Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት
ማር 3፡1-12
ባለፈው ሁለት ሳምንት ኢየሱስ በመጀመሪያ በእግዚአብሄር ዘንድ ስለነበረው ሓሳብ ሰዎችን ሲያስተምር እንደ ነበር አይተን ነበር፡፡
ዛሬም የምናየው ክፍል በተወሰነ መልኩ ከባለፈው ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ በማር 2 ላይ ያየነው፣ ጥያቄ ከደቄ መዛሙርቱ ጋር በተያያዘ መልኩ ቀርቦ ነበር፡፡ ዛሬ የሚናየው ደግሞ አንድ እጁ ከሰለሌች ሰዉዬ መፈወስ ጋር ተያይዞ የተነሳ ነው፡፡
እስከ አሁን ድረስ ከኢሱስ አገልግሎት ውስጥ የምናየው፣ እርሱ ባገኘ አጋጣሚ የእግዚአብሄርን እውነት ለሰዎች ለማድረስና ሰዎችን ወደ መጀመሪያው የእግዚእብሄር ሓሳብ ለማምጣት ይናገር፣ይመክር፣ ያስተምር፣ ይጠይቅ እንደነበር ነው፡፡
በዚህ እውነተኛ ታርክ ውስጥ፡-
- ከሁኔታ የተነሳ አምልኮን ያላቋረጠ ወይም ደግሞ በመተማመን መልካም ቀንን ከእግዚአብሄር የሚጠባበቅ ሰውዬ በመቅደስ ተገኝቶ ነበር፡፡
o ምናልባትም ይህ ሰውዬ ከዚህ የባሰ እንዳይመጣበትም ፈርቶ በእምልኮው በርትቶ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ማናቸው የጤና መታወክ ከሓጢአት ጋር ይያያዝ ስለነበር፡፡
o ምናልባትም ደግሞ እግዚአብሄር ለምን እንደሚመለክ ገብቶት መጥቶ ይሆናል፡፡ስለተመቼንና ስላልተመቸን፣ ስላገኘንና ስለአጣን ሳይሆን፣ እግዚአብሄር በማንነቱ ልመለክና ልሰገድለት ይገባዋል፡፡
- ኢየሱስም ወደዚያው መቅደስ ሄዶ ነበር፡፡
- በሌላ መልኩ ደግሞ ሌሎች ምእመናንና መሪዎችም በዚያ ተገኝቶ ነበር፡፡
-
- በተጨማሪም ከእውነተኛ አምልኮ ሕይወት/ልምምድ ወጣ ያሉ፣ ግን የራሳችውና ወይም በሌሎች ሰዎች የተሰጣቸውን የቤት ሲራ ለመስራት የተነሳሱ ሰዎች በአከባቢው ነበሩ፡፡
o እነዚህም አምልኮን ካቃለሉት ከፈሪሳዊያን ወገን ስለእውነተኛ አምላክ እውቀቱ የሌላቸው ወይም የሮም ገዥዎች በእነርሱ ላይ የነገሱ የሄሮድስ ወጌኖች ነበሩ፡፡
- እግዚአብሄር በሰው ላይ ካልነገሰ፣ ሰው ወይም አጋንንት በእርሱ ላይ መንገሱ አይቀርም፡፡
- በሌላ ጎኑ ደግሞ የእግዚአብሄርን አምልኮ የሚያቃልል(ያልገባው) ከጣኦት አምላክዎች ጋር ሆኖ እውነትንና የእውነትን መልእክተኞች ያዋርዳል፡፡
- እንግድህ በምኩራብ የነበረው እጁ የሰለለች ሰው፣ እርዳታ በሚፈልግበት ጊዜና እግዚአብሄርም እርሱን ለመርዳት በተነሳበት ጊዜ፣ ሌሎች ደግሞ ወጥመድ መዘርጋት ጀመሩ፡፡
o እነርሱ ከእግዚእብሄር ሓሳብ ጋር የሚስማማ ማንነት አልነበራቸውም፡፡ በተጨማሪም፣ ለተቸገረው የሚያዝኑበት ማንነትም አልነበራቸውም፡፡
o ኢየሱስ የተቸገረውን ለመርዳት ሲነሳ፣ ለእነዚህም ተቃዋሚዎች እድልን ሰጣቸው፣ ነገሮችን አመዛዝነው የሚያዩበትን ጥያቄ ጠየቃቸውም፡፡
o ሰማያዊ የሆነውን ነገር ባይረዱ እንኳ በሰዉኛ አነጋገር፣ በሰንበት መደረግ ስላለበት ነገር ጠየቃቸው፡፡
o እነረሱ ግን እጅ መስጠት አልፈለጉም፡፡ ዝም አሉ፡፡
o የኢየሱስ ንግግር ምን ማለት እንደ ሆነም ገብቶአቸው፣ ግን ለመሸነፍ ስላልፈለጉ ቢቻ ዝም አሉ፡፡ ዝምታው የመስማማት፣ በራሳቸው ሁኔታ ንስሓ የመግባት ወይ ደግሞ የመሸነፍ አይነት አልነበረም፡፡ ነገር ግን የተቃውሞ፣ የአልሸነፍ ባይነት፣ የእልክኝነት አይነት ነበር፡፡
o ይህ ደግሞ ኢየሱስን አሳዘነው አስቆጣውም፡፡ ‹‹ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ ዙሪያውን እየተመለከተ በቍጣ አያቸው›› ይላል፡፡
o መቆጣት አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ሆኖም ግን ‹‹ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።›› (ኤፌ.4፡26-27)፡፡
o ጌታ በቁጣ ሲመለከት፣ ይህ የሚያስፈራ ነገር ነው፡፡ ራእይ 6፡ 14-17 ‹‹ሰማይም እንደ መጽሐፍ ተጠቅልሎ አለፈ፥ ተራራዎችና ደሴቶችም ሁሉ ከስፍራቸው ተወሰዱ። የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ፥ ተራራዎችንና ዓለቶችንም። በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን፤ ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፥ ማንስ ሊቆም ይችላል? አሉአቸው።››
o የእግዚአብሄር ታላቅነት የገባቸው ብዙ የእግዚአብሄር ሰዎች የለመኑት ልመና ‹‹ ባሪያህን አትቆጣ… › ‹‹ፍትህን ከእኔ አትመልስ››፣ ‹‹በምህረት አይኖች ተመልከተኝ››.. የሚል ነው፡፡ መዝ. 6፡1፤27፡9-10፤ 38፡1
o ለቤዛ ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሄር መንፈስ አታሳዝኑ››
- የሰው መስማማትና አለመስማማት የእግዚአብሄርን ሃሳብ አያስቀረውም፡፡ ስንስማማ ግን ተጠቃሚዎች እንሆናለን፡፡
o ኢየሱስ እጁ የሰለለችውን ሰውዬ፣ በሁሉ ፍት አስወጥቶ እጁን እንዲዘረጋ አዘዘው፣ እርሱም ህዝቡ ፍት (ተቃዋሚዎችም እያዩ ማለት ነው) በመታዘዝ ፈውሱን ተቀበለ፡፡
o የፈለገ ምንም ይበል ያድርግ እኛ ግን የእግዚአብሄር ሓሳብና ፈውስ በሕይወታችን ውስጥ እንዲገለጥ በእምነት እንታዘዘው፡፡
o ፈውሱንም ተቀበለ፡፡
- እግዚአብሄርን የማይፈሩ ሰዎች ሳያውቁት እርሱን ራሱ ከዙፋኑ ለማውረድ ይሞክራሉ፡፡
o ከፈርሳያን የሆኑ ሰዎችና የሄሮድስ ወገኖች ኢየሱስን ለመግደል ተስማሙ፡፡ ይህ ጥምር ቡድን ኢየሱስን እስከማሰቀል ድረስ ሠርቶአል በሃላም ዴቀ መዛሙርትን/ቤተ ክርስቲያንን በማሳደድ ቀጥለዋል፡፡

