Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት
ከዚህን ቀደም
- ኢየሱስ ከገሊላ ባህር ወዲያ ለመሻገር መናሳቱና በመንገድ ላይ ችግር ደቀመዛሙርቱን አጋጢሞአቸው እንዴነበር አይተናል፡፡ ኢየሱስ ግን ችግሩን ሁሉ በቃሉ አሸነፈና ወደ ማዶ ደረሰ፡፡

- የገሊላንም ባህር ከተሻገረ በኃላ፣ ለረዥም ጊዜ በአጋንንት ጭፍሮች ታስሮ የነበረውን ሰው ፈወሰው፡፡ ሰየውም ራቁቱን ሆኖ በመቃብር መካከል ራሱን እየጎዳና እየተጨነቀ የመኖር ዘመኑ አብቅቶ፣ ወደ ልብ የተመለሰ፣ ለአካባቢው ሰላምን የሚሰጥ/ጨዋ፣ እንደሰው ለብሶ የሚሄድና የእግዚብሄርን ሥራ መስራት የሚችል ሰው ሆነ፡፡

- ይህም ሁሉ ሊከናወን የቻለው የእግዚአብሄር ልጅ ኢየሱስ ባህርን ተሸግሮ ወደ እርሱ በመሄዱና በሥልጣኑ በእርሱ ላይ ሰፍረው ያሰቃዩት የነበሩትን አጋንንቶች ሲያስወግድለት ነበር፡፡ ኢየሱስ ያድናል፡፡ ዛሬም ኢየሱስ ነጻ ያወጣል፡፡

- ሰውዬው ከዳነ በሃላ የመመስከርን ኑሮ በመኖር በአካባቢው ላይ ተጽኖ ማምጣት እንደ ጀመረም አንስተን ነበር፡፡
- ኢየሱስ ወደ ሃገራቸው/መንደራቸው ተሻግሮ ያደረገውን ተዓምር ያዩ ሰዎች እርሱን ከመቀበልና ከማመስገን ይልቅ፣ ሀገራቸውን ለቆ እንዲሄድላቸው ለመኑት፡፡ ከዚሕ የተነሳ ኢየሱስ ተመልሶ ወደ ነበረበት የገሊላ ባህር በስተምዕራብ ተመለሰ፡፡ በተመለሰም ግዜ ሰዎች በባህሩ ዳር ቆመው ሊቀበሉት ይጠባበቁ ነበር፡፡

-ኢየሱስ እጅግ ትሁት ስለነበር አስገድዶ ይህ ዓለም መጀመሪያውኑ የአባቴ ነው፣ በሥራውም ተሳትፈአለው አላለም፡፡ በዚያ የተደረገውንም ተዓምርና ብዙ ተጨማሪ አድርጎ ራሱን ማስከበር ይችል ነበር፡፡ ሆኖም ግን ሰዎቹ በፈቃዳቸው ልቀበሉት ስላልፈለጉ፣ ወደሚፈልጉትና ወደሚቀበሉት ሄዴ፡፡ ለእነዚህ ደግሞ ምስክር አስቀርቶላቸው ነበር የሄደው፣ ምናልባት ሓሳባውን ቀይረው የእግዚአብሄርን ልጅ ይቀበሉ እንደሆነ፡፡ ከአጋንንት እስራት የዳነውም ሰው እየዞሬ ማስተማር ጀመረ፡፡

- ሰው ያዳነውን ኢየሱስን፣ ድንቅ ስራውንና ቃሉን መናገር ሲችል ከራሱ ተርፎ ሌሎችን መርዳት የሚችል ሥራ ያዜ ማለት ነው፡፡

....መቼት?....

