Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት
ማር 7፡ 1-13 ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ማመር

ባለፈው ሳምንትና ከዚያን በፊት አብረን በነበሩን ጊዜያት የማርቆስን ወንጌል መሠረት አድርገን ከጌታችን ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ስነማር ነበረ፡፡ ማር 6ን ስናጠና፣ ኢየሱስ ያደረጋቸውን ተዓምራት አይተን ነበር፡፡

ከተዓምራቶቹም ዋና ዋናዎቹ፣
***ኢየሱስ የእግዚአብሄርን መንግስት ወንጌል በሥልጣንና በምገርም መገለጥ ያስምር ነበረ፡፡

***ኢየሱስ ሰዎችን ሃይል ሰጥቶአቸው ሊኮ አነርሱ ደግሞ በተሳካ ሁኔታ በመለኮታዊ ሥልጣን ወንጌልን ሰብከው፣ በክፉ መናፍስት የታሰሩትን ፈትተውና የታመሙትን ፈውሰው ተመልሰዋል፡፡

***በምድረባዳ ላይ በቀላል አቆጣጠር 5000 የሚሆኑትን ሰዎች በአምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ መመገቡ ቢቻ ሳይሆን 12 መሶብ ተርፎቸው እንዲሰበሰብ አድርጎ ነበር፡፡ ይህም ሁኔታ ደግሞ ሰዎች ለንግስና እንዲፈልጉት አነሳስቶአቸው ነበር፡፡ ኢየሱስ ግን የመጣበት ዓላማ እርሱ ስላልነበረ ትቶአቸው ሄዴ፡፡

***ዴቀ መዛሙርቱ በንፋስ በባህር ላይ ሲቸገሩ በውሃ ላይ ተራምዶ ደርሶላቸው ከፈሩት የሞት ፍርሃት እንዳዳናቸው አንብበን ነበር፡፡

***በገንሳረጥ የታመሙትን ሁሉ (በተለይ ሊብሱን ያዳሰሱትን በሙሉ) እንደ ፈወሰም አይተን ነበር፡፡

እነዚህና ሌሎች ኢየሱስ ያረጋቸውና ያስተማራቸው ነገሮች በጊዜው የሃማኖር መሪ በነበሩ ሰዎች ዘንድ ትልቅ ሥጋትን ፈጥሮ ነበር፡፡ ምናልባት በአከባቢው (ሎካሊ) ያሉት መሪዎችና አስተማሪዎች ኢየሱስን ሊያስቆሙትና ሰዎችን ወደ እርሱ ከመሄድ መከልከል ስላልቻሉ፣ ከዋናው መሥሪያበት/ ቤተመቅደስ ሰዎች ተልከው መምጣታቸው አልቀረም፡፡ አሁን እነዚህ በገሊላና አከባቢው እየተፈጠረ ያለውን ችግር ለማስቆምና ኢየሰስን ለማሸነፍ የህግና የመጽሓፍት አዋቂዎች (ኤክስፐርቶች) ከኢየሩሳለም ሄዱ፡፡ እስቲ ከዚያ በሃላ የሆነውን ነገር ከመጽሃፉ እንዳሌ እናንብብ፡፡

የማርቆስ ወንጌል 7
1 ፈሪሳውያንና ከጻፎች ወገን ከኢየሩሳሌም የመጡትም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ።

2 ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንድ በርኵስ ማለት ባልታጠበ እጅ እንጀራ ሲበሉ አዩ።

3 ፈሪሳውያንና አይሁድም ሁሉ የሽማግሎችን ወግ ሲጠብቁ እጃቸውን ደኅና አድርገው ሳይታጠቡ አይበሉምና፥

4 ከገበያም ተመልሰው ካልታጠቡ አይበሉም፥ ጽዋንም ማድጋንም የናስ ዕቃንም አልጋንም እንደ ማጠብ ሌላ ነገር ሊጠብቁት የተቀበሉት ብዙ አለ።

