Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት

ማር 6 30-44 ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ማመር

30 ሐዋርያትም ወደ ኢየሱስ ተሰብስበው ያደረጉትንና ያስተማሩትን ሁሉ ነገሩት።
31 እናንት ራሳችሁ ብቻችሁን ወደ ምድረ በዳ ኑና ጥቂት ዕረፉ አላቸው፤ የሚመጡና የሚሄዱ ብዙዎች ነበሩና፥ ለመብላት እንኳ ጊዜ አጡ።
32 በታንኳውም ብቻቸውን ወደ ምድረ በዳ ሄዱ።
33 ሰዎችም ሲሄዱ አዩአቸው ብዙዎችም አወቁአቸውና ከከተሞች ሁሉ በእግር እየሮጡ ወዲያ ቀደሙአቸው ወደ እርሱም ተሰበሰቡ።
34 ኢየሱስም ወጥቶ ብዙ ሕዝብ አየና እረኛ እንደሌላቸው በጎች ስለ ነበሩ አዘነላቸው፥ ብዙም ነገር ያስተምራቸው ጀመር።
35 በዚያን ጊዜም ብዙ ሰዓት ካለፈ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው። ቦታው ምድረ በዳ ነው አሁንም መሽቶአል፤
36 የሚበሉት የላቸውምና በዙሪያ ወዳሉ ገጠሮችና መንደሮች ሄደው እንጀራ ለራሳቸው እንዲገዙ አሰናብታቸው አሉት።
37 እርሱ ግን መልሶ፦ እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው አላቸው። ሄደን እንጀራ በሁለት መቶ ዲናር እንግዛላቸውን? እንዲበሉም እንስጣቸውን? አሉት።
38 እርሱም፦ ስንት እንጀራ አላችሁ? ሂዱና እዩ አላቸው። ባወቁም ጊዜ። አምስት፥ ሁለትም ዓሣ አሉት።
39 ሁሉንም በየክፍሉ በለመለመ ሣር ላይ እንዲያስቀምጡአቸው አዘዛቸው።
40 መቶ መቶውና አምሳ አምሳው እየሆኑ በተራ በተራ ተቀመጡ።
41 አምስቱንም እንጀራ ሁለቱንም ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረከ፥ እንጀራውንም ቈርሶ እንዲያቀርቡላቸው ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥
42 ሁለቱን ዓሣ ደግሞ ለሁሉ ከፈለ። ሁሉም በልተው ጠገቡ፤
43 ከቍርስራሹም አሥራ ሁለት መሶብ የሞላ አነሡ ከዓሣውም ደግሞ።
44 እንጀራውንም የበሉት ወንዶቹ አምስት ሺህ ነበሩ።"

ባለፈው አብረን ከማርቆስ ወንጌል እያጠናን ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ስንማር ያነሳናቸውን ነገሮች ካስታወስኳችሁ በሃላ ወደ የዛሬው የጥናት ክፍል እናልፋለን፡፡

ከዚህን ቀደም ኢየሱስ በሌሎች የገሊላ መንደሮች ሲያስተምር ከቆዬ በሃላ ወደ ገዛ ሀገሩና ወደ መንደሩ ሰዎች ዘንድ እንደሄደ አይተን ነበርን፡፡ ሆኖም ግን የኢየሱስ መንደር ሰዎች ኢየሱስን ለመቀበል ባለመፈለጋቸው ኢየሱስ ወደ ሌሎች መንደረሮች አልፎ እንዳሰተማረና፣ ደቀ መዛሙርቱን ደግሞ ሁለት ሁሌት አድርጎ እንደላካቸው አይተን ነበር፡፡

ደቀ መዛሙርቱም በኢየሱስ በታዘዙት መሠረትና በተቀበሉት መለኮታዊ ስልጣን ተጠቅመው የንስሃን ስብከት ይሰብኩ፣ አጋንነትን ያስወጡ፣ በሽተኞችንም ዘይት እየቀቡ ይፈውሱ ነበር፡፡