ዛሬ የምናየው ክፍል ኢየሱስ ተመልሶ ከተሸገረ በኃላ የሆውንና የተደረገውን ነው፡፡

- ኢየሱስ ይህንን በሚያደርግበት ጊዜ፡፡
- ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሲያስፈራራ በነበረው በህር ሂዶ መመለስ በቻለበት ጊዜ ነበር፡፡
- ሰዎች ስለኢየሱስ ሥራ ምስክርነት ሰምተው እርሱን በሚፈልጉበት ጊዜ ነበር፡፡
- አንዳነድ ጊዜ አላሳልፍ ያለንን ነገር ጌታ በቀላሉ ተመላልሰን (ወጥቶ በመግባት) እንድንሰራ ያደርገናል፡፡ ይህ ማለት ለደቀ መዛሙርቱ የድል ግዜ ነበር፡፡
- ለኢያርዎስ ደግሞ የፍርሃትና የጣር ግዜ ነበረ፡፡ ስለዚህ መፍትሄ የተባለን ነገር ሁሉ በፍጥነት ማግኘት የሚፈልግበት ጊዜ ነበረ፡፡
- ደም ይፈሳት ለነበረች ሰትዮ ደግሞ ስለኢየሱስ ከመስማትዋ የተነሳ እምነቷ አድጎ ፈውስን ለማስቀበል የደረሰበት ጊዜ ነበረ፡፡
-- እንግዲህ አፋጣኝ መፍትሄ ፈልጎ ለሚሯሯጠውም፣ እምነቷ በቃሉ እያደገ ላለችዋም ኢየሱስ ሊገኝ ባሕሩን አቋርጦ መጥቶ ነበር፡፡

...በቦታው እነማን ነበሩ?....

-- ኢየሱስ ነበረ፣ ደቀ መዛሙርቱ፣ ያይሮስ፣ ብዙ ህዝብ፣ ደሚ የሚፈፈሳት ሰትዮ ነበሩ፡፡

ያይሮስ ማን ነበረ?
- የቤቴ-መቅደስ አለቃ፡፡ ቤቴ መቅደስን የሚያስተዳድር ሰው፡፡ በሌላ መንገድ የሓይማኖት መሪ፣ ማን ያገልግል፣ ማን ይገልገል፣ አንዴት አገልግሎቱ ይካሄድ ብሎ የአምልኮ ሥርዓቱንና ቦታውን የሚያመቻች ሰው ነበረ፡፡ ይህ እርሱ የሚያውቀው አምልኮ የአይውድ እምነት ነበረ፡፡
- በጊዜው አብዛኞች የቤተ-መቅደስ መሪዎች በኢየሱስ አማኞች አልነበሩም፡፡ አንዱ ግን ለኢየሱስ ከኢሳይያስ መጽሃፍ እንዲያነብ ሰጥቶት ነበር፡፡
- ምናልባት ስለኢየሱስ ሥራዎች በአከባቢው ሲወራ ሰምቶአል፣ ምናልባትም እርሱ በሚመራበት መቅደስ ኢየሱስ ሰዎችን ፈውሶ ነበር፡፡

....ምን ሆነ?....

