Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት
የማርቆስ ወንጌል 8: 1-13
1 በዚያ ወራት ደግሞ ብዙ ሕዝብ ነበረ የሚበሉትም ስለሌላቸው ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ።
2 ሕዝቡ ከእኔ ጋር እስካሁን ሦስት ቀን ውለዋልና የሚበሉት ስለሌላቸው አዝንላቸዋለሁ፤
3 ከእነርሱም አንዳንዶቹ ከሩቅ መጥተዋልና ጦማቸውን ወደ ቤታቸው ባሰናብታቸው በመንገድ ይዝላሉ አላቸው።
4 ደቀ መዛሙርቱም። በዚህ በምድረ በዳ እንጀራ ከየት አግኝቶ ሰው እነዚህን ማጥገብ ይችላል? ብለው መለሱለት።
5 እርሱም፦ ስንት እንጀራ አላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው፥ እርሱም፦ ሰባት አሉት።
6 ሕዝቡም በምድር እንዲቀመጡ አዘዘ። ሰባቱንም እንጀራ ይዞ አመሰገነ፥ ቈርሶም እንዲያቀርቡላቸው ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ ለሕዝቡም አቀረቡ።
7 ጥቂትም ትንሽ ዓሣ ነበራቸው፤ ባረከውም ይህንም ደግሞ እንዲያቀርቡላቸው አዘዘ።
8 በሉም ጠገቡም፥ የተረፈውንም ቍርስራሽ ሰባት ቅርጫት አነሡ።
9 የበሉትም አራት ሺህ ያህል ነበሩ።
10 አሰናበታቸውም። ወዲያውም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ ዳልማኑታ አገር መጣ።
11 ፈሪሳውያንም ወጡና ሊፈትኑት ከሰማይ ምልክት ከእርሱ ፈልገው ከእርሱ ጋር ይከራከሩ ጀመር።
12 በመንፈሱም እጅግ ቃተተና። ይህ ትውልድ ስለ ምን ምልክት ይፈልጋል? እውነት እላችኋለሁ፥ ለዚህ ትውልድ ምልክት አይሰጠውም አለ።
13 ትቶአቸውም እንደ ገና ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ ማዶ ሄደ።

 

ማር 8፡1-10 ላይ ኢየሱስ ለሁለተኛ ጊዜ ብዙ ሰዎችን ሲያበላ እንመለከታለን፡፡

ይህ የማብላት ሥራ ከመጀሪያው 5000 ሰዎችን ከመገበበት ይለያል፡፡ ምክኒያቱም
5000 ሰዎችን ሲመግብ
- ቤተሰይዳ አጠገብ፣ በገሊላ ሀገር ነበረ
- በእምስት እንጀራና በሁለት አሳ ተጠቀመ
- አብዛኞቹ ተመጋቢዎች አይውዶች ነበሩ
- አጠቃላይ ተጠቃሚዎች ወንዶችንና ሴቶችን ሳይጨምር 5000 ይሆኑ ነበር
- ከበሉት በሃላ የተረፈው 12 ቅርጫት ነበረ፡፡

አሁን በምንመለከተው ክፍል ያለው መመገብ ግን
- በአስር ከተሞች ተደረገ
- አብዛኛው ተጠቃሚ ከአሕዛብ ወገኖች ናቸው
- ሰባት እንጀራንና ጥቅት ዓሳዎችን ተጠቅሞ ነበር የመገባቸው
- 4000 የሚሆኑ ሰዎች ነበር የተመገቡት
- 7ለማት ነበር የተረፈው፡፡ ለማት ከቅርጫት ይበልጥ ትልቅ እንደሆነ መገመት እንችላለን፡፡

