Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት
ማር 6፡ 45-56 ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ማመር

ማር 6፡ 45-56
45 ወዲያውም ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ ደቀ መዛሙርቱ በታንኳ ገብተው ወደ ማዶ ወደ ቤተ ሳይዳ እንዲቀድሙት ግድ አላቸው።

46 ካሰናበታቸውም በኋላ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።

47 በመሸም ጊዜ ታንኳይቱ በባሕር መካከል ሳለች እርሱ ብቻውን በምድር ላይ ነበረ።

48 ነፋስ ወደ ፊታቸው ነበረና እየቀዘፉ ሲጨነቁ አይቶ፥ ከሌሊቱ በአራተኛው ክፍል በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣ፤ ሊያልፋቸውም ይወድ ነበር።

49 እነርሱ ግን በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ ምትሀት መሰላቸውና ጮኹ፥

50 ሁሉ አይተውታልና፥ ታወኩም። ወዲያውም ተናገራቸውና። አይዞአችሁ፤ እኔ ነኝ፥ አትፍሩ አላቸው።

51 ወደ እነርሱም ወደ ታንኳይቱ ገባ፥ ነፋሱም ተወ፤ በራሳቸውም ያለ መጠን እጅግ ተገረሙ፤

52 ስለ እንጀራው አላስተዋሉምና፤ ነገር ግን ልባቸው ደንዝዞ ነበር።

53 ተሻግረውም ወደ ምድር ወደ ጌንሴሬጥ ደረሱ ታንኳይቱንም አስጠጉ።

54 ከታንኳይቱም ሲወጡ ወዲያው አውቀውት

55 በዚያች አገር ሁሉ ዙሪያ ሮጡና እርሱ እንዳለ ወደ ሰሙበት ስፍራ ሕመምተኞችን በአልጋ ላይ ያመጡ ጀመር።

56 በገባበትም ስፍራ ሁሉ፥ መንደርም ከተማም ገጠርም ቢሆን፥ በገበያ ድውዮችን ያኖሩ ነበር፤ የልብሱንም ጫፍ እንኳ ሊዳስሱ ይለምኑት ነበር የዳሰሱትም ሁሉ ዳኑ።
ባለፈው ሦስት ሳምንት ወንጌላዊ ማርቆስ የጻፈፋን ታርክ መነሻ አድርጌን ከጌታችን ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ሲንማር እርሱ ከሠራቸውና ካስተማራቸውና ከኖረው ሕይወት ብዙ ስንማር ነበር፡፡ በተለይ የዛሬ ሶስት ሳምንት
- ኢየሱስ ለሰው አሳቢ መሆኑን፣
- የሰው ችግር/ድካም የሚገባው መሆኑን፣
- የመጣበትን ዓላማ ለመፈጸም የሚያስከፍለውን ዋጋ ሁሉ እየከፈለ ማድረጉን
- ደካሞችና የላቸውም የሚባሉት ሰዎች የየዙትን ጥቅት ነገር ለብዙ ማድረግ እንደሚችል አይተን ነበር፡፡

በዚያ ታርክ ውስጥ ደቀ መዛሙርት ከአገልግሎት መልስ እንዲያርፉ ወደ ምድረበዳ እንደመራቸው፣ እነርሱን ተከትለው ለመጡት ብዙ ሕዝብም ርህራሔ እንዳሳያቸውና ብዙ ሰዓታት ወስዶ ብዙ ነገር እንዳስተማራቸው፣ በተራቡ ጊዜም ረሱ አውቆ ሊመግባቸው እንደፈለገና አንዳደረገውም (እንዳበላቸውም) አይተን ነበር፡፡

ጌታ የተራቡትን ያበላል፡፡ የታመሙትን ይፈውሳል፡፡ ግራ የገባቸውንም የእግዚአብሄር መንግስት ነገር በማስተማር ወደ መልካም መንገድ ይመራቸዋል፡፡

በዚያ አከባቢ በተገኘው 5 እንጀራና 2 ዓሳ ለአምስት ሺህ ሰዎች መግቦአል፡፡

ሰዎችን ካስተማረ፣ ካበላቸውም በሃላ ፣ እነርሱን እስኪያሰናብታቸው ድረስ ደቄ-መዛሙርቱ ቀድመው ባህር ተሻግረው እንዲሄዱ ግድ አላቸው፡፡

- ለምን ግድ እንዳላቸው ግልጽ አይደለም፡፡
--ምናልባት 1. እነርሱም በሕዝቡ ጋር በመቆት የተደረውን ተዓምር ሰለብረት ሊያደርጉ ፈልገው ሊሆን ይችላል፡፡ ምክኒያቱም በዮሓንስ (6፡14-15) ምስክርነት መሠረት ሰዎቹ እንጄራ ስለጠገቡ ሊያነግሱት አስበው ነበር፡፡