- የያይሮስ ሴት ልጅ ታማ ሞት አፋፍ ነበረች፡፡ የ12 ኣመት ልጅ ነበረች፡፡ ብቼኛ ልጁም ነበረች፡፡
ሲለዚህ በተቸገረ ጊዜ ክብሩንና አገልግሎቱን፣ ዝናውምን ሁሉ ቁጭ አድርጎ ኢየሱስን ሊመና ሄዴ፡፡ ባገኘውም ጊዜ በእግሩ ላይ ወድቆ ለመነው፡፡
- ይህ ለእንድ በሕብረተሰቡ ውሰጥ ለተከበረ ሰው ቀላል ነገር አልነበረም፡፡ የምኩራብ አለዋው ግን ሃይማኖተኝነቱን ትቶ፣ ሥልጣኑን ትቶ፣ ይሉኝተታንም ሁሉ ትቶ፣ ከእርሱ ለሚበልጠውና ለሚገባው፣ ችግሩንም ሊፈታ ለሚችለው ወድቆ ሰገደለት፡፡
- ኢየሱስም ይህ ፀሎት ከልብና እውነተኛ ነውና ሰማው፡፡ ስለዚህም እርሱ የሚፈልገውን ለማድረግ ወደ ቤቱ ከእርሱ ጋር ጉዞ ጀመረ፡፡
- በእርግጥ በጉዞ መጀመሩና ቤት መድረስ መካከል ነገሮች ጣልቃ እየገቡ ነበር፡፡ አንደኛው ተስፋ አስቆራጭ ወሬ ነበር፡፡ ‹‹ልጅህ ሞታለችና መምህሩን አታድክመው›› የሚል፡፡ ሌላው ደግሞ ኢየሱስን በሚያስገርም ሁኔታ ከጉዞ ያስቆመችው ሴትም ነበረች፡፡ ያንን ማድረግ የቻለችው በእምነቷ ነበረ፡፡
- በሕወታችን ትልቁ ችግር ለነገሮቻችን መፍትሔ አለመኖራቸው ሰይሆን 1. መፍትሔ የሚናገኝነበትን ቦታ አለማወቅ 2. አውቀንም በእምነትና በእውነት አለመቅረብ ነው፡፡
- ይህቺ ሴት ብዙ ዘመኗንና ገንዘቧን ባለመድያኒቶች ጋር ጨረሰች፡፡ ገንዘባችን ሊረዳን የሚችለው እስከተወሰነ ደረጃ ቢቻ ነው፡፡ ያልቃል፡፡ ባያልቅም የምንፈልገውን ሁሉ አናገኝበትም፡፡ ገንዘብ መግዛት የማይችላቸው ብዙ ነገሮች ስላሉ፡፡ ይህቺ ሴት የባለመድሃኒቶችን ምክርና መድሃኒት መግዛት ችላ ነበር ግን ፈውስ አላገኘችባቸውም፡፡ ገንዘበቡ ባለቀ ጊዜ ደግሞ ምክሩም መዲያኒቱም አይገኝም፡፡
-የመጨረሻ ሚርጫዋም ቢሆን የሚበልጥ ክብደቴን በእምነት ሰጠችው፡፡ ኢየሱስ ያድናል የሚባለውን ዕውቀት ብቻ አላደረገችም ግን አመነች፡፡ መንፈሳዊ ነገሮችን አውቆ መስበክና አምኖ ማድረግ በሕይወታችን ውስጥ ከእግዚአብሄር የምንፈልገውን በማግኘት ውስጥ የተለያዬ አክሰስ ለቨል ይሰጡናል፡፡
- ስለዚህ ብዙ ወረኞችና አጋፊዎች ያለገኙትን ፈውስ ተደብቃ ሂዳ አገኘች፡፡ አንዴ ያይሮስ በአደባበይ መለመን አልቻለችም፡፡ ምናልባት በችግሯ አፍራ ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባትም የእርሷ ዓይነት ሴቶች ተገለው መቀመጥ ነበረባቸው፡፡
- ሆኖም ግን ሌሎች በሚፈጥሩት ግርግር ተጠቅማ ፈውስ ጋር መድረስ ትፈልግ ነበር፡፡ ከልካይ የሚመስሉ አጋጣሚዎች በእምነት ስለሄደች ሚቹ ውኔታ ፈጠረላት፡፡

- ኢየሱስን ግን መስረቅም መሸወድም አይቻልም ነበር፡፡ ሰው ሰውን ደብቆ መጠቀሚያ ሊያደርግ ይችላል፡፡
- በድብቅ የተገኘው ፈውስ በአደባባይ እንዲሰበክና ለትውልድ መተላለፊ የሚችል አስተማሪ ታሪክ ሆኖ እንዲጻፍ አደረገ፡፡

