Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት
ማር.5፡ 1-20
መግቢያ
በበለፈው ሶስት ሳምንት፣ በዚህ ከነበራችሁ ሰዎች ጋር ማር 4 መጨረሻናን ክፍል ስናይ ነበር፡፡ ኢየሱስ ደቄ መዛሙርቱን ተስፋ አስቆርጦ የነበረውን ወጀብ ጸጥ እንዳሰኘላቸው አይተናል፡፡ ያ ፈታኝ አስቸጋሪው ንፋስና ማዕበል ሊከለክል ወይም ሊገድል የመጣ አንደነበር ግልጽ ነበር፡፡ ኢየሱስ ግን በሥልጣን ገስጾ ሰላምን ከእርሱ ጋር ለነበሩትና በአካባቢአቸው ላሉት ሰጠ፡፡

ከልካይ ንፋስና ወጀብም ቢሆነር ኢየሱስ አልፎ ለሚፈልጉት/ለተጎዱት መጣ፡፡

ዛሬ የምንናየውን ክፍል ደግሞ በሌላ መንገድ በ2014 መጨረሻ ላይ አይተነው ነበር፡፡ ኢሱስን ማንንነት ሲናጠና-- ስልጣኑንና ተልእኮውን ሲናይ፡፡

ፈተናውን አልፈው ወደ ማዶ ሲሻገሩ ደግሞ በክፉ መናስት የተያዙ ሰዎችን አገኘ፡ ማቴ.8 ላይ ሁለት እንደነበሩ ይናገራል፡፡ ማርቆስ ደግሞ እጅግ በጣም የከፋበትን ያንዱን ታሪክ ትኩረት ሰጥቶት ይተርካል፡፡ ይህ ሰው በለግዮን የተያዘ ነበር--6000 ጭርፎረች፡፡
ሰዉየው እንዴትና ለምን በመናፈስቱ እንደተያዘ አናውቀውም፡፡ አንድ ነገር በድፈርት መናገር የምንችለው፣ ከእግዚአብሄር ጋር መኖር በህይወቱ፣ በቤቱና በአከባቢው አለመኖሩን ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች በክፉ መንፈስ የሚገኘውን ጊዜያዊ ሀብት፣ ዝና፣ ሃይል ለማግኘት መናፍስቱን በእነርሱ ውስጥ እንዲኖሩ እንደሚፈቅዱ ከብዙ ነገር አንሰማለን፣ እናነባለንም፡፡
ሌሎች ደግሞ ለእነርሱ ግልጽ ባልሆነ መንገድ፣ ከቤተሰብ ጋር በተያያዘ፣ ከሓጢያት ጋር በተያያዘ፣… ጠላት ያገኛቸዋል፡፡

ሰዎች በምንም ምክኒያት የርኩስ መንፈስ ተገዥና ሰለባ ቢሆኑም፣ ኢየሱስ ግን ይራራላቸዋል፡፡ ዛሬም ይራራልናል፡፡
ኢየሱስ ለዚህ ሰው ምህረት አደረገለት፡፡

በዚህ ክፍል የምናየው ሰው፣
- በእርኩስ መንፈስ የተያዜ ነበር፡፡
- ከህያዋን መካከል ወጥቶ ሙታን መካከል ይመላለስ ነበር፡፡
- ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ሕይወት ነበረው፡፡ እርሱን በሕያዋን ሰዎች መካከል ለማስቀረትና ለማገልገል የሚያስል አቅም የነበረው ሰው አልነበረም፡፡ ሰንሰለቶችና የብረት ማሰሪያዎችም አልቻሉትም ነበር፡፡
- ቀኖቹና ሌሊቶቹ ጩሄትና በጭንቀት የተሞሉ ነበረ-- እረፍት የራቀው ሰው ነበር ማለት ነው፡፡ እርኩስ መንፈስ ሠላምና እረፍት አይሰጥም፡፡
- ሰውነቱን የሚጎዳ ሰው ነበረ፡፡ ለገዛ አካሉ ርህራሄ አልነበረውም፡፡ በድንጋይ ማለትም ሕይወት/ርህራሄ/ ስመት በሌለው ነገር አካሉን እንዲጎዳ ያደርገው ነበር ክፉ መንፈሱ፡፡
- ይህ እርኩስ መንፈስ ያለበት ሰው መጀመሪያ ወደ ኢየሱስ ሮጠ፣ ከዚያም ሰገደለት፡፡ ምናልባት ማምለጥ ሲለማይችል ይሆናል፡፡ የጌቶች ጌታ ሲገለጥ ለእርሱ ጉልበት ሁሉ እንደሚንበረከክ የእግዚአብሄር ቃል ይናገራል፡፡

