Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት
ማር 6፡1-6
1. ከዚያም ወጥቶ ወደ ገዛ አገሩ መጣ ደቀ መዛሙርቱም ተከተሉት።
2. ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኵራብ ያስተምር ጀመር፤ ብዙዎችም ሰምተው ተገረሙና። እነዚህን ነገሮች ይህ ከወዴት አገኛቸው? ለዚህ የተሰጠችው ጥበብ ምንድር ናት? በእጁም የሚደረጉ እንደነዚህ ያሉ ተአምራት ምንድር ናቸው?
3. ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምዖንም ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን? አሉ፤ ይሰናከሉበትም ነበር።
4. ኢየሱስም፦ ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ዘመዶቹ ከገዛ ቤቱም በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው።
5. በዚያም በጥቂቶች ድውዮች ላይ እጁን ጭኖ ከመፈወስ በቀር፥ ተአምር ሊያደርግ ምንም አልቻለም።
6. ስለ አለማመናቸውም ተደነቀ። በመንደሮችም እያስተማረ ይዞር ነበር።

ሁኔታዉ፡
**ጌታ ኢየሱስ ከገሊላ ባህር አካባቢ ወደ ገዛ ሀገሩ ወደ ናዝሬት ተመለሰ (ማቴ.2፡ 19-23፡፡
‹‹ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ።
የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ።
እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ።
በአባቱም በሄሮድስ ፈንታ አርኬላዎስ በይሁዳ እንደ ነገሠ በሰማ ጊዜ፥ ወደዚያ መሄድን ፈራ፤ በሕልምም ተረድቶ ወደ ገሊላ አገር ሄደ፤
በነቢያት። ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።››

**ቢሆንም ግን ከሥደት የተነሳ ይንን ያደገበትንና የእናቱን ሀገር/ ከተማ ለቆ ሄዴ፡፡
ማቴ. 4፡ 12-13 ‹‹ኢየሱስም ዮሐንስ አልፎ እንደ ተሰጠ በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ፈቀቅ ብሎ ሄደ። ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ።››

ሉቃ 2፡4-5 ‹‹ዮሴፍም ደግሞ ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ ከገሊላ ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ ቤተ ልሔም ወደምትባል ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ይሁዳ፥ ፀንሳ ከነበረች ከእጮኛው ከማርያም ጋር ይጻፍ ዘንድ ወጣ።››

ሉቃ 2፥39 ‹‹ሁሉንም እንደ ጌታ ሕግ ከፈጸሙ በኋላ፥ ወደ ገሊላ ወደ ከተማቸው ወደ ናዝሬት ተመለሱ።››

ሉቃ 2፥51 ‹‹ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር።››

- ናዝሬት የተናቀች ከተማ ስለነበረች፣ ከናዝሬት መጥቶ እዚህ ግባ የሚባልለት ሰው እንደ ሌሌ አድርጎ የሚያስቡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡

ዮሃ1፡47 ‹‹ናትናኤልም። ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን? አለው። ፊልጶስ። መጥተህ እይ አለው።››

- ምናልባትም የናዝሬት ሰዎች ራሳቸው ኢየሱስን ያልተቀበሉት፣ ራሳቸውን ከመካከላቸው የሚወጡትን ከመናቅ የተነሳም ይሆናል፡፡

** አንዳንዶቻችን የመጣንበትነ ሀገር አይተን፣ ሌሎች ቆዳችንን አይተን፣ ከሌሎች ሰዎች አንጻር ተገቢውን ክብር እንኳ ለራሳችን የማንሰጥ ሊንሆን እንችላለን፡፡
- ኢየሱስ ወደዚህች ዓለም ሲመጣ ግን ቦታ መርጦ ማደግ ሲችል ‹‹የናዝሬቱ ሰው›› ተብሎ ማደጉን ሲመርጥ አላፈረም፡፡ ምናልባትም ያንን የራስና ትውልድን መናቅ መርገም ሊሰብርም ሊሆን ይችላል በናዝሬት የኖረው፡፡
-በኢኛም ሕይወት ሲሆር ለዘመናት እኛና ሌሎች ተቀብለን ያገዘፍነውን መርገማችንን ይሰብራል፡፡ እግዚእብሄር ይመስገን፡፡

