Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት
ከኢየሱስ በመማር ፡ በምህረት ክልል ውስጥ ራስህን ጠብቅ፡፡


ማር 4፡1-20
እስቲ ጥቅት ያለፍንባቸውን ነገሮች እያስታወስን የዛሬውን ትምህርት አብረን እንጀምር፡፡ አራት ሰናሪዎችን ጥያቄዎችን ላንሳና በየግላችን መልስ እንድንሰጥበት በፍቅር እጠይቃችሃለሁ፡፡
1. ቃሉን በሚሰበክበት ቦታ/ጉባኤ ቁጭ ብለን ሰምተን/የተባለውንም ተረድተን ከዚያው ሳንወጣ/ቤት ሳንደርስ ስለምን እንደተሰበከ እንኳ ጠፍቶብን የወጣንበትን ጊዜ ታስታውሳላችሁ? ቃሉ የት ሂዶ ነው?
2. ቃሉ ስሰበክ ሰምተን፣ በደምብ ገብቶንና ሃሳቡን ተቀብለን ግን የሰማነው ቃል ተቃራኒ የሆኑ ነገሮች ሲመጡብን የረሳንበትን/የተውንበትንስ ጊዜ ታስታውሳላችሁን? ለምን በዚያ ወቅት ጸንተን በቃሉ መሠረት መቆም ያቃተን ይመስላችሃል?
3. ቃሉን ሰምቴን፣ ተቀብለንና በሕይወታችን ውስጥ ጠብቀነው አቆይተን አንዳነድ ጊዜ፣ የክርስቲናችንን ፍሬ ማዬ የምያቅትበት ጊዜም አለ፡፡ ከቃሉ ይልቅ፣ ከቃሉ ጋር ተመሳስሎና አስታኮ የሚመጡ አንድ አንድ ነገሮች በሕይወታችን አድገውና አብበው የምናየው ከምን የተነሳ ነው?
4. ሌላ ጊዜ የተሰበከን ቃል ደግሞ በሕይወታችን ከመቀመጥ አልፎ፣ ምርጫዎቻችንን፣ አምልኮዎቻችንን፣ ወዳጆቻችንንና ውሎአችንን ሁሉ ቀይሮአል፡፡ ያም ብቻ ሳይሆን ደግሞ፣ ሌሎችን የምስብ፣ የሚኮንን፣ የሚያጽናና፣ የሚያስፈራ ማንነት በውስጣችን ፈጥሮአል፡፡ ይህስ እንዴት ሊሆን ቻለ?

በመጽሓፍ ቅዱስ መሠረት፣ እግዚአብሄር አንድን ሰው የሚገናኝበት፣ የሚያድንበት፣ የሚመክርበት አስቀድሞ ቃሉን በመላክ ነው፡፡
አብርሃምን ሲጠራው በቃሉ ተገልጦለት ነው፡፡ አብርሃም ታምር አይቶ ወጣ የሚል ሳይሆን እግዚአብሄርን ሰምቶ ወጣ የሚልን ቃል እናነባለን፡፡
ሙሴ አስቀድሞ ያየው የምነድ ቁጥቋጦ ቀርቦ ለመስማት (ወደ ቃሉ) ትኩረትን ለመሳብ የሆነ እንጂ በራሱ በቂ አልነበረም፡፡
በሃላም ለእርሱ ለራሱ የጠራውን የእስራኤልን ህዝብ፣ ሕዝብ ሆኖለት እንዲቀጥል፣ ቃልን ሰጣቸው፡፡ በዚያ ቃል ውስጥ የእግዚአብሄር ፈቃድ ተገለጦ ነበር፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ይህ ሕዝብ ለዘላለም (ትውልድ ሁሉ) ከእርሱ ጋር በሕብረት አንዲኖር፣ ቃልን/ሕጉን ሰጣቸው፡፡
ቃሉንም ለልጆቻቸው እንዲያስተምሩ፣ ሁልጊዜም እያስታወሱ እንዲኖሩ፣ በቤታችው መቃን እንዲያኖሩ ጠየቃቸው፡፡
በመጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ የሚናያቸው በግለሰቦችም ሆነ በሐገር ደረጃ የደረሱት ትናንሽና ታላላቅ ውድቀቶች የእግዚአብሄርን ቃል ካለመስማት፣ ካለመታዘዝ ጋር ተያይዞ የመጡ ነበሩ፡፡
በተቃራኒው ደግሞ፣ የምናነባቸው ታላላቅ ድሎች (የአብርሃም፣ የያእቆብ፣ የሙሴ፣ የእያሱ፣ የዳዊት፣ የኢየሱስ፣ የጳውሎስ…) ቃሉን ከመቀበል፣ ከማመንና በእርሱ ከማደግ ጋር ተያይዘው የመጡ ድሎች ናቸው፡፡
ሁልጊዜ ከእግዚአብሄር ቃል ጋር/ቀጥሎ የመለኮት ሓይል መገለጥ አለ፡፡ ይህ ዛሬም እውነት ነው፡፡
የህንን መረሆ እየሱስ ካስተማረው ትምህርት ጋር አያይዘን አንመልከት፡፡
ዘር ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ፡፡
ዘር የሚዘራበት ዋና ምክንያት ትውልድን ለማስቀጠልና ለመብዛት ነው፡፡ አንድ እንዲያፈራ ተፈልጎ የተዘራ/የተተከለ ተክል ፍሬ ካልሰጠ፣ የቆረጣል፡፡ ገበሬው አይፈልገውም፡፡ ገበሬ ብዙ ጊዜ፣ ውጤት ላይ አተኩሮ የሚሰራ አንጂ ለውቤት ብሎ አይደለም፡፡
ኢየሱስም ያንን ነው ያስተማረው፡፡ የማያፈራወን ቅርንጫፍ የቆርጠዋል፣ ወደ እሳትም ይጣላል ብሎ፡፡
ሲለዚህ በክርስቲናችን ውስጥ ማፍራት ትልቁ አላማችን መሆን አለበት፡፡ በእኛ ውስጥ የተዘራው ዘር አንዳያፈራ/አንዲያፈራ ከሚያደርጉት ነገሮች ጥቅቶችን አንመልከት፡፡
የመሬት ዝግጅት (ራስን ማጠንከር፣ ራስን ላይ ላይ ማድረግ ፤ ራሰን ከሌሎች ነገሮች ጋር ማጠላለፍ (አረም) ከማፈርራት ይከለክላሉ፡፡