ሌላው፡-
- የኢየሱስ በዚያ ቦታ መገኘት ለርኩሳን መናፊስቱ ትልቅ ጭንቀት ነበረ፡፡ ስለዚህም ኢየሱስ ሰውየውን ለቆት እንዲወጣ ሲገስጽ ልመና ጀመረ፡፡ አታሰቃየኝ! በማለት፡፡
- አጋንንት ስለኢየሱስ ማንነት በመመስከር ሊመናውን አቀረበ፡፡ በወቅቱ ይህ የኢየሱስ ለሰውች በደንብ አልተገለጠም ነበር፡፡ ማመኑም ያስቸግራቸው ነበር፡፡
- አጋንንትም ቢሆን ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ አንደሆነ ያውቃሉ ያኑማል፣ ግን ደግሞ የእምነትን ፍሬ- በንስሓ አያፈሩምና በዚህ እምነታቸው አይድኑበትም፡፡
- የስዎች እስራትና ሰንሰለት ያልቻለውን በቃልና በመገኘት ተቆጣጠረው ኢየሱስ
-
እንግዲህ በዚህ ቦታ የምናያቸው ሶስቱ ሃይላት የአጋንንት፣ የማህበረሰብና የእግዚአብሄር ሃይል ናቸው፡፡

ክፉ መናፍስቱ ግን ከሰውየው ስወጡ፣ በአከባቢው ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ቀውስን አመጡ፡፡ ወደ 2000 የሚጠጉ አሳማዎች ወደ ባህር ሰጠሙ፡፡
ይህ ደግሞ በአከባቢው ሰዎች ላይ ትልቅ ፍርሃት እንዲወድቅ ከማድረጉ የተነሳ፣ ኢየሱስን ‹‹ሂድልን›› አሉት፡፡
የሀገሩ ሰዎች ኢየሱስን ከከተማቸው (ልብ ብናደርግ፣ ሰፈራችንን፣ መንደራችንን አላሉም፣ ሀገራችንን፣ ግዛታችንን) እንዲሄድላቸው ለመኑት፡፡ ቁ 17
እውነታው
- ሰዎቹ የአኗኗር ዜይበያቸውን ቻለንጅ የሚያደርግ ሰው በሀገራቸው ማየት አስፈርቶአቸዋል፡፡ የኢየሱስ በአከባቢው መቆየት የበለጠ ክሳራ ሊያመጣባቸው እንደሚችል የገመቱ ይመስላሉ፡፡
ለምን? ለሌውጥ የተዘጋጁ አልነበሩም፡፡ ኢየሱስ በሕይወታቸው ከሚያደርገው ነገር የበለጠ፣ እነርሱ የያዙት ነገር በልጦባቸው ነበር፡፡
ጥ› እኛስ እንዲህ ሆነን አናውቀምን? ወደ እርሱ መመለስ ይሻለናል፡፡
- የሰው ዋጋና የዕሪያ ዋጋ ተመሳስሎባቸዋል፡
- ለለውጥ ፈጽሞ የተዘጋጁ ስላልነበሩ፣ የተደረገው ነገር ለምን ነው? ምን ማለትስ ነው?… ብሎ ለመጠየቅ አልደፈሩም፡፡
- በአጠቃላይ ሰዎች ለምን መልካሙን ነገር ከዚያም አልፎ እግዚአብሄርንም ከመንገዳቸው ለማስወጣት ይፈልጋሉ?
ይህ አየነቱ ጠባይ በሰውች ዘንድ ከውድቀት ጀምሮ እየተስፋፋ የሄደ ነገር ነው፡፡
• አዳሚና ሄዋን መሸሽንና መደበቅን የኃጢአት መፍትሄ አድርገው ወሰዱ፡፡
• እስራኤላውያን በግላቸው ከእግዚአብሄር መስማት አልፈለጉም-- እንሞታለን ብለው ስለፈሩ ዘዳግ.5፡25 አሁን እንግዲህ ይህች ታላቂቱ እሳት ታቃጥለናለችና ለምን እንሞታለን? እኛ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ድምፅ ደግሞ ብንሰማ እንሞታለን።
• ኢዮብ 21፡14 እግዚአብሔርንም። ከእኛ ዘንድ ራቅ መንገድህን እናውቅ ዘንድ አንወድድም።
• እናመልከውስ ዘንድ ሁሉን የሚችል አምላክ ማን ነው? ወይስ ወደ እርሱ ብንጸልይ ምን ይጠቅመናል? ይላሉ።
በእርግጥ ሓጢአተኘንታቸውን ማወቃቸው ጥሩ ነው፣ ግን ደግሞሞ ድብብቆች እስከመቼ ይሆናል? ያውም ከዘላለማዊው እግዚአብሄር? ወደ እግዚአብሄር መመለስ ወይስ እርሱን ማባረር ወይም ከእርሱ ለመሸሽ መሞከር ይሻላል?

