Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ጥናት 10: 1ጢሞ.4፡1-6


መግቢያ
1ጢሞቴዎስ ምእራፍ 4ን በምናጠናበት ጊዜ አንድ የእግዚአብሄር አገልጋይ በአገልግሎት ሕይወቱ ውስጥ ያለማቋረጥ መደረግ የሚገባቸውን ሶስት ነገሮች እናጠናለን፡፡ እነዚያም የእግዚአብሄርን ቃል ማካፈል፣ የእግዚአብሄርን ቃል በተግባር መለማመድና በቃሉ ማደግ ናቸው፡፡

በዚህ ጥናት የመጀመሪያውን ነገር እንመረመራለን-- ቃሉን ማካፈል፡፡ በተለይ በዚህ ጥናት ውስጥ ሓዋሪያው ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ሲጽፍ፣ ወቅታዊ የሆነ የመለኮትን ድምጽ/መልእክት እና እንዴት አድርጎ መልእክቱን በተቀባዮች ማስተላለፍ እንዳለበት ይመክራል፡፡ ይህም ሰዎች በክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት ከክፉ መንፈስና ቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚገኙ ከክፉ ሰዎች የተነሳ አንዳይጥሉ ጢሞቴዎስ ማስጠንቀቅ ነበረበት፡፡

የጥናቱ ዓላማ
ተሳታፊዎች አጥብቀው በክርስቶስ ላይ ያለውን እምነታቸውን እንዲይዙና ሌሎችንም በዚሁ አቅጣጫ እንድረዱ ማበረታታት፡፡
የጥናቱ ክፍል 1ጢሞ.4፡1-6

ማጥኛ ጥያቄዎች
1. የጥናት ክፍሉን ደጋግማችሁ አንቢቡት፡፡

2. ያነበባችሁትን ነገር በጭሩ በራስህ አገላለጽ ለቡድንህ ተናገር፡፡

3. ጳውሎስ ይህንን መልእክት ሲጽፍ አጥርቶ የሰማው የማን ድምጽ ነበረ? ተቀብሎት እያስተላለፈ ያለውስ መልእክት ምንድን ነው? (በተጨማሪም የሓሥ.20፡26-32 (ለኤፈሶን ሽማግለዎች)፣ 1ቆሮ.11፡2-6፤ አንቢቡ፡፡)

4. በቁ. 4ና5 ላይ የተገለተጸውን ሓሳብ እንዴት ትረደዋለህ?

5. በቁ.6 መሠረት፣ አንድን አገልጋይ መልካም የክርስቶስ አገልጋይ የሚያስብለው ምንድን ነው? (በተጨማሪም ማቴ.7፡13-23፤16፡21-23፤፤ አንቢቡ፡፡)

6. አሁን ባለንበት ወቅት እየመጣ ያለው የመንፈስ ቅዱስ ድምጽ/መልእክት ምን የምል ይመስልሃል? ያነ የተናገረው ነው ወይስ የተለየ? ለምን?

7. ከዛሬው ጥናት በግልህ ምን ተምረሃል?

 

ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?