5 ፈሪሳውያንም ጻፎችም። ደቀ መዛሙርትህ እንደ ሽማግሌዎች ወግ ስለ ምን አይሄዱም? ነገር ግን እጃቸውን ሳይታጠቡ እንጀራ ይበላሉ ብለው ጠየቁት።

6 እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ ኢሳይያስ ስለ እናንተ ስለ ግብዞች። ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤

7 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ በእውነት ትንቢት ተናገረ።

8 የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደ ማጠብ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፥ ይህንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ።

9 እንዲህም አላቸው፦ ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ ንቃችኋል።

10 ሙሴ። አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞ። አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት ብሎአልና።

11 እናንተ ግን ትላላችሁ። ሰው አባቱን ወይም እናቱን። ከእኔ የምትጠቀምበት ነገር ሁሉ ቍርባን ማለት መባ ነው ቢል፥

12 ለአባቱና ለእናቱ ምንም እንኳ ሊያደርግ ወደ ፊት አትፈቅዱለትም፤

13 ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ።

ሰዎቹ ኢየሱስንና ደቄ መዛሙርቱን በጥንቃቄ ማየትና መስማት ሲጀምሩ፣ ወዲያው ያዩት ነገር እንዴት ምግብ እንደሚበሉ ነበር፡፡ "እጃቸውን አልታጠቡም"፡፡ በብሉህ ክዳን ሕግ ሲሰጣቸው እግዚብሄር ራሳቸውን ከጣዖት አምልኮና ሕብረተሰቡን ወይም የገዛ ሰውነታቸውንም ከሚጎዱ ነገር እንዲጠብቁ የሚጠቅሙአቸውን ህግጋትን ሰጥቶአቸው ነበር፡፡ እነዚህን ህግጋት ለማስጠበቅ ስባል ህዝቡ ደግሞ በጣም ሰፊ ዐጥር አበጅተውለት ነበር፡፡ በጊዜ ርዝመትና ከብዙ ጸጉር ስንጠቃ በሃላ፣ በኢየሱስ ጊዜ የነበሩት አይውዶች ሌሎችን ሰዎች ለመናቅና ራሳቸውን ለማመጻደቅ ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ስለዚህ በማጠብ ስርዓት ውስጥ ያላለፉ ነገሮች ሁሉ ርኩስ ተደርገው ይቆጠራሉ፡፡ አሁን እጅን የመታጠብ ነገር ከግል ንጽሕና መጠበቅና ከዓኦት አምልኮ ተለይቶ እንደ ሥርዓት ሆኖአል፡፡ ሥርዓቱ ግን የሰው ወግ ነው እንጂ የእግዚብሄር ሕግ አልነበረም፡፡ ሕዝቡም ሆነ የሃይማኖት መሪዎቹ ለመጠበቅና ለማስጠበቅ የሚደክሙት ከእግዚብሄር ህግ ይልቅ ይህንን ነበር፡፡

ስለዚህ ደቀመዛሙቱ ሳይታጠቡ እየበሉ መታየታቸው እጅግ አስቆጣቸው፡፡ "ደቀ መዛሙርትህ እንደ ሽማግሌዎች ወግ ስለ ምን አይሄዱም? ነገር ግን እጃቸውን ሳይታጠቡ እንጀራ ይበላሉ" አሉት፡፡

ኢየሱስ ግን እነርሱ የጠየቁትን ብቻ የሚሰማ አልነበረም፡፡ ሰዎቹን ያያቸው ነበር፡፡ ሥራቸውንና አሰራራቸውንም ያውቅ ነበር፡፡ ስለዚህ 5 ዋና ዋና ነገሮችን ገራቸው፡-

- ግብዞች ናችሁ፡፡

- የከንፈር አምልኮ ብቻ አላችው ልባችሁ ግን ከእግዚአብሄር ጋር አይደለም፡፡ በእግዚአብሄር ስም ትጠይቃላችሁ ግን በልባችሁ በእግአብሄር ላይ የሸፈታችሁ ናችሁ፡፡

- የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሃል፤ እጅግም ንቃችኋል፣ ትሽራላችሁትም" ቁ.9፣13፡፡
ለራሱ የእግዚአብሄር ትዕዛዝ የተወ ሰው እንዴት አድርጎ ሌሎችን በእግዚብሄር መንገድ የሚሄዱትን ራሱ በተያዘበት ይከሳል?

