Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት
ማር 4፡ 26- 34
መግቢያ
ኢየሱስ በምድራችን ላይ ሰው ሆኖ መጥቶ ሲያስተምር በነበረበት ወቅት ሰዎች ግራ የተጋቡበት አንድ ትልቅ ነገር ብኖር የእግዚአብሄርን መንግስት መረዳት ነበረ፡፡ ብዙ ስብከት ተሰብኮ (በመጥመቁ ዮሃንስም ሆነ በኢየሱስ) ሰዎች ግን ልገባቸው አልቻለም፡፡ ሰዎች ብዙ ዓይነት ጥያቄዎች ነበራቸው ነገር ግን ኢየሱስ በሕይወታቸው ሊያደርግ የሚፈልገውን ነገርለማወቅ የቦዘኑ ነበሩ፡፡
ዛሬም ብሆን ይህ ነገር በሰዎች ልጆች ዘንድ በስፋት ያለ ይመስለኛል፡፡ ስለ የእግዚአብሄር መንግስት ያለን ግንዛቤ በጣም አናሳ ከመሆኑ የተነሳ፣ ሕይወታችንና ተግባራችን፣ መቀናጀት ያቅተዋል፡፡
በእግዚአብሄር መንግሥት ግዛት ውስጥ ስንገባ፣ የማቋርጥ፣ በማየት ያልሆነ፣ የአስተሳሰብ፣ የአኗኗር የአሠራር ለውጥ በእኛ ውስጥ ይከናወናል፡፡ ለውጡ የሚመጣው እኛ እናደርገዋልን ብለን ስለተጨነቅን ሳይሆን፣ በውስጣችን እያደገ፣ ቦታ እየወሰደና የእያፈራ ያለው ነገር ሳንፈልግ ይወርሰናል፡፡
ዛሬ ኢየሱስ የእግዚአብሄርን መንግስት መረዳት ያቃታቸውን ሰዎች ለመርዳት ያስተማረውን ነገር እናያለን፡፡ ለእኛም መንፈስ ቅዱስ እኔ ማስረዳት ከሚችለው በላይ እንዲያብራራልንና በሕይወታችን መከናውን ያለበት ነገር እንዲከናወን በጸሎቴ ነው፡፡
በሕብረተሰቡ መካከል ብዙ የተለያዩ አይነት ችግሮችና ጥያቄዎች ባሉበት ኢየሱስ የእግዚአብሄርን መንግስት ቅድሚያ የሚሰጠው ርእስ አድርጎ እያስተማረ ነው፡፡
ከዚህን ቀድም ማር. 4 ውስጥ ስለ ዘሪው ምሳሌ ነግሮአቸው ነበር፡፡ ከዚያም መብራት በመቅረዝ ላይ መቀመጥ እንዳለበት አስተማረ፡፡ ቀጥሎም ስለ ዘሪው
የእግዚአብሄር መንግስት ምሳሌዎች
- በምድር ዘርን የሚዘራ ሰው
o የሚበቅልን ንጹህ ዘር ይዘራል፡፡
o የራሱን ተግባር ብቻ ይፈጽምና መደበኛ ኑሮ ይቀጥላል.
 ለማብቀልም ሆነ ለማሳደግ ምንም ሊያደርግ የሚችለው የለም ግን የራሱን ተግባር ፈጽሞ ያርፋል፡፡
 ሌላው ቀርቶ እንዴት እድገቱ እንደሚሆን ራሱ አይታወቅም
o ዘሩ ግን ሕያው ስለሆነ፣ በተዘጋጀ መሬት ላይ ስለተዘራ፣ ተገብውን አገልግሎት (በዘሪው አቅም ያለውን) ስለሚያገኝ
 ዘሩ
• ይበቅላል
• ያድጋል
 ምድርቱ
• ቡቃያ
• ዛላ
• ሰብል ታፈራለች
o ፍሬው ይበስላል
o ማጭድ ይላካል (የመሰብሰብ ጊዜ ይመጣል)
- የሰናፍጭ ቅንጣት
o በምድር ካለው ዘር ሁሉ ታንሳለች
o በምድር ተዘራች
o ትወጣለች/ታድጋለች
 ከአተክልትም ሁሉ የምትበልጥ ትሆናለች
 ታላቅ ቅርንጫፍ ታደርጋለች
 ወፎች በጥላዋ መስፈር ይችላሉ
- ሌሎች ብዙ ምሳሌዎች
o ሰዎቹ ሊሰሙት በሚችሉበት መጠን
o ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም
ከዚህ ትምህት ምን እንማራለን?
1. የኢየሱስ ትልቁ አላማ የእግዚአብሄር መንግስትን መግለጥ ነበረ፡፡ ለዚያም ብሎ ነው ደጋግሞ ስለእርሱ በብዙ ምሳሌ የተናገረው፡፡ አገልግሎቱንም ስጀምር የእግዚአብሄር መንግስት ወደ እናንተ ቀርባለችና ንስሃ ግቡ በማለት ነበር (ማር. 1፡14-15፤ 4፡11-12፤ ማቴ.4፡23፤ 6፡13፣33)፡፡
- የእኛም የአማኞች ዓላማና አገልግሎት ሁሌ ከኢየሱስ የትኩረት አቅጫ ጋር ከሆነ
- በእኛ ሕይወትና አገልግሎት ውስጥ ለራሳችንም ሆነ ለሌሎች ሁሌም መግለጥ የምንፈልገው ነገር ምንድን ነው?