** " ከዚህ የተነሣ ሰዎቹ ኢየሱስ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ።
ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው አሉ።
በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ያነግሡት ዘንድ ሊመጡና ሊነጥቁት
እንዳላቸው አውቆ ደግሞ ወደ ተራራ ብቻውን ፈቀቅ አለ።"
** ከዚህን በፊት አይተነው እንደነበርም የኢየሱስ ዝና እስከቤተ-መንግስት ደርሶ ተወርቶ ነበርና ሰዎች ምናልባት አስበውበት መጥተው ልሆን ይችላል፡፡ ጌታ ሲመግባቸው ደግሞ ላሰቡት ነገር ማረጋገጫ ያገኛሉ፡፡

--ምናለባትም፣ 2. ጊዜው እየመሸ ሲለሆነ፣ የአየሩን ሁኔታ ፈርተው ላለመሄድ ፈልገው ሊሆን ይችላል፡፡

ለማናቸውም ምክንያት ቢሆንም፣ ኢየሱስን ትተው ሊሄዱ ባይፈልጉትም እርሱ ግን የግድ እንዲሄዱ አበክሮ አዘዛቸው፡፡

እነርሱ ከሄዱ በሃላ ሕዝቡን አሰናበታቸው፡፡ ያንን ካደረገም በሃላ ብቻው ሊጸልይ ወደ ተራረ ወጣ፡፡
** ለብቻ የመጸለይ ሕይወት በሕብረት ከመጸለይ እኩል አስፈላጊ ነው፡፡ አብዛኛው ሰው የሚጸልየው ወደ ቤቴ/ያን ሲመጣ፣ ወይም በወገኖች ህብረት መካከል ብቻ ሲሆን ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው፣ እግዚብሄርን ማናገርና በግልም ከእርሱ የመስማት ልምምድ የለውም ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ ግን ምንም እንኳ የእለት ተእለት ኑሮው ከእግዚአብሄር ቃል ትምህርት፣ ከመለኮታዊ ሃይል ሥራዎች ጋር የተገናኘ ቢሆንም አብዛኛውን ሌሊት ግን ወደ ተራራ ወጥቶ በመጸለይ /ከአባቱ ጋር ህብረት በማድረግ ያሳልፍ ነበር፡፡ በጸ

ጥያቄዎች፡1. ኢየሱስ እንዴት አልደከመውም? ጸሎት ለኢየሱስ እንዴ ሥራ አይመስለኝም፣ ነገር ግን ሕብረት ማድረግ እንጂ፡፡ ብዙ ሲገዋዝ፣ ሲናገር፣ ሲሠራ ውሎ ሌሊት ከአባቱ ጋር ለመነጋገር ይሄድ ነበር፡፡ በማያውቀውና በትክክል ባልተቀበለው ሕዝብ መካከል ሲያገለግል ውሎ፣ ለዕረፍቱ ደግሞ ወደሚያውቀውና ወደሚረዳው፣ ወደሚወደውም፣ ወደ ላከውም አባቱ ይሄድ ነበር፡፡

ብዙ ጊዜ እንደምናስበው ጸሎጽ ለገባው ሰው አድካሚ ሥራ ሳይሆን፣ የዕረፍት ቦታ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ለመስማትና ለማናገር ዋናው ነገር በፈቃደኝነት ወደ እርሱ መሄድ ነው፡፡ በእግሩ ሥር ከሆንን፣ እርሱ ሊያናግረን ዝግጁ ነው፡፡

ኢየሱስ እየጸለየም እያለ፣ ደቄ መዛሙርት በባህር ላይ ሆኖ ከንፋስ ጋር ይታገሉ ነበር፡፡ ንፋሱም በፊት ለፍት ገጥሞአቸው ነበር፡፡ ወደ ፊት ከመሄድ ሲለከለከላቸው እዚያው እየቀዘፉ አያሉ፣ እኩለ ለሊት ደረሰ፡፡

ጥያቄ፡2 ኢየሱስ ለምን ግድ ቢሎአች ወደዚህ አይነት ችግር ላካቸው?