ኢየሱስ ይህንን የመመገብ ሥራ የሰራው ከርህራሄ ተነስቶ አንደነበር ማርቆስ ግልጥ አድርጎ ይነግረናል፡፡ በሌሎች ወንጌላት ውስጥ ኢየሱስ በርህራሄ እንደመገባቸው ወንገላዊያን ስዘግቡ በማርቆስ ወንጌል ውስጥ ግን ኢየሱስ ራሱ "እራራላቸዋለሁ" በሎ ተናገረ፡፡

በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ሁለንተናዊ አገልግሎት ይሰጣል፣ ያስፈልጋልም፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ለነፍሳቸው በሕይወት መኖር የእግዚአብሄርን ቃል ከመገባቸው በሃላ፣ ለሰውነታቸው መጠንከርና መበርታት ደግሞ እንጄራን አበላቸው፡፡

ኢየሱስ ከእርሱ ጋር ጊዜ ስለሚያሳልፉት ሰዎች ግድ ይለዋል፡፡
ዛሬም ቢሆን ከእርሱ ለመማር፣ እርሱን ለመከተልና እርሱን በመታመን ወደ እርሱ የሚመጡትን ጌታ አያሳፊራቸውም፡፡ እነዚያን ሰዎች በመንገድ ላይ ይዝላሉ ብሎ ስለ አካላዊ ዝለታቸው ግድ ካላቸው፣ እርሱን ታምነን ወጥተን ወደ ተጠራንበት የዘላለም ህይወት እንድንደርስ ይልቁኑ እንዴት ግድ ይለው ይሁን!

ኢየሱስ በሶስተኛ ቀን ላይ ነው ሰዎቹን የመገበው፡፡ ምናልባት የመጀመሪያ ቀን ላይ መግቦ ብሆን ሰዎች ትምህርቱን በሚገባ ባላዳመጡት ነበር፡፡ አብዛኞቻቸው ደግሞ የራሳቸው ስንቅ ስላላቸው አስፈላጊነቱና ታምራት መሆኑ ግልጥ ባልሆነ ነበር፡፡ እርሱ ግን ስንቃች እስኪያልቅና የምግብ አስፈላገነት በሚታይበት ጊዜ መገባቸው፡፡

ኢየሱስ ሰዎች የራሳቸውን ስጨርሱ የእርሱን በማድረግ ታላቂነቱን ያሳያል፡፡ በወንጌላት ብቻ የተጻፉቱን ብቻ እንኳን ብንመለከት፣
-- 12 ዓመት ደም የፈሰሳት ገንዘብዋን ለባለመድሃኒቶች ሰጥታ ከጨረሰች በሃላ ኢየሰሱስ ፈወሳት፡፡
-- በቃና ዘገሊላ ሠርግ ላይ ኢየሱስ ውሃውን ወደ ወይን የቀየረው ሰዎቹ ያላቸውን ከጨረሱ በሃላ ነበር፡፡
-- በዛሬውም ክፍል ኢየሱ በሦስተኛ ቀን ላይ ሁላቸውም ስንቃቸውን ከጨረሱ በሀሃላ ኢየሱስ ራርቶ አበላቸው፡፡
እውነቱ ሰዎች የራሳቸውን ሳይጨርሱ መታዘዝንም ሆነ ማመን አይቀላቸውም፡፡ እግዚአብሄር ግን እነዚህን ነገሮች ከሰዎች ይፈልጋል፡፡ እርሱን መስማት/መታዘዝ፣ ደግሞም በእርሱ መታመን፡፡ እርሱ እንዴ መካከለኛ ወይም የመጀመሪያው አማራጭ ሳይሆን እርሱ እንደ ብቸኛ አማራጭ መሆን ይፈልጋል፡፡

እነዚያ 4000 ሰዎች ሦስት ቀናት ከኢየሱስ ጋር አሳለፉ፡፡ እኛስ ሌሎች ነገሮቻችን ቁጭ አድርገን ሰዓቶቻችን ከኢየሱስ ጋር ጊዜ ማሳለፍ እንችላለን? በዚህኛውም ሆነ 5000 ሰዎችን በመመገበበት ሰዓት ተአምሩን የማድረግ ፍላጎት ከኢየሱስ እንጂ ከሰዎቹ አልነበረም፡፡