- እናንተ ለራሳችሁ ወግ ብቻ የምትኖሩ ናችሁ፤ በዚህ ክፍል ብቻ 6 ጊኤ ደጋግሞ "ወጋችሁ/የሰው ወግ፣ የሽማግሌቻች ወግ" ይላቸዋል፡፡

- እኔ አውቃችሃለሁ "ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ" ቁ 8ና 13

- "ኢሳይያስ ስለ እናንተ...በእውነት ትንቢት ተናገረ"፡፡ ከሰባት መቶ አመታት በፊት በኢሳይያስ የተነገረውን ትንቢት "ዛሬም ስለእናንቴ ፍጹም ትክክል ነው" ይላቸዋል ኢየሱስ፡፡
መጽሃፍ የሚናገረውን ነገር አነርሱ እንዴ ታርክና ስርዓት ቢያስተምሩም ኢየሱስ ግን ቃሉ ሕያው ነውና አስተውሉት እያላቸው ነው፡፡

ዛሬም ብዙዎቻችን የእግዚአብሄር ቃል ስናነብም ሆነ ስንሰበክ በግል ከራሳችን ጋር በማዛመድ እርምጃ የመውሰድ ዝግጅት፣ ፍላጎት ወይም ዓቅም የለንም፡፡
ኢየሱስ ግን ስለእናንተም ነው ይለናል፡፡

ኢሳይያስ ምን ብሎ ነበረ?

ኢሳ.29፡ 13-24
13 ጌታም፦ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባልና፥ በከንፈርቹም ያከብረኛልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛልና

14 ስለዚህ፥ እነሆ፥ ድንቅ ነገርን በዚህ ሕዝብ መካከል፥ ድንቅ ነገርን ተአምራትንም፥ እንደ ገና አደርጋለሁ የጥበበኞችም ጥበብ ትጠፋለች፥ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።

15 ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ፥ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው። ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል? ለሚሉ ወዮላቸው!

16 ይህ የእናንተ ጠማምነት ነው እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃ የምትቈጠሩ አይደላችሁምን? በውኑ ሥራ ሠሪውን፦ አልሠራኸኝም ይለዋልን? ወይስ የተደረገው አድራጊውን፦ አታስተውልም ይለዋልን?

17 ሊባኖስ እንደ ፍሬያማ እርሻ ሊለወጥ ፍሬያማውም እርሻ እንደ ዱር ሊቈጠር ጥቂት ዘመን የቀረ አይደለምን?

18 በዚያም ቀን ደንቆሮች የመጽሐፍን ቃል ይሰማሉ፥ የዕውሮችም ዓይኖች ከጭጋግና ከጨለማ ተለይተው ያያሉ።

19 የዋሃን ደስታቸውን በእግዚአብሔር ያበዛሉ፥ በሰዎች መካከል ያሉ ችግረኞችም ሐሤትን በእስራኤል ቅዱስ ያደርጋሉ።

20 ጨካኙ ሰው አልቆአልና፥ ፌዘኛውም ጠፍቶአልና፥ ለኃጢአትም የደፈጡ ሁሉ ይቈረጣሉና

21 እነዚህም ሰውን በነገር በደለኛ የሚያደርጉ፥ በበርም ለሚገሥጸው አሽክላ የሚያኖሩ፥ ጻድቁንም በከንቱ ነገር የሚያስቱ ናቸው።

22 ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠ እግዚአብሔር ስለ ያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል። ያዕቆብ አሁን አያፍርም፥ ፊቱም አሁን አይለወጥም።

23 ነገር ግን የእጄን ሥራ ልጆቹን በመካከሉ ባያቸው ጊዜ ስሜን ይቀድሳሉ የያዕቆብንም ቅዱስ ይቀድሳሉ፥ የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ።

