Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት

- በተጨማሪም ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ በማሳዬት በንስሓ ወደ እግዚአብሄር እንዲመለሱ መጋበዝ ነበር፡፡
- ሌላው ራሱን ስለሌሎች መስዋዕት አድርጎ ማቅረብ ነበር፡፡

2. ተላኪዎች/ምሽኔሪ
- ይህም እንዲሆን እርሱን ሊያግዙት የሚችሉ ሰዎችን፣ ወይም ደግሞ ለተልኮው መሳካት የሚረዱትን ሰዎች መላክና ማሰራት ነበረ፡፡
- ተላኪ የራሱን መልእክት እንዲያስተላልፍ አይጠበቅም፡፡ ካልሆነ ታማኝና ብቁ ተላላኪ መሆን ይሳነዋል፡፡
- ጌታ ኢየሱስ ደቄ-መዛሙርት ተብለው የሚታወቁትን ሰዎች ጠርቶ ለአገልግሎቱ ሾሞ ሲልክ፣ መናገር ያለባቸውንና ማድረግ ያለባቸውን የሌለባቸውንም በደንብ ከነገራቸው በሃላ ነበር፡፡
- የነዚህ ተላኪዎች ትልቁ አላማ ሰዎችን ወደ ንስሃ መጥራት፣ ሰዎች በግላቸው ከእግዚአብሄር ጋር እንዲዛመዱ ማርዳት ነው፡፡ ያንን የሚያደርጉበት መንገድ ደግሞ እንዲናገሩት የተላኩት ነገሮችን በመንገር ነበር፡፡
-

3. ተላኪዎች የሚጠበቁ ነገሮች/ሚሽን ኤይድ ቱልኪትስ፡፡
- በእግዚአብሄር አቅርቦት መታመን አለባቸው፡፡
- እምነታቸውን በእግዚአብሄር ላይ መጣል አለባቸው፡፡
- ከጌታ የተቀበሉት ሥልጣን
- ከጌታ የተቀበሉት ሓይል፡፡
- ከጌታ የተቀበሉት ቃል/መልእክት
** በሓዋሪያት ይደረጉ የነበሩት ምልክቶችና ተአምራት ይሰበክ የነበረው ቃል ትክክል ስለመሆኑ ለማረጋገጥ ነው፡፡

- መስማትና መታዘዝ-- "እኛ የማንጠቅም ባሮች ነን አድርግ ያልከንን ግን አድርገናል" ብሎ ነበር ያስተማራቸው፡፡
- በዘመናችን አገልግሎት ውስጥ የራስ አስፈላጊነት/ሰልፍ እምፖርታንስ/ እንጂ የጌታና የመልዕክቱ አስፈላጊነት አይነገርም፡፡ ከዚህም የተነሳ፣ እንዲወራ የሚፈለገው፣ እንዲታወቅ የሚፈለገው፣ እንዲመዘገብየሚፈለገው የራስ ፍላጎት ነው፡፡ ኢየሱስ ግን በእግዚአብሄር አቅም በተሠራው ሥራ ውስጥ እኛ ያደረግነው ብኖር መታዘዝና እንድንፈጽም የተነገረንን መፈጸም ብቻ ነው እንድንል እስተማረ፡፡
- ስለዚህ ለተላኪዎች ማህበረሰባዊ ሥልጣን/መንፈሳዊ ዓቅም የሌለው ሳይሆን መለኮታዊ አቅም የሚገለጥበት ነገር አለበት፡፡፡፡

4. በተልኮ አላማ ውስጥ ራስን መጠበቅ፡፡ ለተሊኮው መፈጸም የሚያስፈልጉ ነገሮች፡፡
- ሓይል ነው፡፡

የትኩረት አቅጣጫን ለይቶ ማወቅ ነው፡፡

እምነት በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ትልቅ ምና ይጫወታል፡፡
እምነት መገናኛ ነጥብ ነው፡፡

በእምነት ብቻ እግዚአብሄርን ማስደሰት እንችላለን፡፡

እምነት ማለት እግዚአብሄር የሠጠውን ተስፋ ይሆንልኛል ብሎ መቀበል ነው፡፡ ዕብ. 11፡ 1 -

ተልዕኮ አለን ወይ?

ተልዕኮአችንስ ምንድን ነው?

ለተልኮው የሚያስፈልጉ ነገሮችን ከጌታ ዘንድ ተቀብለንናል?

በተልዕኮአችን ላይ ብቻ ትኩረት ሰጥተን እየኖርን ነው ወይስ በሌላ ነፋስ ተወስደናል?

** በሌላ ጎኑ ደግሞ የእግዚአብሄርን ቃል ለመስማትና ለመቀበል፣ እርሱም የሚፈልግብንን ለማድረግ ምን ያክል ዝግጁዎች ነን?
** ይህ ቃል እጅግ በጣም አስፈላጊና ከባድ የሆነ መልእክት ያስተላልፋል፡፡
- ለሚቀበሉት መልካምና አስፈላጊ ሲሆን የሚሰበከውን የንስሃ መልእክት ለማይቀበሉትና ወደ እግዚአብሄር መመለስ ለማይፈልጉት ደግሞ ከባድ ነው፡፡
- ቢሆንም ግን ሰዎች ቢቀበሉትም ባይቀበሉትም ተላኪዎቹ መልእክቱን መናገር መቻል አለባቸው፡፡
- ሰሚዎቹ መልእክቱን ባይቀበሉት ምስክር የሚሆንባቸው ነገር ተደርጎና መልእክቱን ሰሚተው ግን ራሳቸው መቀበል አለመፈለጋቸውን የሚያስታውሳቸው ነገር ተደርጎ ማለፍ አለበት፡፡

** የንስሓ ጥሪ በተለያዬ መንግድ ይቀርብልናል፡፡ ያንን መቀበልና ምላሽ መስጠት የእያንዳንዳችን ሃላፊነት ነው፡፡

የሰደሞንና የገሞራ ሰዎች የሎጥን ምክር አልሰሙም፡፡ እነርሱ መጽሃፍ ወይም ቤተ/ያን ወይም እኛ ዛሬ እንደምናገኛቸው እድሎች አላገኙም፡፡ ቢሆንም ግን ለደረሳቸው መልእክት እስከመጨረሻ ድረስ መልካም ምላሽ ስላልሰጡ እሳት ከሰማይ ወርዶ በላቸው፡፡
ኢየሱስ ግን በፍርድ ቀን ለእነርሱ ይቀላል አለ፡፡ ምክንያቱም ከእግዚአብሄብሄር ጋር ያለመታረቅ ውጤት እስከመጨረሻ ለያይቶ ስለሚያስቀር ነው፡፡ ከእርሱ ለዘላለም መለየት ማለት ደግሞ የዘላለም ስቃይ ነው፡፡

ስለዚህ ንስሓ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ሲሆን የጉዞ አቅጣጫ ለውጥ ማድረግ ነው፡፡

ኢየሱስ የላካቸው ሰዎች እንዲሰብኩ የተፈለገው በተለወጠ የህይወት አቅጣጫ ላይ መሄድ እንዲጀምሩ ነው፡፡

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?