Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት

ማር 6፡ 14- 29 የኢየሱስ ስም ይታወቅ

14 "ስሙም ተገልጦአልና ንጉሡ ሄሮድስ በሰማ ጊዜ። መጥምቁ ዮሐንስ ከሙታን ተነሥቶአል ስለዚህም ኃይል በእርሱ ይደረጋል አለ።
15 ሌሎችም። ኤልያስ ነው አሉ፤ ሌሎችም። ከነቢያት እንደ አንዱ ነቢይ ነው አሉ።
16 ሄሮድስ ግን ሰምቶ። እኔ ራሱን ያስቈረጥሁት ዮሐንስ ይህ ነው እርሱ ከሙታን ተነሥቶአል አለ።
17 ሄሮድስ የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን አግብቶ ነበርና በእርስዋ ምክንያት ራሱ ልኮ ዮሐንስን አስይዞ በወኅኒ አሳስሮት ነበር፤
18 ዮሐንስ ሄሮድስን። የወንድምህ ሚስት ለአንተ ልትሆን አልተፈቀደም ይለው ነበርና።
19 ሄሮድያዳ ግን ተቃውማው ልትገድለው ትፈልግ ነበር አልቻለችም፤
20 ሄሮድስ ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው እንደ ሆነ አውቆ ይፈራውና ይጠባበቀው ነበር፤ እርሱንም ሰምቶ በብዙ ነገር ያመነታ ነበር፤
21 በደስታም ይሰማው ነበር። ሄሮድስም በተወለደበት ቀን ለመኳንንቱና ለሻለቆቹ ለገሊላም ሹማምንት ግብር ባደረገ ጊዜ ምቹ ቀን ሆነላትና
22 የሄሮድያዳ ልጅ ገብታ ስትዘፍን ሄሮድስንና ከእርሱ ጋር የተቀመጡትን ደስ አሰኘቻቸው። ንጉሡም ብላቴናይቱን። የምትወጂውን ሁሉ ለምኚኝ እሰጥሽማለሁ አላት፤
23 የመንግሥቴ እኩሌታ ስንኳ ቢሆን የምትለምኚውን ሁሉ እሰጥሻለሁ ብሎ ማለላት።
24 ወጥታም ለእናትዋ። ምን ልለምነው? አለች። እርስዋም፦ የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ አለች።
25 ወዲያውም ፈጥና ወደ ንጉሡ ገብታ። የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን ልትሰጠኝ እወዳለሁ ብላ ለመነችው።
26 ንጉሡም እጅግ አዝኖ ስለ መሐላው ከእርሱም ጋር ስለ ተቀመጡት ሊነሣት አልወደደም።
27 ወዲያውም ንጉሡ ባለ ወግ ልኮ ራሱን እንዲያመጣ አዘዘው። ሄዶም በወኅኒ ራሱን ቈረጠ፥
28 ራሱንም በወጭት አምጥቶ ለብላቴናይቱ ሰጣት፥ ብላቴናይቱም ለእናትዋ ሰጠች።
29 ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው መጡ በድኑንም ወስደው ቀበሩት። "

ባለፈው ሳምንት ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ሥልጣንን ሰጥቶ ሁለት ሁለት አድርጎ ለአገልግት እንደላካቸው አይተን ነበርን፡፡ እነርሱ ደግሞ ተልከው የንሰሃን ስብከት እንደ ሰበኩ ተነጋግረን ነበር፡፡ ንስሓ ማለት መንገድን/አቅጣጫን መለወጥ፡፡

ይህም የተደረገው ሰዎች ከእግዚአብሄር ጋር እንዲታረቁ ለማድረግ እንደ ነበር፡፡ ያነ እንዳየነው
-- ተልዕኮ - የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትልቁ አመጣጥ ሰዎችን ከሐጢአታቸው ማዳንና ከእግዚአብሄር ጋር ማስታረቅ ነው፡፡
-- የተላኩ ሰዎች - ተላኪ የራሱን መልእክት እንዲያስተላልፍ አይጠበቅም፡፡ ካልሆነ ታማኝና ብቁ ተላላኪ መሆን ይሳነዋል፡፡
-- ለተልእኮው የሚያስፈልጉ ነገሮችና - በእግዚአብሄር አቅርቦት መታመን፣
-- መልእክተኞቹ ማድረግ ያለባቸው ነገሮች፡፡ - በተልእኮው ውስጥ ራሳቸውን እንዲጠብቁ፡፡