እነዚህ የተላኩት ሰዎች ራሳቸውን ሳይሆን ኢዩሱስን ይሰብኩና የእግዚአብሄርን መንግስት ለሰዎች ያስተዋውቁ ስለነበር፣ የኢየሱስ ወሬ ወደ ሀገረ ገዥው ጆሮ ደርሶ ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳ ትልቅ ፍርሃት በቤተ-መንግስቱ አከባብና በንጉሱ/ሀገረ ገዢው ላይ መጥቶ ነበር፡፡ ከተሰበከው የንሃሓ ስብከት የተነሳ፣ ንጉሱ አድርጎት የነበረው ሓጢአት ይታወሰውና ያስጨንቀው ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳ፣ ኢየሱስን ከመጥመቁ ዮሃነስ ጋር አንድ በማድረግ፣ "አኔ አስገድየው የነበረው ዮሓንስ ተነሳ" እያለ ማውራት ጀመረ፡፡

ሄሮድስ በራሱ እየመሰከረ ከሚናገረው እውነተኛ ታርክ የተነሳ፣ የመጥመቁ ዮሃንስ አሟሟት ተተረከልን፡፡

ከተተረከው ታርክ የነሳም ለእኛ ጠቃሚ የሆኑ ብዙ ትምህርቶችን አግኝተን ውስደን ነበር፡፡ ለማስታወስ ያክል፣
- ሄሮድስ ለንስሓ የተሰጡትን አጋጣሚዎች ሁሉ ሊጠቀም እንዳልቻለና፣ በአንዱ ጥፋት ወደ ሌላው ጥፋት እየጨመረ እንደ ሄዴና በሃላም ዮሓንስን እንዳስገደለው አይተን ነበርን፡፡
- ሄሮዲያስ የሰማችውን ለጽድቅና የንስሃ መልእክት በክፉ መንገድ አይታው ሰባኪውን እስከማጥፋት የሚያደርስ ቅም እንዳከማቸች አይተን ነበር፡፡ ከቅመኝነቷ የተነሳ ደግሞ ለልጅ አይምሮ ቀርቶ ለአዋቅም ዘግናኝ የሆነ ነገር እንዳስደረገቻት አይተናል፡፡ ታዳጊ የሆነች ልጅ፣ በዘመኗ ሁሉ ሊትረሳው የማትችል ነገር በወጭት አሸከመቻት፡፡ ለእርሰዋ መጥቶ የነበረውንም መልካም እድል በእናትዋ ልብ ከሞላው ክፋትና ጥላቻ የተነሳ ልጂቱ ተጠቃሚ አልሆነችም ነበር፡፡
- ዮሃንስ ደግሞ ባገኘው አጋጣሚ ተጠቅም ከእግዚአብሄር የተቀበለውን የንስሃ ስብከት ለሌሎች ሰዎች እንደ ሰበከ፣ ለንጉሱና ለቤተሰቡ አድርሶ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ዋጋ ቢያስከፍለውም እውነትን ከመናገርና ክትን ከመቃውም አልተመለሰም ነበር፡፡
- የእየሱስ ደቀ መዛሙርት ደግሞ የታዘዙትን ከማድረጋቸው የተነሳ በሁሉም ዘንድ መልእክታቸው እንደ ደረሰም አይተናል፡፡

በዛሬው እለት የምንመለከተው ደግሞ ከዚህ ታርክ የቀጠለው ነገር ይሆናል፡፡

ደቄ መዛሙርቱ አገልግሎታቸውን በታዘዙት መሠረት ከፈጸሙ በኃላ መጥተው ለኢየሱስ ዘገባ አቀረቡ፡፡ "ያደረጉትንና ያስተማሩትን ሁሉ ነገሩት"፡፡
- እኛ ክርሲቲያኖች ለሥራችም ለትምህርታችንም (ለምንናገረው ነገር) በጌታ ፊት እናቀርበዋለንና "ይገባል ወይ" እያልን ነገሮችን ማድግ ይኖርብናል፡፡

ኢየሱስ ግን እነርሱን ካዳመጣቸው በሃላ፣ አንድ ነገር መከራቸው "እናንት ራሳችሁ ብቻችሁን ወደ ምድረ በዳ ኑና ጥቂት ዕረፉ አላቸው"፡፡

ለምን ይሆን?

- ለእግዚአብሄር አገልጋዮች የአገልግሎትና የግርግር ግዜ ብቻ ሳይሆን፣ የማረፍና የመታደስ ጊዜም ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነርሱም ጥቅት አርፈው የሆነውን ሁሉ በእግዚአብሁር እንጂ በራሳቸው አንዳልሆነ ካላስተዋሉ ለችግር የተጋለጡ ሊሆኑ ነው፡፡
- ኢየሱስ የነበረው ልምምድ በህዝብ ፍት የሚሰራበት ጊዜና በአባቱ ፊት ደግሞ በጸሎት የሚያርፍበት ጌዜ ነበረው፡፡

- ለምን ለእረፍት ወደ ምድረበዳ እንዲወጡ ተጋበዙ?

