Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ጥናት 12: 1ጢሞ.4፡13-15


መግቢያ
1ጢሞቴዎስ ምእራፍ 4ን በምናጠናበት ጊዜ በአንድ የእግዚአብሄር አገልጋይ በአገልግሎት ሕይወቱ ውስጥ ያለማቋረጥ መደረግ የሚገባቸውን ሶስት ነገሮችን እንደምናጠና ባለፉት ሁለት ጥናቶች ላይ አንስተን ነበር፡፡ እነዚያም የእግዚአብሄርን ቃል ማካፈል፣ የእግዚአብሄርን ቃል በተግባር መለማመድና በቃሉ ማደግ ናቸው፡፡

በዚህ ጥናት ሦስተኛውን ነገር እንመረመራለን-- በቃሉ ማደግ፡፡ በተለይ በዚህ ጥናት ውስጥ ሓዋሪያው ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ሲጽፍ፣ እንዴት አድርጎ በቃሉ ማደግ እንዳለበት ይመክረዋል፡፡ በተለይ ደግሞ በቃሉ ማደግን ከራሱና ከሌሎች ድነት ጋር አያይዞ ይነግረዋል፡፡ ምንም እንኳን ሰውን የሚያድነው ክርስቶስ የተገለጠው የእግዚአብሄር ጸጋ ቢሆንም (ሮሜ.3፡19-25፣ ኤፈ.2፤1-8)፣ እምነት እንድኖርና እንድጠበቅ የእያንዳንዱ ሰው በቃሉ ማደግ፣ ይልቁንም ደግሞ የአገልጋዩ እድገት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ብዙዎችን ከእምነታቸው ወደ ሃላ የሚመልሳቸው ነገር በበዛበት ጊዜ፣ ሰዎች ሰምተው፣ ተምረውና አይተው የሚበረቱበት የቃሉ ንባብ፣ እንዴ ቃሉ የሆነ ምክርና ትምህርት ሰው ከእምነት ነገር እንዳይጠፋ ለማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

የጥናቱ ዓላማ
ተሳታፊዎች በቃሉ ለማደግ እንድነሳሱ በማድረግ በክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነታቸውን እንዲይዙና ሌሎችንም በዚሁ አቅጣጫ እንድረዱ ማበረታታት፡፡

የጥናቱ ክፍል 1ጢሞ.4፡13-15
ማጥኛ ጥያቄዎች
1. የጥናት ክፍሉን ደጋግማችሁ አንቢቡት፡፡

2. ያነበባችሁትን ነገር በጭሩ በራስህ አገላለጽ ለቡድንህ ተናገር፡፡

3. በቁ. 13 ላይ ያለው ማሳሰቢያ ከክርስቲያናዊ አገልግሎትና ሕይወት እድገት ጋር ምን ኣይነት ግንኙነት አለው? ለምን በማሳሰቢያ መልክ የተሰጠ የይመስልሃል?

4. በቁ 14 ላይ ያለው ‹ጸጋ›፣ በሮሜ 3፡ 19-25 ውስጥ ከተነገረው ‹ጸጋ› ጋር ምን ኣይነት ግንኙነትና ልዩነት አለው?

5. የእጅ መጫንን ትርጉምና አስፈላጊነት ተወያዩበት፣ አንድ ሰው በሌላው ላይ እጁን የምጭነው ዓላማ ነው?

6. በቁ15 መሠረት አንድ ክርስቲያን ሌሎች ሊመሰክሩት በሚችሉት መልኩ በብስለት ነገሮችን መናገርና ማድረግ የሚችለው ምን ሲያደርግ ነው?

7. በቃሉ ውስጥ የተገለጠልንን የእግዚአብሄር ፈቃድ ማሰብና ማዘውተር እንዴት አድርጎ ለአንድ ክርስቲያን ላይ የሚፈለገውን ሲከት (ማለትም ራሱ ድኖ ሌሎን ማዳንን) ሊያመጣ ይችላል?

8. ሰው በክርስቶስ አምኖ እንደምድን ብዙ የመጽሃፍ ቅድሱስ መረጃ አለ፡፡ እንዲህ ከሆን፣ በቁ 16 ላይ እንደተጻፈው ‹‹ለራስህና ለትምህርትህ መጠንቀቅ›› ከራስህና ከሌሎች ድነት ጋር እንዴት ይያያዛል? (መረጃ፣ ትምህርትህ የሚለው በቃል፣ በኑሮና በተግባር የሚናሳያቸውን አርአያነትንም የሚጨምር ሊሆን ይችላል)፡፡

9. ከዛራ ጥናት የተማርከው አንድ ነገር ቢኖር ምንድን ነው?

 

ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?