- በዚያም ብዙ የሚያስገርሙና በሰው ሃይልና ዕቀት ብቻ ሊደረጉ የማይችሉ ሥራዎችን ሰራ፣ ደግሞም በየምኩራቡ ገብቶ አስተማሬ፡፡
- ትምህርቱን የሰሙና እርሱ የሰራቸውን ታአምራቶች ያዩ የሀገሩ ሰዎች ግን በመገረም ሊያምኑት አልቻሉም፡፡

- የተሰራው ሥራ የሚያስደንቅና ግሩም ብሆንም የሰሙትም ቃል እምነታቸውን የሚጨምርላቸው ቢሆንም፣ ዕውቀታቸውና ልምምዳቸው ግን አንዳይቀበሉት ከለከሉአቸው፡፡
- ‹‹እናውቀዋለን እኮ››፣ ‹‹የሰፈራችን ልጅ ነው እኮ››፣ ‹‹ወንድሞቹና እህቶቹ ከእኛ ጋር ናቸው እኮ›› ማለታቸው እንዳያምኑ አደረጋቸው፡፡

- መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ‹‹ለጣዖት ስለ ተሠዋ ሥጋም፥ ሁላችን እውቀት እንዳለን እናውቃለን። እውቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንጻል። ›› ይላል፡፡ 1ቆሮ. 8፥1

** ሓዋሪያው ጨምሮ ‹‹ጢሞቴዎስ ሆይ፥ በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ፥ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፤
ይህ እውቀት አለን ብለው፥ አንዳንዶች ስለ እምነት ስተዋልና። ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን።›› (1ጢሞ. 6፡20-21)

- ሰው በራሱ እዉቀትና ልምምድ ላይ መሠረት አድርጎ ሲኖር ለሚበልጠውና ለሚጠቅመው ነገር ትርኩረት አይሰጥም፡፡
- የዮሴፍ ወንድሞች አንድ ቀን ዮሴፍ እንደዚያ እንደሚጠቅማቸው ቢያውቁ ኖሮ፣ ሊገድሉት ባልተማከሩ ነበር፡፡ አሳልፈውም በርካሽ ዋጋ ባልሸጡት ነበር፡
- የዮሴፍ ወንድሞች ስለ ሕልሙ ሲሰሙ፣ ቶሎ የመጣላቸው፣ አባታቸው ራሱ ታናሽ ሆኖ ሳሌ በታላቅ ወንድሙ ላይ ስላደረገው ታሪክ፣
- አያታቸው ላባን እንዴት አድርጎ ራሄል እያለች ሊያን ለያእቆብ እንዳጋባ የሰሙት ታርክና፣
- በሊያና በራሄል መካከል ደግሞ ስላለው መቀናናት ነበር፡፡
- በቤታቸው ሁሌም ይህ አይነቱ ፉክክር የተለመደ ነገር ነበር፣ ከአያት፣ ከአባት፣ ከእናቶታቸውም የሰሙት ነገር ከዚኛው ወንድምህ፣ ከዛኛው ወነድምህ ተጠንቀቅ የሚል ነገር ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳ፣ የሚያልም፣ የሚንቀሳቀስ፣ የሚያድግ ወንድም እንደ ችግር ይታይ ነበር፡፡

- እኛም ብንሆን ዛሬ ስለወንድሞቻችን ምን ተሞልተን አለን፣ ምንስ እናስባለን፡፡ ከእኛው ተራ መቆማቸው ወይስ ከኛ ውሃላ መሆናቸው ወይስ ደግሞ መቅደማቸው እንዴ ችግር ይታየናል?
- ይህ አይነት ልምምድ እየሰፋና እየበዛ ይሄዳል፡፡
- እጅግ በጣም የሚገርመው ችግሩ ውስጥና ቅርብ ስለሚበዛ እግዚእብሄር የሚበልጥን ፍቅርና ፀጋ በሥጋ ወንድሞችና ዘመዶች መካከል አበዛ፡፡
- አየሰፋ ሲሄድ ፍቅሩ/መተሳሰሩ እየቀነሰ ሲሄድ መተዋወቁ ደግሞ እንደዚያው እየቀነሰ ስለሚሄድ ክፋቱ እየጨመረ ይሄዳል፡፡

- ምናልባት ይህ አሁን እየሰማችሁ ያላችሁት ነገር ከዛሬው ክፍላችን ጋር ተያይዞ ተነስቶ ላያውቅ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን በኢየሱስ ላይ የደረሰውና ኢየሱስም ያስተማረው ትምህርት አሁን ከሚነግራችሁ ቲዖሪ ጋረ እንደሚሄድ ለመግለጽ እሞኪራለሁ፡፡

