Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት
ከኢየሱስ በመማር ፡ በምህረት ክልል ውስጥ ራስህን ጠብቅ፡፡


ማብራቱን በመቅረዙ ላይ አኑሩት
ማር. 4፡ 21-25
ባለፈው ጊዜ (በ28 .10.2015) ኢየሱስ መልካ መሬት የተዘራበትን ዘር እንደሚያበቅልና ትርፋማ እንደሚሆን እንዲሁ ደግሞ የእግዚአብሄር ቃልን የተቀበለና በጊዜያዊ ነገር ሳይታለል እስከመጨረሻ የሚጠብቀው ፍሬ እንደሚያፈራ ነግሮናል፡፡
እኛ ፍሬ ስናፈራ የሰማዩ አባት እግዚአብሄር እንሚከብር ጌታችን ኢየሱስ ተናግሮአል፡፡
የዛሬውም ክፍል ከማምፃለፈው ገር ይያያዛል፡፡
የጽድቅ ጸፅኖ ማምጣት ያስፈልጋል፡፡
በዚህ ያለን ሁላችን፣ በአንድ አላማ በዚህ እንዳለን አስባለሁ፡፡ ይህ ዓላማችን በእግዚአብሄር እይታ ሲታይ ጠቃሚም ጎጂም ሊሆን ይችላል፡፡
ዓላማ መራሽ ሕይወት መኖር ያስፈልጋል፡፡ መብራት የሚበራው ብርሃኑ ስለሚፈለግ ነው፡፡ ስለዚህ መብራት አብርቶ ብርሃኑ በማይታይበት ቦታ ማስቀመጥ ዓላማን መሳት ነው፡፡
ክርስቲያኖች የእግዚብሄር ልጅ ሆነው መገለጣቸው በመልካም ሥራ ሲገለጡና ስለእነርሱ ሰዎች እግዚብሄርን ማክበር ሲችሉ ነው፡፡
ቤተክርስቲያንም ማንነቷ የሚገለጠው በሚታደርገው ነገር ና በሚታጣው ተጽዕኖ አንጂ ቤተክርስቲያን በመባሏ ብቻ አይደለም፡፡
ይህ ሁሉ አንዲሆን ደግሞ ሰዎች በቦታቸው መቀመጥ ወይም ወደ ቦታቸው መመለስ አለባቸው፡፡ ቦታችን የት ነው?
ቁ.21 ላይ ‹‹መብራትን በመቅረዝ ላይ ያኖሩታል›› አለ ኢየሱስ፡፡
በአንድ ቤት ውስጥ አልጋም፣ እቅብም፣ መብራትም፣መቅረዝም ያስፈልጋሉ፡፡ ቢሆኑም ግን ሁሉም በየቦታቸውና ለተሰሩበት ዓላማ ሲውሉ ቤቱን ያሳምራሉ፡፡
ያለቦታው የተቀመጠ መብራትም ቢሆን እንኳ ተገቢውን ጥቅም መስጠት ስለማይችል ውጤታማ አይሆንም፡፡
ጌታ ኢየሱስ ይህንን ያስተማረው የተዘራው ቃል ፍሬ ማፍራት አለበተ ብሎ ካስተማሬ በሃላ ነበር፡፡
- የተዘራው ዘር ማፍራት እንዲችል የመሬት ዝግጅት እንደሚያስፈልግ ሁሉ፣ ልባችን የእግዚአብሄርን ቃል ለመስማት ከተዘጋጄ አኛም ማፍራት እንችላለን፡፡
- ፍሬ ሲኖረን ደግሞ እግዚአብሄር ይከብራል፡፡
o ምን ዓይነት ፍሬ ማፍራት ይጠበቅብናል?
ፍሬ ማፍራት ማለት ማምጣት ያለብንን በጎ ተጽኖ ማምጣት መቻል ነው፡፡ ያ ሊሆን የሚችለው ሁሉም በቦታው ሲሆን ነው፡፡
መቼ ነው መብራት ያለቦው የሚቀመጠው?
- እንዳያበራ በሚፈለግበት ጊዜ
- ነገሮች አንዲሰወሩ በሚፈለጉበት ጊዜ ማለት ነው፡፡
ጌታ ኢየሱስ ደግሞ የተሰወረ/ተሰውሮ የሚቀር ምንም ነገር የለም፡፡ ቢኖር አንኳ ጊዜ ጠብቆ አንዲገለጥ ተፈልጎ ነው እንጂ ተሰውሮ እንዲቀር አይደለም፡፡
- በሕይወታችን ውስጥ የተደበቀ ነገር ምን አለ?
o የልባችን ሓሳብ
o እግዚአብሄር እያንዳንዱን ሓሳብ ይመረምራል፡፡ ወደ ብርሃንም ያመጣዋል፡፡
- ይህ አይነቱ ትምህርት ለሰዎች ጆሮ ደስ ስለማይለው ሰዎች መስማት እንደማይወዱት ኢየሱስ አውቆአል፡፡ ስለሆነም፣ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ ብሎ አስጠነቀቀ፡፡
o ይስማ--- ይቀበል፣ ይጠብቀው፣ ያድርገው
ሰው መስማትና መማር ከፈለገ፣ በዙሪያው ያሉ ነገሮች ሁሉ ሊያስተምሩ የሚችሉ መንፈሳዊ እውነቶች አሉአቸው፡፡
ወደ መስማት ስመጣ ደግሞ ሰዎች ለሚንሰማው ነገር ጥንቃቀ እንድናደርግ ይመክራል፡፡
- መልካምን ነገር (የእግዚአብሄርን ቃል) መስማት ድነት የሚገኝበት እምነት አንዲኖረን ያደርጋል፡፡
- የሚሰማ ነገር በሰሚውስ ውስጥ ተጽእኖ ያመጣል፡፡
o ሰው የሚሰማውን ለማመን የበለጠ ዕድል ይኖረዋል
o የሰማውን መልሶ ይናገራል
o በሰማውም ነገር ለማጽደቅ ይሞክራል
o በሰማው ነገር ላይ ሆኖ ይፈርደዳል
- ሰዎች በሚመዝኑበት መመዘኛ ራሳቸውም ይመዘናሉ፡፡