- ሁለት ሁለት ሆነው ሄደው የነበሩትም በኢየሱስ ስምና እርሱ በሰጣቸው ሥልጣን ሲያገለግሉ ኢየሱስ የሚባለው ስም በሀገረው ሰው ሁሉ ጆሮ ከመድረሱ የተነሳ፣ ወደ ቤተመንግስት ይሄዱ የነበሩት ሁሉና ያንን ሀገር ያስተዳድር የነበረው ንጉስ ሄሮድስም መስማቱን ወንጌላዊው ማርቆስ ይመሰክራል፡፡

- እጅግ በጣም ትልቅ ትምህርት የሚሰጠን የተላኩት አገልጋዮች የሚያስተዋውቁት የላካቸውንና እነርሱም የሚጠቀሙበትን ነገር ሁሉ የሰጣቸውን ኢየሱስን እንጂ ራሳቸውንና የራሳቸውን ክብር አልሰበኩም፡፡

- ሄሮድስ የኢየሱስን ስራ ሲሰማ በመለኮታዊ አሠራር ውስጥ የሚሳተፍ እንጂ ተራ ፖሌቲከኛ እንዳልነበረ አመነ፡፡
ከዚህም አስተሳሰቡ የተነሳ ትልቅ ፍርሃት በሄሮድስ ሕይወት ውስጥ እንደ ተፈጠረ፣ እርሱው ከተናገረው ነገር መረዳት እንችላለን፡፡

ሄሮድስ ለምን ይፈራል?

- መጽሃፍ ቅዱስ ሲናገር "ኃጢአተኛን ኃጢአቱ ታሳድደዋለች " ይላል፡፡ ሄሮድስ ነቢዩ ዮሓንስ የተናገረውን እውነት ሲሰማ መልእክቱን በደስታ አልተቀበለውም ነበር፡፡ ምክንያቱም እርሱ የተናገረው ነገር የድፍረት፣ የጣልቃ ገብነት፣ የፖለቲካ ሃሳብም ነበረው፡፡

ስለዚህ ዮሃንስም መልካም ያልሆነ ነገር በሥልጣንና በዝና፣ ምናልባትም በገንዘብ አቅሙ ተጠቅሞ መልካም ያልሆነ ነገር ሲያደርግ የነበረውን ንጉስ ልክ እንዳልሆነ በመንገርና በመገሰጽ ስለተናገረው ንጉሱ ሄሮድስ ወደ እስር ቤት ከትቶት ነበር፡፡ እኔና ምናልባት እናንተም ድንበራችን፣ ደረጃችንን ጠብቀን ለነገሮች ሁሉ ኮመንት እንሰጣለን፡፡ በእግዚአብሄር መንፈስ ይመራና የንስሃን ስብከት ይሰብክ የነበረው ዮሃንስ ግን ትኩረቱ በዓላማውና ለዚያም ዓላማ በሾሜው በእግዚአብሄር አንጂ መልእክቱን ፍት አይቶ አይቀያይርም ነበር፡፡

የተላከው የንስሃን ስብከት መስበክ ስለነበረ፣ ለታናናሾችም፣ ለታላላቆችም፣ ስለሃይማኖት ግን ለማይላቸውና ሃይማኖተኞች ለሆኑት ሓጢአተኞችም፣ ለህዝቡና ኃጢአተኞች ለሆኑት መሪዎችቸው ተመሳሳይ ስብከት ይሰብክ ነበር፡፡

"ንስሃ ግቡ!" እያለ፡፡ አንዳንድ ግዜ እኛ በሰዎች መካከል ካለን ስም፣ ዝና፣ ስልጣን፣ ሃብት የተነሳ፣ ሰዎች መልካም መልካሙን ብቻ ነግረውን ስላስለመዱን እውነት የሚነግረን ሰው ለመቀበል ይከብደን ይሆናል፡፡ ሔሮድስም ያንን ልምምድ ሳይኖረው አልቀረም፣ ንጉስ ስለሆነ ታላቅነቱን፣ ሥልጣኑን፣ ዝናውን፣ ሀብቱን .. እንጂ የወደቀበትን፣ የተሳሳተበትን፣ ንስሃ መግባት ያለበትን የሚነግረው አልነበረውም፡፡

-ተልእኮውን ለመፈጸምና እግዚብሄርን ብቻ ማስደሰት ዓላማው የሆነው ዮሃንስ ግን ቀርቦ "ንስሃ ያስፈልግሃል" አለው፡፡ ምናልባት እኔ? ለምን? በምን? ማለቱ አልቀረም፡፡
ዮሃንስም በወንድምህ ላይ ክፋት ሰርተሃል አለው፡፡ ፍልጶስን አስገድለህ አንተ ደግሞ ምስቱን መውሰድ አይገባህም አለው፡፡