- ኢየሱስ ለአገልጋዮቹም ለሕዝቡም ሪህራሄ ነበረው፡፡

- ስለእኔ፣ ስለአንተና ስለአንችም ጌታ ይራራል፡፡

-ኢየሱስ ደቄ መዛሙርቱ አንዲያርፉ ይዞአቸው ወደ ምድረበዳ ጉዞ ቢጀምርም፣ እየሮጡ ሲከተሉት የነበሩ ሰዎች ደግሞ አሳዘኑት፡፡

-"እሬኛ እንደሌላቸው በጎች"-- በጎች እረኛ ከሌላቸው ይቅበዘበዛሉ፣ መዋል ማይገባቸው ቦታ ላይ ጊዜ ያጠፋሉ፡፡ ለመጥፋትና ለአውሬ የተጋለጡ ናቸው፡፡ ኢየሱስ ህዝቡን ሲመለከት እንደዚያ አያቸው፡፡ በእውነት ሕዝቡን የሚጠብቁ መሪዎችና የሃይማኖት አባቶች ሲላልነበሩ ነውን? አይደለም፡፡ ግን ለሕዝቡ የሚያዝንና ለሕዝቡ የሚያስፈልገውን የሚያደርግ አልነበረም፡፡ ረሃብ ነበረባቸው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ይራቡ ነበር፡፡
- በቢሉኅ ክዳን ረኃብ የሚሆንበት ጊዜ እንደሚመጣ፣ ግን የሚራበው ደግሞ እንጀራ ሳይሆን እግዚአብሄር ቃል እንዲሆነ ነቢዩ አሞጽ ተናግሮ ነበር፡፡ ምናልባት ያ በሕይወታቸው እየተከናወነ ሊሆን ይችላል፡፡
- ኢየሱስ ለብዙ ሰዓታት አስተማራቸው ይላል፡፡ ኢየሱስ ሞኝ ኖሮአልን? የሰዎቹን የመስማት ዓቅም ያገናዘቤ (በዘመናዊው ፈልስፊናችን) የትምህር አሰጣጥ ነበረን?
- ያውም ያለፕሮግራም፣ ረጅም ሰዓት አስተማረ፡፡ ድምጹስ፣ በምን ያንን ህዝብ በሙሉ ዝም አሰኝቶ? ልብ አድርጉ፣ በየመሃሉ፣ መዝናኛ፣ ዝማረ፣ ... ያለ አይመስለኝም፡፡ ከሊብ ከሚመጣ የመነካት ዝማሬና መዝናኛ ካልሆነ በስቀር፡፡
- "እኔ ኢየሱስን እንደሚመስል..." ብሎ የተናገረው ሓዋሪያው ጳውሎስም በሓ.ሥ ውስጥ ስብከቱን አስረዝሞ እንደነበረ ሉቃስ ጽፎታል፡፡
- ኢየሱስ ስብከቱን ማስረዘም ስለፈለገ ነበር ወይስ "ማስተማር የሚፈልጋቸው"፣ ህዝቡም ማወቅ ያለባቸው ነገሮች ነበሩ?

- ሕዝብ እየተንጋጋ ሲከተለው፣ ኢየሱስ ቁጭ ብሎ አስተማራቸው፡፡ ምናልባት ቁጭ ብሎ መማር ሕዝቡ የሚፈልጉት አይነት ነገር ላይሆን ይችላል፡፡ ምናልባት እነርሱ ተዓምራት ብቻ ማዬት ፈልገው መጥተው ሊሆን ይችላል፡፡ ሌላም ጉዳይ ለማስፈጸም መጥተው ሊሆን ይችላል፡፡ የሚሆውንና የሚፈጠረውን አድስ ነገር ለማየትም መጥተው ይችላል፡፡

- እነርሱ ለምን ይምጡ፣ ጌታ ግን ያዝንላቸው ነበርና ለሕይወታቸው የሚያስፈልጋቸውን ሰጣቸው፡፡ በመንፈሳዊም ከዚያም በሃላም በቁሳዊም ምግብ አጠገባቸው፡፡