የትምህርቱ ጠቅላላ ሓሳብ፣
- ቃሉን ለመናገር ድፍረት ያስፈልጋል፡፡
- በስተመጨረሻ እውነት ያሸንፋል፡፡

መብራት (ኩራዝ) ለመብራት በነዳጅ/ዘይት መሞላት አለበት፤ ከልተሞላ ሊበራ አይችልም፡፡ ከተሞላ ደግሞ ከፍ ብሎ መቀመጥ አለበት፡፡ ክርስቲያኖችም ስለኢየሱስ ክርሰቶስ በዓለም ሊናሳየና እውነቱንም ልንገልጥ ተጠርተናል፡፡ ይህንን ሓላፍነታችን ለመወጣት የእግዚአብሄርን ቃል መስማት (መሞላት) ያስፈልገናል፡፡ አብዝተን ቃሉን ስንሰማ አብልጠን ስለእርሱ መመስከር እንችላለን፡፡
ምን እንድንሰማና እንዴት እንደምንሰማ መጠንቀቅ እንዳለብንም አስተምሮአል፡፡ ከጌታ ሳንሰማ ለሌሎች የጌታን ነገር ማስተላለፍ አንችልም፡፡ ነገሮችን መሸፋፈን ብቻ በቅ አይሆንም ምክንያቱም ጌታ ሁሉንም ነገር ወደ ብርሃን የሚያመጣበት ጊዜ ስላለው፡፡

ዛሬ ብርሃናችንን የመደፍን እንቅብ ምን አለ?
- ፍርሃት?
- ይሉኝታ?
- ስንፍና?
- ራስ ወዳድነት?
- እውቀታችን?
- ክብራችን?
- ሌሎችም?
ወዲያው መገለጥ ሁለም አስፈላጊ ላይሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን አሁን ስላልተገለጠ፣ ተሰውሮ የሚቀር ነገር አይኖርም፡፡

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?