24 በመንፈስም የሳቱ ማስተዋልን ያውቃሉ፥ የሚያጕረመርሙም ትምህርትን ይቀበላሉ።

ኢሳይያስ (29:13) ይህንን ትንቢት በተናገረበት ጊዜ ምን ዓይነት ሁኔታ ነበረ?
--የአምልኮ ልምምዶች ነበሩ--
--ቤተ መቅደስ ነበረ
--የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ነበሩ
--ነገሮችን በቅንዓት/በሥርዓት ይደረጉ ነበር፡፡
-- እግዚአብሄርን ማወቅ አልነበረም፡፡
--እግዚአብሄርን መፍራትም አይታይም፡፡
--የእግዚአብሄር ቃል/ድምጽ አይተገበርም ነበር፡፡
--የሰዎችን ሥርዓት እንጂ የእግዚአብሄርን ህግ አያስተምሩም ነበር፡፡ አስተምዕሮታቸው (ዶክትሪናቸው) የተበላሼ ነበር፡፡
-- አብዛኛው የአምልኮና የህይወት ልምምዶች የሚመሩት በእግዚአብሄር ምክር ሳይሆን "ብልዎችና፤ ጥበበኞች" በሚባሉ ሰዎች ነው፡፡
ስለዚህ እግዚአብሄር ሊያደርግ ያሰበው ተኣምር አስቀድሞ "የጥበበኞችን ጥበብ ማጥፋት" ነው፡፡ እነዚያ ሰዎች "ጥበባቸውንና ብልሃታቸውን ከእግዚአብሄር ለመሰወር ይጠቀሙበታል፡፡ ዉጭ ውጪውን አምልኮና ሃይማኖተኛ እያደረጉ ጥልቅ በሆነው ልባቸው ውስጥ ግን ከእግዚአብሄር እንኳ ሳይቀር ሊሰውሩት የሚፈልጉ ዓላማ ነበራቸው፡፡ እግዚአብሄር ያንን ነገር በመግለጥ፣ የተደበቀውን ምክራቸውን በማፍረስ ክብር እንደሚያገኝ ተናገረ፡፡
-- እግዚአብሄር ፈጣሪአቸው እንደሆነ ሊያስታውሳቸው ፈለገ፡፡ እርሱ "እኔ ሰርቻችሃለሁ፣ አኔ በእናንተ ላይ ስልጣን አለኝ፣ እኔ አልታለልም፣ እኔ በማደርገውም ነገር አልጠየቅም" ይላቸው ነበር፡፡ ይህን ደግሞ በሸክላ ሰሪና ከሸክላ በተሠራው ዕቃ አስመስሎ ነገራቸው፡፡
-- በተጨማሪም እግዚአብሄር ነገሮች እንዳሉ እንዳይቀጥሉ ሁኔታዎችን የሚገለባብጥበትን ጊዜ እንደሚያመጣ በነቢዩ በኢሳይያስ (29፡17) ተናገራቸው፡፡ በዚያን ግዜ በደንቆሮነትና በአውርነት የተፈረጁት ሁሉ የሚያዩና የሚሰሙ ይሆናሉ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ እግዚአብሄርንና ቃሉን ረስተው በራሳቸው ማስተዋል የሚደገፉት ደግሞ ይወድቃሉ፡፡