ይንን አይነቱን ንግግር ንጉሱም ሆነ ምስት ተብየይቱ አልወደዱትም፡፡ ሁለቱም ተቆጥተዋል ሁለቱም ጠልተውታል፡፡ ሆኖም ግን በእርሱ ውስጥ የጽድቅን ንግርና ሌላውን መለያየት የቻለ ሰው ነው፡፡ ምናልባትም ከአስተዳደርሥራው ጋር፣ ምናልባት እግዚአብርን መፍራት በተወሰነ መልኩ ውስጡ ገብቶም ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንኒያቱም ዮሃንስ የተናገረው ነገር እውነት መሆኑን ውስጡም ይመሰክርለት ነበር፡፡ ስለዚህ ወዲያው መግደል አልፈለገም፡፡ ሆኖም ግን ሁለተኛ እንዳይመለስበት ትምህርት ያገኝበት እንደሆን ብሎ አሳሰረው፡፡

ያቺ ባሏን ትታ ወደ እርሱ የገባችሁ የወንድሙ ምስት ግን ቅመኛ ነበረች፡፡ መራራነት በውስጧ ሞልቶ ነበርና ምንም አይነት የመልእክት ምዛን መጠቀም አልቻለችም፡፡ ሞት የተገባው እንደሆን በየነችና በራሷ ምንም ማድረግ ስለማይቻላት፣ ቀንን ትጠብቅ ነበር፡፡ ሰበብን ትፈልግ ነበር፡፡ እግዚአብሄር ከእንደዚህ ዓይነቱ ሕይወት ይጠብቀን፡፡

ሁሌም ክፋትን የሚያስቡና መራራነትን የምንከባከቡት ሰዎች የሚያገኙትን አድል ሁሉ ለመግደል/ለማጥፋት ይጠቀሙበታል፡፡ የጦርነት ቀንም ቢመጣ የልደት ቀን ቢመጣ የሚደሰቱበትም የሚያዝኑበትም ነገር ብከሰት አጋጣሚዎችን ሁሉ ለመግደል ይጠቀሙበታል፡፡
ጌታ ከዚህ ይጠብቀን፡፡ ልባችንንም ይጠብቅ፡፡

የፍልጶስ ምስት የነበረችዋም በንጉሱ ልደት ቀን ንጉሱ ደስ ብሎት ስጦታ መስጠት ሲፈልግ በራሱን ክብር ተገን አድርጋ ገዳይ አስደረገችው፡፡

- ክብራችን ጣኦታችን ከሆነ፣ ስማችን ጣዖታችን ከሆነ፣ ለእርሱ ብለን ባንወድም ገዳዮች፣ ባንወድም አስገዳዮች፣ እያወቅንም የክፉ ምክር ተቀባዮች እንሆናለን፡፡

- ንጉሱ ሄሮድስ የተጠየቀውን ነገር አንቢ ማለት ይችል ነበር፡፡ ግን እርሱ በሚወደው ክብር መጣችበት ‹ምስቱ›፡፡

- ዛሬ ከጌታ ይልቅ የምንወዳቸውና የከበረ ቦታ/ዋጋ የሚንሰጣቸው ነገሮች ምንድናቸው? ለእነርሱ ብለን እናማለን፣ እንጠላለን፣ እንገድላለን፣ እንዋሻለን፣ በመጨረሻም ውድዋ ነፍሳችንን እንጎዳለን፡፡ እባካችሁ ይቅርብን፡፡

ንጉሱ ሄሮድስ ሁለት እድሎች ነበሩት፡፡
1. መጥመቁ ዮሃንስ ሲናግረው በንሰሃ መመለስ፡፡ ግን አልቻለም፡፡ የተባለው ነገር እውነትነት ያለው መሆኑ ቢታወቅም ክብሩን ግን መጠበቅ ይፈልግ ነበር፡፡ ጻድቅ መሆንን የሚያውቀን ሰው እውነት መናገሩን የሚያውቀውን ሰው፣ በሰዎች ዘንድ ያለውን ክብሩን ለመጠባቅ ብቻ ሲል አሳሰረው፡፡

የሚገርማፈችሁ ቁ 20 ላይ ስናነብ፡-

"ሄሮድስ ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው እንደ ሆነ አውቆ
ይፈራውና ይጠባበቀው ነበር፤
እርሱንም ሰምቶ በብዙ ነገር ያመነታ ነበር፤
በደስታም ይሰማው ነበር። " ይላል፡፡