ጥያቄ፡3 የጌታን መልእክት ሰምቶ የሚወጣ ሰው በመንገድ ተግዳሮት ሊገጥመው ይችላል ወይ?
--- አንዳነድ ጊዜ ድምፅ ሰምተው የሚሄዱ ሰዎች መከራቸው ሊበዛ ይችላል፡፡ ሙሴ ከእግዚአብሄር ሰምቶ ወደ ግብጽ ከተመለሰ በሃላ የሕዝቡ መከራ እጥፍ ሆነ፡፡ ፈሪኦን መከራቸውን አበዛባቸው፡፡
---ኤርሚያስ ከእግዚአብሄር ሰምቶ ሲናገር ወደ ጉድጓድ መጣልና ሥደት ደርሶበት ነበረ፡፡
--- ዳዊት ከእግዚአብሄር ዘንድ ቅባትን ከተቀበለ በሃላ ብዙ ስደትና መንከራተት ደርሶበት ነበር፡፡

** የሚያስቸግር ሁኔታ ሳይገጥመው ወይም የማይቻል ነገር ሳይኖር የእግዚአብሄርን ተዓምር ማየት ለሰው ይከብዳል፡፡ ሰው የሚያምነው ከሚያየውና ከሚለማመደው ነገር ነው፡፡

- አስታውሱ፣ እነዚህ ደቄመዛሙርት ሲያገለግሉ ቆይቶ የመጡ ሰዎች ናቸው፡፡
በእነርሱ እጂ ከጌታ ትእዛዝና ከመንፈሱ የተነሳ ብዙ ተዓምራት ሆነዋል፡፡

ግን ደግሞ ሲለ እንጄራው ኢየሱስ ሲጠይቃቸው ምንም እንደማይቻል ነበር ያሰቡት፡፡ አሁንም በባህር ላይ ችግር ገጥሞአቸዋል፡፡ ይህንን ንፋስ መገሰጽ ችለሏልን? አልፈውስ ሊሄዱ ችለዋልን?
- ኢየሱስ በተራራው ላይም ሆኖ፣ ይከታተላቸው ነበር፡፡ ርቀቱም፣ ነፋሱም፣ ሌላውም ነገር አልከለከለውም፡፡

- ጌታ "ሂዱ!" ቢሎ ስንቸገር ቸል አይለንም፡፡ በእርግጥ በሚገጥመን ችግር ሁሉ ላይ ክንዱን በማሳየት፣ ታላቅነቱን በሕይወታችን እንድናውቅ ያደርገናል፡፡ ይህ ደግሞ ለእኛ ትልቅ ሀብት ነው፡፡ እግዚብሄርን ማወቅና እርሱ ምን ማድረግ እንደሚችል ካወቅን ትልቅ ነገር አግንተናል ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም በሃላ ሊገጥመን ለሚችል ማንኛውም ችግር መፍትሄው አለንና፡፡

- በፍሪኃታቸውም መካከል ሲደርስ "እኔ ነኝ ፣ አትፍሩ" አላቸው፡፡

- በደከሙና ተስፋቸው በተሟጠጠ ጊዜ ኢየሱስ መጣላቸው፡፡ ሲመጣም እነርሱን ከመሄድ ባገደው ባህሪና በሃይለኛው ንፋስ መካከል አቋርጦ ነበር የደረሰው፡፡
- በደረሰም ጊዜ ነፋሱ ጸጥ ብሎ ነበር፣ ሰዎቹ ግን እጅግ ተረሙ፡፡ ማርቆስ ሲጽፍ፣ "የእንጄራውን ነገር አላስተዋሉም ነበር" ይላል፡፡

ማቴዎስ ደግሞ ጴጥሮስ ያለውንም ነገር ጨምሮ መስክሮአል፡፡

ከዚያም ከተሻገሩ በኃላ ወደ ሲራ ገቡ፡፡ ቁ.55-56፡፡

- በእምነት ለዳሰሱት የኢየሱስ ልብስ፣ የጌታ ስምና ክብር የተጠራበት ነገር ሁሉ ይረዳናል፡፡

- የዳሰሱት ሁሉ ዳኑ ሲል፣ ምናልባትም ለመዳሰስ ባለመፈለጋቸው ወይም በመናቃቸው ከእነ በሽታቸው ወደ ቤታቸው ምናልባትም ወደ መቃብራቸው የገቡ ሰዎችም እንዳሉ ነው፡፡

-- ዛሬም ብዙ ሰዎች የእግዚአብሄር ነገር፣ የኢየሱስ ነገር ሞኝነት ብቻ የሚመስላቸውም አሉ፡፡

እውነቱ ግን በእጅ መዳሰሱ ሳይሆን፣ በእግዚአብሄር ጸጋ የቀረበላቸውን የፈውስ እድል ከእርሱ እጅ በእምነት መቀበላቸውን ለማሳየት የሚያደርጉት መንካት ነው፡፡

ከዚህ ክፍል ከኢየሱስ ምን ተማርን
- ፍቅሩና ርህራሄ ነበረው
- ከአባቱ ጋር ላለው ህብረት ትልቅ ዋጋ ነበረው
- ቃሉን ሰምቶ የወጡትን ፈጽሞ አይተውም
- በፍጠረት ሁሉ ላይ ሥልጣን አለው
- የሰዎችን አምነት ያከብራል፡፡
- ተልእኮወን ለመፈጸም የሚያስፈልገውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ ነበረ፡፡

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?