o በጤናማ ሁኔታ ቢሆን እንዚህ ቡድኖት በዚህ ላይ መተባበር አይችሉም ነበር፡፡ ‹‹ብርሃንና ጨለማ ሊተባበር አይችልም፡፡›› ይላልና ቃሉ፡፡ ነገር ግን ብርናቸው ስለጨለመ መኖንም ስለነበረበት የግድ ሆኖ ነበር፡፡

o በሌላ ክፍል ፣ጌታ ኢየሱስ ሲያስተምር ብርሃናችሁ ወደ ጨለማ እንዳይለወጥባችሁ ተጠንቀቁ ብሎአል፡፡

o እርሱን ለመግደል ብማከሩም እርሱ ግን ያለጊዜ መሞት የለፈበትምና ወደ ባህር ፈቀቅ አለ፡፡
አይቶ የማያዩ፣ ሰምተውም የማይሰሙ ሆነዋልና ኢሳ.6፡9-10፤42፡18-20 ማቴ 13፡ 13-16
ኢየሱስ ለዴቀ መዛሙርቱ፣
‹‹ስለዚህ እያዩ ስለማያዩ እየሰሙም ስለማይሰሙ ስለማያስተውሉም በምሳሌ እነግራቸዋለሁ።
መስማት ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትም ታያላችሁና አትመለከቱም።
በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል።
የእናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው።›› አላቸው
o ብዙ ሕዝብ ደግሞ ስለሥራው ሰምቶ ተከተሉት፡፡
 እርሱን ከብበውት የነበሩት እያዩ እንዳላዩ ሲሆኑ፣ ሌሎች ደግሞ አደራረጉን ሰምተው ከሩቅ ተሰብስበው መጡ፡፡
 ሰዎች ሊፈወሱ ፈልገው በኢየሱስ ላይ ይወድቁ ነበር፡፡ ኢየሱስ በዚያም ሊጎዳ ስላልፈለገ፣ በመርከብ ላይ ሆኖ ለማስተማር ወሰነ፡፡ አገልግሎቱን ከሚያደናቅፍ ከማናቸውም ነገር ራሱን ይጠብቅ ነበርና፡፡
o አጋንንት ምስክርነት አስመስለው የማጋለጥ ሥራ ሲሰሩ ኢየሱስ ከለከላቸው፡፡
 የእግዚአብሄር ልጅ እንዴሆነ በመናገር ምናልባት መስዋእት በመሆን ሰዎችን እንዳያድን መከልከል ይፈልጉ ነበር፡፡
 በሌላ መልኩ ደግሞ ተረጋግቶ የእግዚአብሄርን ሀሳብ እንዳያስተምር ተቃውም ያስነሱ ነበር፡፡
 ሰይጣን በሰላም በዚህ መቀመጣችንንም ከአምላካችንም ጋር ሄዴን መኖራችንን አይፈልግም፡፡
 ኣላመው፣ ዘላለማዊ ማስጨነቅ ነው፡፡ እግዚአብሄር ይገስፀው!
o ኢየሱስ ሌሎችም ከእርሱ ጋር እንዲያገለግሉ አሰታጥቆ (ስልጣንን ሰጥቶ) ላካቸው፡፡
 በቴክርስቲያን በተለይ ደግሞ መሪዎች፣ ራሳቸውን በእግዚብሄር ፈቃድ ውስጥ እየጠበቁ፣ ሌሎችም አገልግሎታቸውን/ራእይአቸውን እንዲቀበሉ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?