-
2. በተዘጋጅቶ ቃሉን በሚቀበል ሰው ሕይወት የቃሉ ሕያውነት ቀንና ሌሊት ባለማቋረጥ ይገለጣል፡፡
- በአንድ ሰው ሕይወት ላይ ቀንና ሊልት መፈራረቁ አይቀረ ነው፡፡ ቀን በብርሃን፣ በሙቀትና ለመሥራት በምቹነቱ ይታወቃል፡፡ ሌሊት ደግሞ በጨለማው፣ በጭጋጉ፣ በርጥበቱ፡፡ እነዚህ ሁሉ ለተዘራው ዘር ማደግ አስታቃጽዖ አላቸው፡፡
- ሰው/ዘሩን የሚዘራ/ሰባኪው ቀን ይነሳለል፣ ሌሊት ይተኛል ዘሩን የሚያሳድግ እግዚብሄር ግን ቀንና ሌሊት ከሥራው አይቦዝንም፡፡
-
3. ከተዘራው ዘር የሚፈለገው ፊሬ ነው፡፡
- መዘራት፣ መብቀል፣ ዛላ ማውጣት የእድገት ደረጃዎች ስለሆኑ ያስፈልጋሉ፡፡ ሆኖም ግን ከእነዚህ አንዱ ጋ ደርሶ ብቻ መቆም በቂ አይደለም፡፡ ማፍራት ይፈለጋል፡፡
- የእግዚአብሄር መንግስት የፍጹም ለውጥ ህዴት ያለበት ነው፡፡
- በውጭ የሚታዩ ለውጦች /ድራማዎች አይደሉም፡፡ ግን ውስጣዊና የማንነት ጋር የሚገናኝ ለውጥ ያለበት ነው፡፡
- ፍፌ የሌለው ቅርንጫፍ እንደሚቆረጥ እየሱሰ መናገሩን ከባለፈው ትምህርታችን እናስታውሳለን፡፡
- አንድ ሰው ወደ ቤተ/ኪያን ስመጣ ለእድገቱ የሚጠቅም ነገርን ለማግነት ይመጣል፡፡ሆኖም ግን ዕድገቱ የሚካሄደው በሰውየው የግል ሕይወት ውስጥ በሚሆን ነገር ነው፡፡ በሰው አፕሩቫል ወይም በሰው ሥራ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ግን በውስጣችን እንዲሰራ ቃሉን በመቀበልና በማድረግ ከተለማመድነድ ራሱ እግዚአብሄር በሚያደርገው ሥራ ፍሬ እስከማፍራት እንደርሳለን፡፡
4. የሰነፍጭ ቅንጣት በምድር ካሉት ዘሮች ታንሳለች
- በምድር ያሉ ዘሮች የሓጥአት ዘር፣ የክፋት ዘር፣ የዝሙት ዘር፣ የጥላቻ ዘር፣ የራስ ወዳድነት ዘር፣ የትዕብት ዘር፣ የሞት ዘር ናቸው፡፡
- እነዚህ ሁሉ ዘሮች ባለማቋረጥ በሰዎች ላይ በብዛት ሁልጊዜ ይዘራሉ፡፡
- የእግዚአብሄር መንግስጥ ዘር ግን በመጠኑና በብዛቱ ከእነዚህ ሁሉ ትንሽ ሆኖ ይዘራል፡፡ ስዘራብም ጥቅት የተዘጋጄ መሬትን ያገኛል፡፡ ሌላው መንገድ ዳር፣ ጭንጫ፣ እሾአማ መሬት ስለሚሆኑበት፡፡
- በገኘው መሬት ላይ ግን ስበቅል ከተዘሩት ዘሮች ሁሉ በልጦ በመገለጥ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ቃል በእኛ ውስጥ ተዘርቶ ማደግ ሲጀምር፣ ቀድሞ ተዘርቶ የነበረውን ዘር ሁሉ ሳፕረስ አድርጎ ለመንግሥቱ የሚሆነውን ለውጥ በእኛ ውስጥ ያመጣል፡፡›
5. ለደቀ መዛሙርት የተለየ የትምህርት ጊዜ አለ፡፡ ይህም ማለት ከሕዝብ በተለየ ደቀ መዛሙርት ከኢየሱስ የሚሰሙበት ጊዜ ያስፈልጋቸዋል፡፡ መማርና ማስተማር ሃላፊነት አለበት፡፡ ስለዚህ ሌሎች ስበተኑ ከእርሱ ጋር ለሚቀሩት ክፍል ኢየሱስ ይፈታላቸው ነበር፡፡
6. መጨረሻ ላይ ፊሬ ወደ ጎተራ ሊገባ አጨዳ ይከተላል፡፡ የአጨዳ ጊዜ አለ፣ የመሰብሰብ ጊዜ ቀርቶልናል፡፡ ያኔ ገለባ ከመሆንና ከመቅረት የያድን በእኛ የሚገነው ፍሬ ነው፡፡
እንግዲህ እኛ ዛሬ ራሳችንን መጠየቅ ያለብን፣
- ህይወቴ ለዘሩ የተዘጋጄ መሬት ነው?
- የእግዚአብሄር ቃል በእኔ ሕይወት ወስጥ ምን ደረጃ ላይ ደርሶአል?
- የእግዚአብሄር መንግስት ሐሳብ በእኔ ውስጥ ጎልቶ መታየትችሎአል፣ ይችላል ወይም እንዲችል እየፈቀድሁለት ነው?

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?