የኢየሱስ ምላሽ
- ጌታ ኢየሱስ ለታሰሩት ይራራል--- ሊደርስበት ያለው ነገር ከመስራት አላገደውም፡፡
- እርሱ እንደ አየም አይፈርድም--- እድልን ይሰጣል፤ መንገድን ይከፍታል፡፡
o እኛ በብዙ ቁጥር በምንታለልበት ጊዜ እግዚአብሄር ግን በጥቂቱ (አንድም ቢሆን) የሚያመጣበትን ታላቅ ለውጥ ይመለከታል፡፡
- እግዚአብሄር ያደረገልህን ምህረት ተናገር
o ቤተሰዎቱቹ --ሙሉ ታሪኩን ያውቃሉ፤ ሊረዱትም ብዙ ሞክረው ነበር፤፤ መርዳት የሚችሉትም አስረው ቤት በማቆየት ነበር--እርሱንም አልቻሉም፡፡ በገመድ፣ በሰንሰለት በብረትም አስረውት ነበር፡፡ ሆኖም ግን ከአቅማቸው በላይ በሆነው ሃይል ሰውየው ከእጃቸው ሊያመልጥ፣ ራሱንና ሌሎችንም ሊጎዳ በሚችልበት ሁኔታ ለመኖር ሆነ፡፡
o ቤተሰቤ ምናልባት ኃጢአቱ እጂግ ስለበዛ፣ ለዚህ ክፉ ነገር ተጋለጠ ሳይሉት አልቀሩም፡፡ ከእጃቸውም ካመለጠ በኃላ እንደሞተ አድርገው መቁጠራቸው አልቀረም፡፡
o ኢየሱስ ግን ሰውየውን ካዳነው በሃላ፣ እግዚአብሄር ምህረቱ እንደማያልቅ፣ እንደገናም ምህረት እንደሚያደርግ እንዲያውቁ፣ ለእነርሱም አሁን እድል እንዳለ እንዲያውቁ፣ ወደ እርሱም እንዲመለሱ እንዲናገር ፈለገ፡፡
o የዳነው ሰው ግን ከቤተሰዎቹ አልፎ ለመላ ሀገሩ ሰዎች የእግዚአብሄርን ምህረት ሰበከ፡፡

ከክፍሉ የምንማረው
- የእርኩሳን መናፍስት መኖርና በሰዎች ላይ አሉታዊ ተፅኖ ማምጣት ትክክል ነው፡፡
o ከሰይጣን ጋር የወደቁ መላእክት ናቸው
o በተያዙበት አጋጣሚ ሁሉ ሰዎችን ሲጠቅሙ ሳይሆን ስያስጨንቁና ሲያሰቃዩ ነው
o ቢሆንም ግን ኢየሱስን ይፈሩትና ይታዘዙለት ነበር --- ኢየሱስ በሁሉም ላይ ጌታ ስለሆነ
o እኛ ደግሞ ወደ ኢየሱስ ተጠግተን ስንኖር ራሳችንን ከክፋ መናፍስት እንጠብቃለን፣ ምክንያቱም እርሱ በሚኖርበት እነርሱ መቀመጥ አይችሉምና
1ዮሃ.4፡4 ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።

ታሪክን የሚለውጠው ኢየሱስ፣ በአጋንንት ሃይል ይሰቃይ የነበረውን፣ በበተሰዎቹና በሃገረው ሰዎች ተስፋ የተቆረጠለትን አድኖ የድህነትና የእግዚአብሄር ምህረት ሰባኪ አደረገው፡፡
እኛ ያልቻልነውና የለቀቅነው ነገር ይኖር ይሆን?
ስለራሳችንስ ቢሆን ተስፋ ቆርጠንበት የተውነው ነገር ይሆርን?
ወይ ደግሞ ሓጢአታችንን በራሳችን ላይ አይተን ወደ እግዚአብሄር ከመመለስ ይልቅ ተራርቆ መቀመጥን የመረጥንስ እንኖር ይሆን?
አይዞአችሁ፣ የሚያየወው ኢየሱስ በመንገዱ ላይ ያለውን ተግዳሮቶች ሁሉ እየሰበረ ይመጣል፡፡ እርሱ እንደሌሎች መንገድ ቀይሮ አያልፈንም፡፡ ወደ እኛው መጥቶ በተለወጠ ታርክ ታአምራቱን የሚናገሩ ሰዎች ያደርገናል፡፡ እርሱ ያያል፡፡

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?