ማሪ 4፡
ኢየሱስ በተናገረው ምሳሌ ውስጥ
1. በመንገድ ዳር የወደቄ-- ሠይጣን ወዲያው መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ይወስዳል፡፡ ስለዚህ ከቃሉ ጋር የሚኖሩት ለጥቅት ጊዜ ብቻ ስለሆነ፣ ቃሉ በሕይወታቸው ለመብቀል አድል አያገኝም፡፡
- እነዚህ ሰዎች መስማትን ይሰማሉ፣ ደንቆሮዎች አይደሉም ፡፡ ነገር ግን ቃሉን ሰምተው ለመቀበል ዝግጅት የላቸውም፡፡
- አንዳነዶችን የቃሉ እውነት ቀልድ ስለሚመስላቸው፣ ለመሸነፍና ለማመን የተዘፋጁ አይደለም፡፡ በዚያኑ ልክ ደግሞ፣ ክፉው መጥቶ የባሰውኑ ይቀማቸዋል፡፡
- በእስር ቤት ተቆልፎበት ያለን ሰው ውሰዱ፡፡ አንዱ ቁልፍ ያቃብለዋል፡፡ እርሱ ደግሞ ቁልፉን ካመጣውና ከቁልፉ ምንም እምነት የለውም፡፡ እየቀለደ እያለ፣ የእርሱ ጠባቂ/አጋች ደግሞ መጥቶ ያንን ቁልፍ ይቀማዋል፡፡
- ሠይጣን ቃሉን የሚቀማቸው ለራሱ ሊጠቀምበት ሳይሆን፣ ሰዎቹ ቃሉን ሰምቴው፣ አምነትም በውስጣቸው ተፈጥሮ እንዳይድኑ ለማድረግ ብቻ ነው (ሉቃ.8፡12)፡፡
- የሓሥ. 17፡ 18-34
‹‹18 ከኤፊቆሮስ ወገንና ኢስጦኢኮችም ከተባሉት ፈላስፎች አንዳንዶቹ ከእርሱ ጋር ተገናኙ። አንዳንዶቹም። ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይወዳል? አሉ፤ ሌሎችም የኢየሱስንና የትንሣኤውን ወንጌል ስለ ሰበከላቸው። አዲሶችን አማልክት የሚያወራ ይመስላል አሉ።
19-20 ይዘውም። ይህ የምትናገረው አዲስ ትምህርት ምን እንደሆነ እናውቅ ዘንድ ይቻለናልን? በጆሮአችን እንግዳ ነገር ታሰማናለህና፤ እንግዲህ ይህ ነገር ምን እንደሆነ እናውቅ ዘንድ እንፈቅዳለን ብለው አርዮስፋጎስ ወደ ተባለው ስፍራ ወሰዱት።
21 የአቴና ሰዎች ሁሉና በዚያ የኖሩ እንግዶች አዲስ ነገርን ከመናገርና ከመስማት በቀር በሌላ ጉዳይ አይውሉም ነበርና።
22 ጳውሎስም በአርዮስፋጎስ መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፦ የአቴና ሰዎች ሆይ፥ እናንተ በሁሉ ነገር አማልክትን እጅግ እንደምትፈሩ እመለከታለሁ።
23 የምታመልኩትን እየተመለከትሁ ሳልፍ። ለማይታወቅ አምላክ የሚል ጽሕፈት ያለበትን መሠዊያ ደግሞ አግኝቼአለሁና። እንግዲህ ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን እኔ እነግራችኋለሁ።
24 ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም፤
25 እርሱም ሕይወትንና እስትንፋስን ሁሉንም ለሁሉ ይሰጣልና አንዳች እንደሚጎድለው በሰው እጅ አይገለገልም።
26-27 ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደ ሆነ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፥ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።