ይህ ምን ማለት ነው ? ዮሃንስ በተናገረው ነገር ላይ እርምጃ መውሰድ የሚልግ ግን ምናልባት ከክብሩ፣ ከይሉኝታ፣ ከምስቱ ድምጽ... የተነሳ ደግሞ ማድረግ አቅቶት ያመነታ ነበር፡፡ ግራ ይጋባ ነበር፡፡ መልእክቱና መንፈሱ ተስማምተዋል፣ ልቡና አይምሮው ግን ከሌሎ ሁኔታዎች የተነሳ ተሳታፊዎች አልነበሩም፡፡
ወይም ደግሞ እግዚአብሄር ለሕዝቅኤል (ም 33) እንደ ነገረ ነበር፡፡ ሙዝቃው ጥሞት፡፡

"30 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የሕዝብህ ልጆች በቅጥር አጠገብና በቤት ደጆች ውስጥ ስለ አንተ ይናገራሉ፥ እርስ በርሳቸውም፥ አንዱ ከአንዱ ጋር። እንሂድና እግዚአብሔር ያለው ቃል ምን እንደ ሆነ እንስማ ብለው ይናገራሉ።
31 ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፥ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፥ ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም በአፋቸው ብዙ ፍቅር ይገልጣሉ፥ ልባቸው ግን ስስታቸውን ትከተላለች።
32 እነሆ፥ አንተ መልካም ድምፅ እንዳለው እንደሚወደድ መዝሙር ማለፊያም አድርጎ በገና እንደሚጫወት ሰው ሆነህላቸዋል ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም።
33እነሆ፥ ይህ ይመጣል በመጣም ጊዜ እነርሱ ነቢይ በመካከላቸው እንደ ነበረ ያውቃሉ። "

ስለዚህ የመጀመሪያ አድሉን ሳየጠቀም ስለቀረ ሕይወቱን በበለጠ ችግር ውስጥ የሚከት ሁለተኛው አድል መጣ፡፡

2. በምስቱ ልጅ በኩል የመጣውን ሁለተኛውንም ሃሳብ እምቢ ማለት ሲችል አሁንም ጣዖቱ የነበረችው "ክብሩ" ከለከለችው፡፡ አሁንም ሁለተኛ ጊዜ አያዘነም ቢሆን በማስገደል ክብሩን ማስቀረትን ፈለገ፡፡
- ዮሃንስ አንገቱ ቀቶርጦ በቅርጫት ለሄሮዲያስ ተሰጣት፡፡ እርሷም ወደ እናቷ ወሰደችው፡፡ እናትዋስ ምን እንደ አረገችው አይታወቅም፡፡ ግን በእርሷ ውስጥ የተከማቸው መራራ ነገር ልጅዋን፣ ንጉሱን፣ ሎሌዎቹን፣ ቤተ/መንግስቱን አልፎም ሃገሩን የሚያረክስና የሚያስጨንቅ ነገር አመጣ፡፡

መጽሃፍ ቅዱስ በዕብ.12፡15-16 "የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ፥ ወይም ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው እንዳይሆን ተጠንቀቁ።" ይላል፡፡

ይህን ማድረጉ ደግሞ ጽድቅ በምነገርበት ጊዜ ሁሉ መኮነንና ፍርሃት ውስጡ መንገስ ጀመረ፡፡ የኢየሱስ ተዓምራትና ዝና ሲወጣ፣ በእርሱም ዘንድ ሲሰማ፣ ስሙንና ክብሩን ጠብቆ ያለው ሄሮድስ በፍርሃትና በጭንቀት ይወረር ነበር፡፡

ሰዎች "ስሙ ኢየሱስ ይባላል፣ ተአምራቶችን ያደርጋል፣ ንስሃን ይሰብካል" ቢለው ሲነግሩት ሄሮድስ ደግሞ "እኔ ያስገደልኩት ዮሃንስ እኮ ነው" ይላል፡፡

3. ይህም ሶስተኛ እድል ሲመጣ እንኳ ሄሮድስ ወደ ኢየሱስ ሂዶ ወይም ኢየሱስን ወደ ቤቱ አስጠርቶ ሊያናግረው አልቻለም፡፡ ፍርሃቱ ግን ቀጥሎአል፡፡ ለምን?
- ምናልባት አሁንም ክብሩን ለመተው ዝግጁ አይደለም
- ምናልባት አሁንም ንሰሃ ያልገባበት ነገር አለ፡፡ ባለፈው ሰምንት ጸጸት ብቻውን ንስና እንዳልሆነ ተነጋግረን ነበር፡፡
- ምናልባት የበደለኝነት ስሜት ስለሚያስቸግረው ሊሆን ይችላል፡፡

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?