- በህይወታችን ለሚገጥሙን ትልልቅ ጥያቄዎች ከጌታ መስማትና ከእርሱ መታዘዝ ይፈተዋል፡፡
-ደቄ መዛሙርቱ በተላኩ ጊዜ አስተማሪዎች፣ ተአምራት አድራጊዎችች፣ ለበሽተኞች ፈውስ አምጪዎች ነበሩ፡፡ አሁን ጊን በምድረበዳ ኢያሉ አድስ ተግዳሮት ገጥሞአቸዋል፡፡ ለሕዝቡ የሚያቀርቡት ምግብ አልነበራቸውም፡፡ አቅማውም አይችልም፡፡ ስለዚህ ለኢየሱስ የለገሱት ምክር ቢኖር "ሸኛቸው!" የሚል ነበር፡፡

- ጌታ ግን ምን አላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ብዙ ጊዜ እኛ በእኛ እጂ ያለውን ነገር በቂና ለሌሎ ሰዎች መትፍ የሚችል መሆኑን አናምንም፡፡ ስለዚህ ኣይኖቻቸን ሁልጊዜ ወደ ሌላ ያያል፡፡ ከሌላ ቦታ መጥቶ ወይም ሌላ ቦታ ተክዶ የሚገኘውን ነገር ላይ እናተኩራለን፡፡ ጌታ ግን ያላችሁን ነገር አምጡ ሲል፣ ትልቅ ነገር ተናገረ፡፡

1. በእጃችሁ ያለ ነገር አለ፡፡
2. በእጃችሁ ያለው ወደ እኔ ይምጣ፡፡
3. ሰዎቹን አስተካክላችሁ አስቀምጡ አል-- ልክ በቂ ምግብ አለ፣ ልምግብ ተቀመጡ ማለት ነበረባቸው፡፡ ይህም የእምነት እርምጃ ነው፡፡
4. በእጃችሁ ኖሮ ግን ወደ እኔ የመጣው ነገር ለሁሉም ይበቃል፡፡
5. ምግቡ መብዛት የጀመረው ከተቆረሰና መሠጥት ከጀመረ ባሃላ ነው፡፡ አንዳነድ ነገሮቻችን እኛ እንደ ታዘዝን የእምነት እርምጃ መውሰድ ስንጀመር የተአምራት ክፍሉም ይጀመራል፡፡

ይህ ከሆነ በሃላ በቁጥር ብዙ የሆኑ ሰዎች ተከፋፋፍለው በሃምሳና በመቶ እንዲቀመጡ አዘዛቸው፡፡
- ይህም ምናልባት ምግቡን ለማደል/ለማቅረብ አንዲመች ነው፡፡
- በተጨማሪም ጉልበታሙ በልቶ ደካማው እንዳይረሳም ሊሆን ይችላል፡፡
- የተረፈውም ደግሞ እንዲሰበሰብና ለሌሎች ሰዎችና ለሌሎች ጊዜያት እንዲያገለግሉም ሊሆን ይችላል፡፡
- ግን ሁሉም በልተው ጠገቡ፡፡

ከዛሬው ክፍል ከኢየሱስ ምን ተማርን?
-- እርሱ ለሁሉም ግድ ይለዋል፡፡ የሰውን ልጅ ድካምና ፍላጎት ያውቃል፡፡
--›ለአገልጋዮችም ሆነ ለሕዝቡ የሚያረራ ል ነበረው፡፡
-- በምድረ ባዳም ቢሆን እርሱን ሰምቶ የሄደና እርሱን ቢሎ የወጣ ሕዝብ አያፍርም፡፡ በመንፋሳዊውም ለምድራዊውም ያቀርብለታል፡፡
-- ቃሉን መናገርና ማስተማሪ ትልቅ የእሬኝነት ሥራ ነው፡፡ ለብዙችግሮችም መፍትሄ ነው፡፡

በዮሃንስ ወንጌል ውስጥ "የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድግ ነው" እንዳለ በዚህ ክፍል ደግሞ በድርግቱ "የእኔ እረፍት ሰዎች የእግዚአብሄርን ፈቃድ ሲያውቄና ሲያደርጉ ነው" ቢሎአል፡፡

የእኛ ደስታ፣ እረፍት፣ ትልቁ ዓላማ በተለይ በእግዚአብሄር ቤት ውስጥ ሲንኖር ምንድን ነው?

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?