ስለዚህ ኢየሱስ 4ሺኅ የሚሆኑ ሰዎችን ከመገባቸው በሃላ የተረፈው ፍርፋሪ ተሰብስቦ 7ለማት እንደ ነበር ተገልጾአል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳሌ፣ ከፈርሳዊያን ወገን የሆኑት ደግሞ ከመንደሩ ወደ እርሱ ተሰብስበው "ይፈትኑት ዘንድ" ጥያቄ ጠየቁት፡፡
እነርሱ እስከአሁን ኢየሱስ ያደረጋቸውን ነገሮች ሁሉ ከእግዚአብሄር ዘንድ ተልኮ ስለመምጣቱ በቂና አሳማኝ ሆኖ አላገኙትም፡፡ ምናልባትም "ምድራዊ" ብለው ሳይሰይሙት ሁሉ አልቀሩምና፣ አሁን "ከሰማይ ምልክት" እንዲያሳያቸው ጠየቁት፡፡

ኢየሱስ ግን ይህንን በማለታቸው አዘነ፡፡
- ብዙ ጊዜ የጌታን ፀጋ ጥለን፣ በሕይወታችናና በአከባቢያችን ያደረጋቸውን ነገሮች አጣጥለን፣ በእርሱ ከማመን ይልቅ ለማመንና መመለስ የማይፈልገውን ልባችንን በጥያቄዎቻቸን ስንደግፈው እንታያለን፡፡

ጌታ ከሕይወታችን የሚፈልገው ሌላ እኛ ደግሞ እንደ ምክንያት የምናቀርባቸው ሌላ፡፡ እንዲህ አይነቱ የልብ መሸፈትና የእኛም በጥያቄዎቻችን መተባበር ጌታን ያሳዝነዋል፡፡

ይህም ማለት ለማመንና ለመረዳት ብንፈልግ ለዚያ የሚሆን በቂ ማስረጃ አቅርቦአል፡፡

እውነተኛ እምነት አግዚብሄርን በቃሉ መውሰድ ነው እንጂ ምልክት ጥየቃ አይሄድም፡፡

ማቴ 16፡4 ላይ "የነቢዩ ዮናስ ምልክት ብቻ እንደሚሰጣቸው ተናግሮአል፡፡" ማርቆስ ግን ለአይዛብ ስለጻፈ፣ ይህንን ነገር አንልመዘገበ የመጽሓፍት ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡

ኢየሱስ ከዚያ በሃላ ከዚያ ሰፈር ወጥቶ ተሻግሮ ሄዴ፡፡

በዚህ ክፍል ከኢየሱስ የምንማረው፡
--- ሰዎችን ረዥም ግዜ ወስዶ ያስተምር ነበር፡፡
--- የኢየሱስ ሥራ ስለእግዚአብር መንግስት ማሳወቅንና የአግዚአብሄርን ፈቃድ መግለጥን እንጂ ተዓምራትን ማድረግ/ሥልጣኑን ማሳየት ላይ ትኩረት ያደረገ አልነበረም፡፡
--- በአይውድ መንደሮች እንዳደረግ በአይዛቦችም ዘንድ እንዲሁ ያደርግ ነበርና፣ ሰዎችን ሁሉ የመርዳት ዓላማ ነበረው፡፡
--- ምልክቶችንና ተዓምራትን አስፈላጊ ስሆኑ ብቻ ያደርግ ነበር አንጂ ስለተጠየቀና ሰዎችን ለማስደነቅ ብሎ አልነበረም፡፡
--- ኢየሱስ መልካም ያልሆኑ ነገሮችን ሲያይ ያዝን፣ ይቃትት፣ እምብ ይልም ነበረ፡፡


እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?