28 ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ። እኛ ደግሞ ዘመዶቹ ነንና ብለው እንደ ተናገሩ፥ በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን እንኖርማለን።
29 እንግዲህ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆንን፥ አምላክ በሰው ብልሃትና አሳብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ እንዲመስል እናስብ ዘንድ አይገባንም።
30 እንግዲህ እግዚአብሔር ያለማወቅን ወራት አሳልፎ አሁን በየቦታቸው ንስሐ ይገቡ ዘንድ ሰውን ሁሉ ያዛል፤
31 ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።
32 የሙታንንም ትንሣኤ በሰሙ ጊዜ እኵሌቶቹ አፌዙበት፥ እኵሌቶቹ ግን። ስለዚህ ነገር ሁለተኛ እንሰማሃለን አሉት።
33 እንዲሁም ጳውሎስ ከመካከላቸው ወጣ።
34 አንዳንዶች ወንዶች ግን ተባብረው አመኑ፤ ከእነርሱ ደግሞ በአርዮስፋጎስ ያለው የፍርድ ቤት ፈራጅ ዲዮናስዮስ ደማሪስ የሚሉአትም አንዲት ሴት ሌሎችም ከእነርሱ ጋር ነበሩ። ››
2 ቆሮ.4፡ 3-4 ‹‹ ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳ የተከደነባቸው ለሚጠፉ ነው። ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ። ››
2. በጭንጫ ላይ የተዘራው--
- ቃሉን በደስታ የተቀበሉት ናቸው፡፡ ወዲያው ተቀብለው ወዲያው የሚገለጡ፡፡ ላይ ላይ ስላሌ በቀልቱ ለመውጣት ምንም ጊዜ አይፈጅም፡፡ ከቃሉ የተነሳ መከራ/ስደት ሲመጣ ወዲያው ይሰናከላሉ፡፡
- አነዚህን ሰዎች መሠረታዊ ለውጥ በውስጣቸው አልመጣም፡፡ በእውነትም ጌታን ለመከተል አልወሰኑም፡፡
- የሚከተሉትም ነገሮች እነርሱ በሚፈልጉት መንገድ፣ ለሌላ ችግር በማያጋልጣቸው መልኩ እስከሄደላቸው ብቻ ነው፡፡ ለእነረሱ ምቹ ሆነው እስከተገኙ ብቻ ናቸው፡፡
- ለቃሉ ተብሎ ችግር ብከሰት፣ ለቃሉ መኖር ዋጋ የሚያስከፍል ሁኔታ ውስጥ ሲያስገባ ግን ይተውታል፡፡
-

3. በቁጥቋጦ መካከል የወደቀ-- ቃሉ ለመብቀል፣ ለማደግም ግዚ አግኝቶአል፡፡ ሆኖም ግን ለማፍራት እድል አላገኘም፡፡ ምክንያቱም ‹‹የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፥ የማያፈራም ይሆናል›› እነዚህ ምንድን ናቸው?
a. ‹‹የዚህም ዓለም አሳብና --
b. የባለጠግነት ማታለል --
c. የሌላውም ነገር ምኞት --
4. መልካም መሬት ፍሬ ለማፍራት የተዘጋጄ ነው፡፡ ታርሶአል፣ ጥልቀት አለው/ስር ያስሰድዳል፣ ታርሞአል --ለዘሩ ብቻ አመቺ ሁኔታ ተፈጥሮአል፡፡
በአጠቃላይ፣ የሚያስፈልገው ነገር መሬቱን (ልባችንን) ለእግዚአብሄር ቃል (ዘር) ማዘጋጀት ነው፡፡ ያልታረሰው ይታረስ፣ ጉቶዎች ይነቀሉ፣ መሬቱ ይለስልስ፡፡

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?