ቁ. 35-36፡፡ በዚህ ንግግር ወቅት ሌላ ወሬ መጥቶ ነበር፣ የኢያኢሮስ ቤት አንድ መልእክት መጥቶ ነበር፡፡ ‹‹ልጂህ ሞታለች›› የሚል፡፡
- መልእክቱ የመጣው ኢየሱስን ትቶ ወደ ቤቱ ህዶ ሬሳውን እንታቀፍ ነበር፡፡
- ምንም እንኳ ፀሎታችን የተሰማ ቢሆነም፣ ለጊዜው ነገሮች የባሴ መጥፎ የሚሆኑበት ጊዜ አለ፡፡
- የነገሮች መጨረሻ ደርሶ መበርታት ምናልባት የመጨረሻ ተስፋችንን ቆርጠን ወደ ሞቱብን ነሮቻችን ልባችንን እንዲንመልስና ከጌታ ጋር የጀመርነውን ጉዞ እንዲናቆም ነው፡፡
-ኢየሱስ ግን ወደ ሬሳህ ብቻህን አትሂድ ይላል፡፡ አብረን እየሄድን ስለሆነ አብረን ይህንን ጉዞ እንቀጥላለንና እምነት ይኑርህ፣ ተረጋጋም እያለው ነበር፡፡
- ኢየሱስ በኢያሮስ ቤት ያገ ኛቸውን ‹‹ሲንጫጩና ሲያለቅሱ ዋይታም ሲያበዙ›› ያያቸውን ሰዎች ወደ ተኣምር ዕፍራው ቦታ ይዞአቸው አልገባም፡ ጌታ ሲመጣ ‹‹ዝም ብሎ የእርሱን ማዳን ማየት›› ነው እንጂ ሁካታ እየፈጠሩ የጌታ ቃል እንዳይሰማ ማድረግ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ሰዎቹን ባያስወጣ ኖሮ ኢየሱስ ምን ብሎ እንደ አስነሳት ፣ ምን ብሎ ቤተሰቦቿን እንደተናገረ ስለማይሰማ፣ ብዙ መላምቶች ይፈጠሩ ነበር፡፡

- ሙታን የእግዚአብሄርን ልጅ ድምጽ ይሰማሉ፡፡ ኢየሱስ መኖርን ስለወሰነባት፣ ሞታም ቢትሆን ‹‹አንቺ ልጅ›› ብሎ ነበር የጠራት፡፡ በእግዚአብሄር ሓሳብ ውስጥ የተወሰነ ነገር ያለቀ ነገር ነው፡፡ ለዚሀም ነው ቃሉን ሰምቴን እንደሚሆንልን በእምነት መቀበል ያለብን፡፡ እግዚአብሄር ሳያስብ አይናገርም፣ እርሱ አስቦት የተናገረው ነገር ደግሞ እንዲፈጸሙ ትእዛዝ የወጣባቸው ነገሮች ናችው፡፡

- አንዳይናገሩት የከለከለው ሌሎች ቀሪ ሥራዎች እንደፈጸሙ ነው፡፡

- ምግብ እንዲሰጣት ያዘዘው ያዩት ነገር ትክክልና እውነተኛ እንጂ ቅዠት እንዳልነበረ ሊያረጋግጥላው ነበር፡፡

 

ከኢየሱስ ሕይወት ምን እንማራለን
- በፍጥረት ላይ ጌታ ነው፡፡
- የሰዎችን ምርጫ ያከብራል፡፡ ግን እውነትን እንዲረዱ ሊረዳቸውን የሚችል ነገር ደግሞ ይሰጣቸዋል፡፡
- አገልግሎቱ በቦታና በሁኔታ የተወሰነ አልነበረም፡፡ በበቴ መቅደስም፣ በባህር ላይም፣ በመንገድ ላይም፣ በቤትም፣ በቀንና በሌሊት ያድናል፡፡
- ለተጨነቁት፣ ለጎዱት፣ ለታመሙት፣ ለፈሩት ልመናቸውን ሰምቶ ይደርስላቸው ነበር፡፡
- በእምነት የሚቀርቡትን ሰዎች ጸሎትና ድርግት ያከብር ነበር፡፡
- መለኮታዊ አቅምና ክብር ነበረው፡፡ ስሰገድለት አትስገድልኝ አላለም፡፡ ሥግደት ለአምላክ ብቻ እንዴሚገባ ደግሞ በሰይጣን ስፈተንም ተናግሮ ነበርና፡፡ አምላክነት ባይኖረው ያይሮስን በገሰጸው ነበር፡፡

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?