- ኢየሱስ በሌሎች ከተሞች ሲያስተምር፣ ሲራው ከአሳመናቸውና ትምህርቱ ካስገረማቸው ከሚያውቁት የራሳቸው ስነመለኮት አረዳድ ጋር፣ ከባህላቸው ጋር፣... ኣያይዘው ይቀበሉት/ይንቁት ነበር፡፡

** የኢየሱስ ቤተሰዎችና የመንደሩ ሰዎች ግን ከሥነ መለኮቱ ይልቅ ትልቅ ችግር ይሆንባቸው የነበረው ‹‹የሚያውቁት ነገር›› ነበረ፡፡
- ይህ ደግሞ የናዝሬት ሰዎች ብቻ ችግር አልነበረም፣ ሰው ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሄር በተለያዬ መንገድ ለሕዝቡ ሲናገር ከበራቸው ቃላት መካከል ‹‹ስሙኝ፣ አድምጡኝ›› የሚሉት በብዛት ተደጋግመው አሉ፡፡
- እግዚአብሄርም ካዘነባቸው ነገሮች መካከል አንዱና ትልቁ የሰው አለመስማት ነበር፡፡ ‹‹ሰምቶኝ ቢሆን፣ አድምጦኝ ቢሆን...፣ እናንቴ ግን አልሰማችሁም...› ይላል፡፡

መዝ. 81፡ 8-16
8 ሕዝቤ ሆይ፥ስማኝ እነግርሃለሁም እስራኤል ሆይ፥ እመሰክርልሃለሁ።
9 አንተስ ብትሰማኝ ሌላ አምላክ አይሆንልህም፥ ለሌላ አምላክም አትሰግድም።
10 ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና አፍህን አስፋ እሞላዋለሁም።
11 ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰሙኝም፥ እስራኤልም አላዳመጠኝም።
12 እንደ ልባቸው ሥራ ተውኋቸው፥ በልባቸውም አሳብ ሄዱ።
13 ሕዝቤስ ሰምቶኝ ቢሆን፥ እስራኤልም በመንገዴ ሄደው ቢሆን
14 ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባዋረድኋቸው ነበር፥ በሚያስጨንቋቸውም ላይ እጄን በጣልሁ ነበር
15 የእግዚአብሔር ጠላቶችም በተገዙለት ነበር፥ ዘመናቸውም ለዘላለም በሆነ ነበር
16 ከስንዴም ስብ ባበላቸው ነበር፥ ከዓለቱም ማር ባጠገባቸው ነበር።

-** ** እግዚአብሄርን ሳይሰሙ ፈቃዱን ማወቅ አይቻልም፣ ፈቃዱን ካላወቁና ካላደረጉ ደግሞ እርሱን ማስደሰት አይቻልም፡፡ ይህ ደግሞ ወጤቱ ወደ መጨረሻ እጅግ የከፋ ይሆናል፡፡
-ኢየሱስ ራሱ ሲናገር ሰዎች በስተመጨረሻ ራሳቸውን ለማጽደቅ ቢለው የሚሉት ነገር ቢሆር ‹‹ አንደዚህና እንዲያ አላደረግንምን›› የሚል ሲሆን የጌታ መልስ ደግሞ ‹‹...የአባቴን ፈቃድ አለደረጋችሁምና አላቅሁኃችሁም›› የሚል ይሆናል፡፡

ማቴ 7፡21-23 ‹‹ በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።
በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።
የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።››

- ጌታን ለመስማት ደግሞ ራሳችን ለመስማትና ለማወቅ የተዘጋጄ አድርጎ ማቅረብ አስፈላጊ ነው፡፡ ‹‹አፍህን አስፋ እሞላዋለሁም›› ቢሎአልና፡፡
ካልሆነ፣ በራሳችን እውቀትና ልምምድ ብቻ ላይ ተመስርተን ነገሮችን የምናራምድ ከሆነ፣ ጌታንም በውሉ የማንሰማ ከሆነ፣ ህይወታችንም፣ አገልግሎታችም፣ ሥራችንም፣ ትዳራችም፣ ሁሉ ነገራችን በችግር ላይ ሊወድቅ ይችላል፡፡
እግዚአብሄር ራሱ እርሱን መስማት እንችል ዘንድ ይርዳን፡፡

