Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት
ማር 4፡35-41
‹‹በሰላም እተኛለሁ
አንቀላፋለሁ፣
እግዚአብሄር ሆኞቻል መተማመኛ
ከጥፋት ሁሉ መዳኛ፡፡›› ዘማሩ ተስፋየ ገቢሶ

ባለፈው ወር ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት የመማር ዓላማ ይዘን ከእግዚአብሄርን ቃል አብረን ስንመለከት፣ ኢየሱስ እንዴት አድርጎ ስለ እግዚአብሄር መንግስት ሲያስተምር እንደ ነበረ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግሥት ዘር በምድር ከሚዘሩት ሌሎች ዘሮች አንጻር ሲትታይ አናሳ እንደ ሆነችና በሃላም ከሌሎች በልጣ እንደሚታድግ በምሳሌ አስተምሮ ነበር፡፡
በምድር ላይ የሚዘሩ ብዙ አይነት የሓጢአትና የበደል ዘሮች ሰዎችን ከእግዚአብሄር መንግስት ለመለየት የሚደረጉ ሲሆን፣ አብዛኛው ሰዎች ጆሮ በማይሰጥና እጅግ ጥቅቶች በጥቅቱ የሚትዘራው የእግዚአብሄር መንግስት ቃል ግን በሚታመጣው ተጽእኖ አስገራሚ ለውጥን የሚታመጣ እንደ ሆነችነበር፡፡
በተጨማሪም በሌሎች ዓይነት ምሳሌዎች ወደ ሰሚዎች ቀርባ ያለችውን የእግዚአብሄር መንግስት ያስረዳ ነበር፡፡
ኢየሱስ በሰዎች በቀላሉ ሊገባ የማይችለውን ርዕስ ሲያስረዳ በምሳሌ ብቻ ነበር የተጠቀመው፡፡ ምሳሌዎቹ ደግሞ ለሰሚዎች ግልጽና ትርጉም የሚሰጥ ከመሆናቸውም ባሻገር በቤታቸውና በሥራ ቦታቸው፣ በጓሮአቸው ከሚመለከቱት ጋር አያይዞ ነበር ያስተማረው፡፡
ይህም ማለት ኢየሱስ ሰዎች በሁሉም ቦታና ጊዜ ስለእግዚአብሄር መንግስት መረዳቱ እንዲኖራቸው እንደሚፈልግ ያስረዳል፡፡ ይህም ማለት ከእግዚብሄር ጋር ያለን ነገርና ሕብረት በአምልኮ ቦታዎችና ጊዜያት ብቻ የተገደቡ እንዳይሆኑ ነው፡፡
የእግዚአብሄር መንግስት እጅግ አስፈላጊና ወሳኝ መሆኑን ለማሳየት የስብከቱ መጀመሪያ በማድረግ፣ የምህርቱ ብዙ ጊዜ እንዲወስድ ያደረገ፣ ባስተማረው ፀሎት ውስጥ እንብርት ያደረገ፣ ከትንሳኤው በኃላም ቀጥሎ ያስተማረው ነገር ነበር፡፡
ይህንን በግልጽ በገሃድ ያስተማረውን ትምህርት በደንብ ጠንቅቀው እንዲያውቁት ለደቀመዛሙርቱ ደግሞ ለብቻቸው አስረዳቸው፡፡ ሁላችንም ለብቻችን፣ በተለይ ደግሞ አገልጋዮች፣ ጊዜ የማንወስድ ከሆነ፣ ከፍለፊታችን ለላው አገልግሎት ብቁ መሆን አንችልም፡፡ በግርግር ውስጥ ከሌሎች ሰዎች ጋር ሆነን የምንሰማውን ለሌላው ሰው እደሆነ ገምተን የማለፍ እደላችን የሰፋ ነው፡፡ ሆኖም ግን በግላችን ለብቻችን ጌታ ሲያናግረን ወደ ሌሎች ማስታከክ እንችልም፡፡ በማናቸውም የሕይወት ደረጃ ቢሆን የማይለወጠው የእግዚብሄር መንግስት ቃል አስፈላጊያችን እንደ ሆነ ከእርሱ ተምረናል፡፡
በዛሬው ክፍል ደግሞ ካስተማረ በሃላ የሆነውን ነገር እናያለን፡፡
‹‹ወደ ማዶ እንሻገር፡፡››
- ከገሊላ ባህር ማዶ ነበር፡፡ አገልግሎት አንድ ቦታ አያበቃም፡፡ የኢየሱስ አገልግሎት ድንበርም መስፋት ነበረበት፡፡ ከማዶ ያሉትም ይፈለጋሉ፡፡ ወደ ማዶ ለመሻገር የተነሳው በመሸ ጊዜ ነበር፡፡ ሌሎች ወደእየበታቸው ሲሄዱ፣ እርሱና ከእርሱ ጋር ያሉት ግን ለሚቀጥለው አገልግሎት ጉዞ ጀመሩ፡፡
- ይህ አይነት ሕይወት አድካሚ እነደ ነበር መገመት ይከብዳል ብየ አላስብም፣ ትኩረት ሰጥተን ብናየው፡፡ ቀኑን ሙሉ በጠራራ ጸሓይ ውስጥ ሆኖ ሲያስተምር ቆይቶ፣ ሲመሽ ሌላ የአገልግሎት ጉዞ መጀመር፡፡ እንደዛሬው የድምጽ ማጉያ መሳሪያ እንደሌለ ማወቁ ቢቻ ነገሩን የበለጠ ያስረዳናል፡፡
- ፍጹም ሰው ስለነበር ደክሞታል፡፡ ስለዚህ ጉዞው ሲጀመር በመርከቡ ውስጥ ተኝቶ ነበር፡፡
- ብርቱ ዓውሎ ነፋስ ደግሞ ተነሳባቸው፡፡ ከዓውሎ ነፋሱ የተነሳ ደግሞ ማዕበል ተነሳ፡፡ ከማዕበሉ የተነሳ ውሃ ወደ መርከብ መግባት ጀመረ፣ መርከቡም መስጠም ጀመረ፡፡ ሰዎቹም ለሕይወታቻው መፍራት ጀመሩ፡፡ እንደዚአህ አይነቱ ንፋስ ርህራኤ የለውም፣ ሰውንም አይመርጥም፡፡ ምናልባትም ኢየሱስ ሁለተኛ የዚህን ዓይነቱን(የቀኑን) ሥራ እንዳይሰራ ታስቦም ሊሆን ይችላል፡፡
- ኢየሱስ ግን በእምነት በሰላም ተኝቶ ነበር፡፡
o ‹‹የሚሰማኝ በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ስጋት ያርፋል፡፡››
o ‹‹ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።›› መዝ.46፡10
o ‹‹ትእዛዜን ብትሰማ ኖሮ፥ ሰላምህ እንደ ወንዝ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር ›› (ኢሳ.48፡18)
o
- ስለዚህም ለደቀ መዛሙርቱ ሲመልስ ‹‹ እንዲህ የምትፈሩ ስለ ምን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም? ›› (ቁ40) ብሎ ነበር፡፡
-
ደቀ መዝሙር የወሰዱትን እርምጃ ስንመለከት
- ቀሰቀሡት - የራሳቸውን ጥረት ከጨረሱ በሃላ፣ በነፋሱ ሃይል ተስፋ ከቆረጡ በሃላ ቀሰቀሱት፡፡
o አንደ ማናችንም፣ ነገሮችን በራሳቸው ጥረት ብቻ ለመቆጣጠር ሞከሩ፡፡ ያንን ሲያደርጉ ደግሞ ምናልባት ከልምዳቸውና ከቁጥራቸው፣ ከአቅማቸውም ጋር አመዛዝነው በማየት ‹‹ይንንስ እኔው እችላለሁ›› በማለት ሳይሆን አይቀርም፡፡
o በእምነትም አልነበረም፡፡ ኢየሱስ ግን በሁሉም

