Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት
ማር 7፡14- 23

14 "ደግሞም ሕዝቡን ጠርቶ። ሁላችሁ እኔን ስሙ አስተውሉም።

15 ከሰው የሚወጡት ሰውን የሚያረክሱ ናቸው እንጂ ከሰው ውጭ የሚገባውስ ሊያረክሰው የሚችል ምንም የለም።

16 የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ አላቸው።

17 ከሕዝቡ ዘንድ ወደ ቤት ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ምሳሌውን ጠየቁት።

18 እርሱም፦ እናንተ ደግሞ እንደዚህ የማታስተውሉ ናችሁን? ከውጭ ወደ ሰው የሚገባ ሊያረክሰው ምንም እንዳይችል አትመለከቱምን?

19 ወደ ሆድ ገብቶ ወደ እዳሪ ይወጣል እንጂ ወደ ልብ አይገባምና፤ መብልን ሁሉ እያጠራ አላቸው።

20 እርሱም አለ፦ ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው።

21 ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፥

22 ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና፤

23 ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል።"

 

የዛሬ ሁለት ሳምንት ማር 7፡1-13 ላይ በመመሥረት ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ስንማር ብዙ ለሕይወታችን የሚጠቅሙን ነገሮችን እንዳገኝን አምናለሁ፡፡
ለማስታወስ ያክል
- የኢየሱስ ደቄ መዛሙርት እጃቸውን ሳይታጠቡ ምግብ መብላታቸው ከኢየሱረሳለም ተልከው በመጡት ፈሪሳዊያንና ጸሓፊት ዘንድ ትልቅ ጥያቄ አስነስቶ ነበር፡፡
- ኢየሱስ ግን ከጥያቄው ይልቅ በጥያቄዎቹ ጀርባ ተሰውረው የነበሩትን መረታዊ ችግቶች ላይ መናገር ጀመሬ፡፡
- ኢየሱስ ሰዎች የሚያወሩትን ብቻ ሳይሆን እነርሱ የሚያወሩበትን መነሻ ምክንያት (ሞቲቭ) ይፈትሽ ነበር፡፡
- ስለዚህ ከኢሳ. 29 ጠቅሶ እነርሱ እንዴ ታርክ የሚያነቡትን (በአባቶቻቸው ላይ ጣታቸውን እየጠቆሙ የሚያስተምሩትን) ኢየሱስ ደግሞ "ስለእናንቴ ተናገረ" ቢሎ ያስተምር እንደ ጀመር እናስታውሳለን፡፡
- ይህንንም በማለቱ ኢየሱስ ሰዎቹ ወደ እውነተኛ የአምልኮ ህይወት አንዲመለሱና እግዚብሄር በዘመናቸው ሊሠራ ከተነሳው ድንቅ ነገር ተጠቃሚ አንዲሆኑ ለመምከርና ለማስጠንቀቅ ነው፡፡
- ሌላው ደግሞ "በእግዚብሄር የታወቁ" ሰዎች መሆናቸውንም ጭምር ማስገንዘብ ነበረ፡፡ የድብብቆሽ ሕይወት ከእግዚአብሄር ጋር ለጫወት ብንሞክት ራሳችንን ብቻ እንደምንጎዳም ማሳሰቡ ነበር፡፡
- ጠያቂዎቹ ኢየሱስ ስመልስ ግብዝነት እነደ ነበረባቸው፣ ከእግዚአብሄር ትዕዛዝ ይልቅ የሰው ትዕዛዝ እንደምትበልጥባቸው በግልጽ ተናገረ፡፡

- እየሱስ እነዚህን ነገሮች ሲናገር በነገሩ ግራ የተጋቡት ሕዝቡ ነበር፡፡ ህዝቡ እስከአሁኑን የኖሩት የሓይማኖት መሪዎቻቸው ባዘዙአቸው መሠረት ነውና፣ ያወቁተና የለመዱት የሚያምኑበትም ነገር በኢየሱስ ቀላል ተደርጎ ሲቀርብ መገረማቸው አልቀረም፡፡
-- ይህ አይነት ሁኔታ በሚፈጠርበት ጊዜ ደግሞ (በቀላሉ መገመት እንደሚቻለው)፣
---እንዳንዱ ምን እያለ ነው
---ሌሎች ደግሞ "አላልናችሁም" እርሱ እኮ የሙሴን ህግ አይጠብቅም
---ሌሎች ደግሞ "በእውነት ይህ ሰው ከእግዚአብሄር መሆኑን በምን ኣውቃለሁ"
--- ሌሎችም በተለያዩ አይነት መንገድ ብቻ ሃቦቻቸው በጥያቁ ተሞልቶና ግራ ተጋብቶ ታይቶ ነበር፡፡ ምናለባት ትልቅ ውስጣዊና ውጫቂ ጫጫታዎች ሳይኖሩ አልቀሩም፡፡