ይህንን ታዲያ ኢየሱስ በነበረበት ጊዜ ካለው ሁኔታ ጋር ምን አገናኘው?
-- አምልኮ ነበረ፡፡ ወግንና ሥርዓትን መጠበቅ ነበረ፡፡
-- ቤተ መቅደስ ነበረ-- (ይሸጥበትና ይለወጥበት ነበረ-- ጥቅት ሰዎች ለራሳቸው ትርፍ ይጠቀሙበት ነበረ-- እነርሱ በተመቅደስን ሲያስቡ ንግዳቸውን ብቻ ያስባሉ፣ እንዴ አድርገው ምርታቸውን እንደሚሸጡ፣ እንዴ አድርገው ብዙ ብር እንደሚያገኙ ያስባሉ፤ ምናልባት ሽያጩም የሚካሄደው በአም
-- ባነበብነው ስፊራም ሆነ በሌሎች ቦታዎች መልካም እየመሠሉ (የእግዚአብሄርን ቃል እየጠቀሱ) ኢየሱስን በነገር ሊያጠምዱት ይሞክሩ እንደነበር እናነባለን፡፡ ይህንንም ሲያደርጉ ኢየሱስ በልባቸው ያለውን እንደማያውቅ እግዚአብሄርም ስለሚያስቡት ነገር እንደማይጠይቃቸው አድርገው ይቆጥሩ ነበር፡፡ በሌላ ጎኑ ደግሞ ኢየሱስን የሚሰሙትንና እርሱን በየዋህነት የሚከተሉትን እንደ ሞኞችና ምንም እንደማያውቁ ይቆጥሩአቸው ነበር፡፡ ኢየሱስ ግን "የማያዪ እንዲአዪ፣ የሚአዩ ደግሞ እንዳየያዩ ለማድረግ መጥቻለው ብሎ ነበር፡፡
-- የተበላሼ አስተምህሮት ነበራቸው፡፡ (ማር.7፡7-8)
በኢሳያስ የተነገረው ትንቢት በጊዜ የነበሩትን ሰዎች ቢመክርም፣ ኢየሱስ በምድር ላይ ይመላለስበት በነበረም ጊዜ የአግዚአብሄር ሀሳብ ያልተለወጠ እንደሆነ፣ እግዚአብሄር ዓቅሙ፣ እውቀቱ፣ ስልጣኑ እንዳልተለወጠ መሆኑን ኢየሱስ ተናገረ፡፡

ዛሬም ቢኆን፣ እግዚአብሄር ሕያው ነው፡፡ እርሱ አልተለወጠም፡፡ ስለዚህ የአምልኮና የአገልግሎት ሕወቶቻችንን በእግዚአብሄር ቃል መሠረት ልንፈትሻቸው ይገቡናል፡፡

ዛሬ በክርስቲያኖች መካከል ምን አለ?
ይህን በሚልበት ጊዜ ሁሉም ከራሱ ጀምሮ ያስብበት፡፡
-- አምልኮ አለ፡፡ ይዘመራል፣ ይጸለያል፣ ማገልገል፣ መገልገል፣ የተለያዩ ኣይነት ስርዓቶችና ደንቦች አሉ፡፡ እነዚህ ሥርዓቶች እኩለታቸው ከአባቶች የወረስናቸው፣ እኩለታቸው ከምንኖርባቸው ሀገሮች፣ አከባብዎች ባህል ያገኘናቸው፣ እኩለታቸው ደግሞ እኛው ራሳችን የፈጠርናቸውና ያሳደግናቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚሀ ሁሉ በእግዚአብሄር ሕግ የበላይነት ሥር ቢሰሩ መልካም ነው፡፡
-- ችግሩ ግን የእግዚአብሄር ህግ ሲጣስና ስንጥስ ግድ የማይለን ክርስቲያኖች፣ እነዚያ ሕጎቻችን ሲጣሱ ደማችን ይፈላል፡፡ እግዚአብሄር ሲቃለል የማይሰማን ሰዎች ወጎቻችን ሲጣሱ ዱላ ይዘን እንወጣለን፡፡
-- ኢየሱስ ዛሬም እንዲህ ይላል፣ "ኢሳያስ ስለ እናንተ ትክክል ተናገረ... በከንፈሮቻችሁ ቢቻ ታመልኩኛላችሁ"፡፡

ታዲያ ምን ማድረግ ይኖርብል?
- ንስሓ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡
- ወደ እኔ ተመለሱ ይላል እግዚአብሄር፡፡ የራሳችሁን ወግ አስቀምጡና የእግዚአብሄርን ስርዓን አንግቡ፡፡

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?