- ኢየሱስን ግድየለሽ አስመስለውታል ‹‹መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን?>>ፍ
- ስለማንነቱ ጥያቄ ነበራቸው ‹‹ይህ ማን ነው?››
o ‹‹መምህር›› የሚለውን ታይትል ተጠቅመ ዋል በዚህ ክፍል፡፡
o ከማስተማር ባሻገር ጌታ ሊያደርግ የሚችለውን ነገር የረሱ ይመስላል፡፡
እኛ ጌታን እንዴት እናውቀዋለን?

በዚህ ክፍል ከኢየሱስ የምንማረው
- ነገሮችን በእምነት ማድረግ በማናቸውም ቦታና ሁኔታ ውስጥ ያስፈልጋል፡፡
- እምነታችን ደግሞ በጌታ ቃል ላይ የተመረኮዜ መሆን አለበት፡፡ ‹‹እንሻገር›› ያለው ሳይሻገርና ሳያሻግር አይተውም፡፡
- ፍጥረት በሙሉ፣ ግውዛንና መናፍስትን ጨመርሮ ይገዙለታል፡፡ ኢየሱስ ገሰፀው፡፡ኢሱስ አጋንንትንም ስገስጽ በዚህ መልኩ ነበርና (1፡25) ምናልባት ከነፋሱና በስተጀርባ የሚሰረውን ሃይል መገሰጹ ሊሆን ይችላል፡፡
- ሁኔታዎች ሁልጊዜ እኛ እንደምንገምተው ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ መንፈሳዊውን ተግዳሮት በእምነትና ከጌታ በምናገኘው ሥልጣን እንጂ በልምምድና በእኛ ጥረት ብቻ አንፈታውም፡፡
- ኢየሱስ በክርስቲያኖች ሕይወትና በቤተክርስቲያን በሚያደርገው የሠላም መሥጠትና ሌሎች ሥራዎች ብዙ ቅርብና ሩቅ ያሉ ሁሉ ይጠቀማሉ፡፡ ኢየሱስ የነበረበትን ጀልባ ስከተሉ የነበሩ ሰዎች/መርከቦች ሠላም አግኝተዋል ግን ከየት የመጣ መሆኑን ስለማስተዋላቸው የምንናውቀው ምንም ነገር የለም፡፡

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?