- የናዝሬት ሰዎች በኢየሱስ የተሰናከሉት፣ ከሌሎች ሰዎች ይልቅ ክፉዎች ስለነበሩ፣ ሞኞችም ስለነበሩ አልነበረም፡፡ ግን ኢየሱስ ባደገበት መንደር ለመኖር እድል አገኙ፡፡ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት አንዳንድ ጊዜ በሕይወታችን የሚናገኛቸው እድሎች ለሌሎች ጉዳቶች ሊዳርጉን ይችላሉ፡፡ ገንዘብ ለማግኘት፣ ሥልጣን ለማግኘት፣ ለመማር፣ ለመታወቅ፣ ለመብዛት... ያገኘን እድል በአግባቡ ከልተጠቀምንበት ሌሎችንና ራሳችንን ለመጉዳት መንስኤ ይሆናል ማለት ነው፡፡

‹‹ኢየሱስም፦ ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ዘመዶቹ ከገዛ ቤቱም በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው።›› ማር. 6፡4

** ** - ሊያምን የማይፈልግ ሕዝብ ጥያቄዎችን ለማወቅ ካለው ጉጉት ሳይሆን አለማመኑን ለመግለጽ ይጠይቃል፡፡ ስለዚህ የናዝሬት ሰዎች ጥያቄ፣
‹‹2... እነዚህን ነገሮች ይህ ከወዴት አገኛቸው? ለዚህ የተሰጠችው ጥበብ ምንድር ናት? በእጁም የሚደረጉ እንደነዚህ ያሉ ተአምራት ምንድር ናቸው? 3. ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምዖንም ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን? አሉ፤ ይሰናከሉበትም ነበር። ››

- እነዚህ ሰዎች እያሉ ያሉት ይህንን ነው፡- ** ** ‹ማመን ከእኛ አይጠበቅም፣ ምንም መረጃ ቢቀርብ ሊያሳምነን አይችልም፣ እኛ እናውቀዋለን፡፡›

- በእውነት ግን ያዉቁታል? አሁን እንደሚረዳው ከሆነ አለወቁትም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ስለእርሱ የሚመሰክረውን ሰምተዋል? አብ ከሰማይ የሚመሰክረውን ሰምተዋል? ሌሎች ቅዱሳን ፣ እንደ እነ መጥመቁ ዮሃንስ፣ ስለእርሱ የተናገሩትን ሰምተዋል? መላእክትስ ስለእርሱ የተናገሩትን ሰምተዋል? ሌላውስ ይቅር መጽሓፍ ስለ እርሱ የሚናገረውን የእርሱን ሕይወት አገናዝበው አይተውታል? ያደረጉት አይመስለኝም፡፡

- ስለዚህ እውቀታቸው ሙሉ አልነበረም፡፡ እንዲህ አይነቱ ዕውቀት ደግሞ ጎጂ ነው፡፡
- እግዚአብሄር ሲናገር ‹‹ ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፋ›› ቢሎ ነው፡፡
- ጠቢቡ ሰለሞን ደግሞ ‹‹ለሰው መልካም የሚትመስል መንገድ አለች መጨረሻዋ ግን ሞት ነው፡፡››

- የናዝሬት ሰዎች ግን በመንደራቸው እግዚአብሄር ካስነሳለቸው ነቢይ፣ ጌታ፣ ንጉስ የሚያስፈልጋቸውን ፈውስ ማግኘት አልቻሉም፡፡

-- ኢየሱስም ባለማመናቸው ተገረመ፡፡ አልፎቸውም ወደ ሌሎች መንዴሮች ሄዴ፡፡ ቢሆንም ግን ደቄ መዛሙርቱን ሁለት ሁሌት አድርጎ የመንግስቱን ወንጌል ሁሉም መስማት ይችሉ ዘንድ በየመንደራቸው ላኬ፡፡

-- በእውቀታችንና በልምዳችን ብቻ ላይ እንዳንቆም እግዚአብሄር ይርዳን፡፡ እርሱ ሁልጊዜ ፈቃዱን ያሳየን፡፡ አሜን፡፡

-** ጌታን የለመድነው መስሎች ሥረውንና አሰራሩን ብንንቅ እኛው ራሳችን የተናቅን እንደምንሆን ማውቅ አለብን፡፡
- ** አለማመናችን ጌታ በእኛ መካከል ማድረግ የሚችለውን እንዳይከለክል መጠንቀቅ አለብን፡፡

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?