ቁ. 14 ኢየሱስ "ሕዝቡን ጠርቶ። ሁላችሁ እኔን ስሙ አስተውሉም" አላቸው፡፡
-- ጠራቸው -- ጆሮ እንዲሰጡት ካሉበት ጫጫታ መካከል ቀሰቀሳቸው፡፡ "እናንቴ" እኔን ስሙኝ፡፡
-- ወደ ራሱ ጠቆመ፡፡ እኔ የተናገርኩትን አኔው በደንብ ማብራራት እችላለሁ፡፡ ሐሳቡን ግልጽ ላደርግላችሁ እችላለሁና "ጆሮ ስጡኝ"፡፡
-- ደግሞም አሁን የሚነግራችሁን በደንብ ስሙ፣ ደግሞም አስተውሉ፣ ይግባችሁ፡፡ አገናዝቡት፡፡ ሎጅኩና የተናገርኩበት ሓሳብ ምን እንደ ሆነ ይግባችሁ፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሰዉ ከእግዚአብሄር ጋር እያለም እርሱን የማይሰማበትና በሌሎች ድምጾች ግራ የሚጋበበት ጊዜ አለ፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ሁሌም ሊገዳደረን የሚችል ነገር ነው፡፡ ስለዚህ እየሱስሰ "እኔን ስሙን"፡፡ በጎቼ ድምጼን ይሰማሉ፡፡ የእግዚአብሄርን ሃሳብ የማያስተውሉ ሰዎች በድምጽ ብዛት፣ በጫጫታ ብዛት፣ በንዝነዛ ብዛት የጉዞ አቅጣጫቸውን ይቀይራሉ፡፡ ስለዚህ ስትሰሙት ለመረዳት፣ በደንብ ለመገንዘብ ስሙኝ አላቸው፡፡

ቁ. 15. "ከሰው የሚወጡት ሰውን የሚያረክሱ ናቸው እንጂ ከሰው ውጭ የሚገባውስ ሊያረክሰው የሚችል ምንም የለም።"
-- የተጠየቅሁት ጥያቄ የቅድስና ጥያቄ ከሆነ፣ የቅድስና ወንዝ የሚፈሰው ከየትኛው ምንጭ እንደ ሆነ ላሳያችሁ፡፡
-- ከሰው ልብ/ሓሳብ እርሱን የሚያረክሰው ክፉ ሓሳብ ይወጣል፡፡ እንጂ ከምትመገቡት ምግብ ጋር የሚያያዝ አይደለም፡፡ አንድ ሰው እጁን ሳይታጠብ መብላቱ መንፈሳዊ ቅድስናውን አይጎዳም፡፡ ምክንያቱም የአፍ የገባው ተመልሶ የሚወጣበት መዝመር ደግሞ ተዘርግቶለታል፡፡
-- ይልቁንስ ከውስጥ የሚወጣው ብዙ ትኩረት ሊሠጠው ይገባል፡፡ ከዋናው ምንጭ ይወጣልና፡፡ ምንጩ ተበርዞ ከሆን፣ መርዛማው ምንጭ ይፈሳል፣ ምንጩ ተቀድሶ ከሆነ ደግሞ የሕይወት ውሃ ወንዝ ይወጠዋል፡፡
-- ስለዚህ ኢየሱስ በሕዝቡ መካከል የተመለከታቸው ብዙ ነገሮች ከእጅ መቆሸሽ ወይም ከተበሉት ምግቦች ጋር ተያይዞ ሳይሆን በልብ ውስጥ ከተፈጠረው መርከስ የሚወጡ ናቸው፡፡ እንግዲህ ኢየሱስ እያለ ያለው ፈሪሳዊያንና ጸሓፍት ስለ እጅ መታጠብ ከባድ ነገር አድርገው በሚያወሩበት በዚያው ሰዓትና በዚያው ሕዝብ መካከል
"...ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፥
ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥
ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥
ስንፍና ናቸውና፤" (ቁ 21-22)

ኤርም. 17፡9-14
9 "የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው ማንስ ያውቀዋል?
10 እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።
11 ያልወለደችውን እንደምታቅፍ ቆቅ፥ እንዲሁ በቅን ሳይሆን ባለጠግነትን የሚሰበስብ ሰው ነው በእኩሌታ ዘመኑ ይተወዋል፥ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።
12 የመቅደሳችን ስፍራ ከጥንት ጀምሮ ክፍ ያለ የክብር ዙፋን ነው።
13 አቤቱ፥ የእስራኤል ተስፋ ሆይ፥ የሚተዉህ ሁሉ ያፍራሉ ከአንተም የሚለዩ የሕይወትን ውኃ ምንጭ እግዚአብሔርን ትተዋልና በምድር ላይ ይጻፋሉ።
14 አቤቱ፥ ፈውሰኝ እኔም እፈወሳለሁ አድነኝ እኔም እድናለሁ አንተ ምስጋናዬ ነህና።"

 

 

--- ኢየሱስ "... ምዕመናን ያልነቁበት ሕይወታቸውን ያረከሰና ከእውነተኛ መንፈሳዊነት የከለከለው ነገር አሁን በጥያቄ መልክ የረበው ነገር ሳይሆን ሌላ ነው" ማለቱ ነው፡፡

--- ከዚህ ነገር ምን እንማራለን
--- ልብህን ጠብቅ
--- ከዋናውን/ኦሪጂናሉን የእግዚእብሄር ሓሳብ አስተውል እንጂ በወግና በሥርዓት ብቻ ተተብትቤህ እያመለኩ ነኝ አትበል፡፡
--- እነዚህ በእግዚአብሄርም በሰውም ተቀባይነት የሌላቸው ነገሮች የሚመነጩት እግዚአብሄርን ሰምቶ ፈቃዱን ከማያስተውል ህዝብ መካከል ስለሆነ፣ "ስሙኝ፣ አስተውሉም"፡፡
--- ኢየሱስ በአሥርቱ ትዕዛዛት ውስጥ የተከለከሉትን ነገሮች በዝርዝር አስቀምጦአል፡፡ ያ ደግሞ የሚያሳየው፣ የእግዚብሄር ትዕዛዛት አልተሸሩም ማለት ነው፡፡
--- በአድስ ክዳን ውስጥ መኖራችን ለሓጢአተኝነት የሥራ ፈቃድ አይሰጠንም፡፡ ግን ወደ ዋናው የእግዚአብሄር ሃሳብ መድረስ የምንችልበትን ጸጋናና የመቅረብን ፈቃድ ነው፡፡

ጌታ ይርዳን፡፡

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?