቀፋ›› የሆነ የአኗኗርና የመሪነት ስርኣትን በመገንባት ነው፡፡
የጥናቱ ዓላማ (ለአስጠኚ ብቻ) ፡ የጥናቱ ጥያቄዎች 1. የጥናት ክፍሉን ቢያንስ ሁለት ጊዜ በጋራ አንቢቡ፡፡ 2. የጥናት ክፍሉን ሃሳብ በአጭሩ በራሳህ አገላለጽ ለተሳታፊዎች ተናገር፡፡ 3. በዚህ ክፍል ‹‹ኤጵስ ቆጶስ›› ማለት ምን ማለት ነው (ቁ.5; Acts 20:17-28)? 4. ከቁ 2-7 የተዘረዘሩትን የብቃት መለኪያዎች/መስፈርቶች በቅደም ተከተል ብናስቀምጣቸው፣ የትኛው አሁን ላለንበት ቤተ/ያንና ህብረተሰብ ቅድሚያ ይሰጠዋል? (የሚሰጣችሁን ሠንጠረዥ በመጠቀም፣ ጥያቄውን ለመመለስ ሞክሩ ) 5. ክርስቲያን/አማኝ በሙሉ ወደዚህ ማደግ የግድ ይጠበቅበታልን? ለምን? 6. አንድ ተራ አማኝ (ማለትም ለመሪነት ያልታጨ/ያልተጠራ) እነዚህን ክርስቲያናዊ መሪ መለ ኪያዎች ወደ ማሟላት ለመምጣት ምን ዓይነት ነገሮችን ማድረግ ይጠበቅበታል? (ሚሰጣችሁን ሠንጠረዥ በመጠቀም ይህንን ጥያቄ በውይይት መልሱ፣) 7. እስከምቀጥለው የስብሰባ ጊዜ፣ በግል ጊዜ በመውሰድ፣ የራስን ህይወት በእነዚህ ክርስቲያናዊ እሴቶች ፍትሽና፣ የተማሪከውን ነገር በሚቀጥለው የጥናት ጊዜ ለቡድንህ ተናገር፡፡ (ለመናገር ፈቃደኛ ከሆንህ ብቻ)፡፡ በግላስጎ ያለን አማኞች ሁላችን አሁን ባለንበት ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ ውስጥ ሆነን ክርስቶስን ለሌሎች ለመግለጥ የሚትችል ቤተ/ያን ለመፍጠር፣ እያንዳንዳችን የትኞቹን የመሪነት ቢቃት መስፈርቶች በይበልጥ ማሳደግ/መገንባት ይኖርብናል?
ተክሉ ተ. ጉታ ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት
E-mail: [email protected]
|
Waaqayyo si jaallata
Ati Eessa? |
|||||