Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት
ከኢየሱስ በመማር ፡ በምህረት ክልል ውስጥ ራስህን ጠብቅ፡፡
ማር. 3፡13-35

13 ወደ ተራራም ወጣ፥ ራሱም የወደዳቸውን ወደ እርሱ ጠራ፥ ወደ እርሱም ሄዱ።
14 ከእርሱም ጋር እንዲኖሩና ለመስበክ እንዲልካቸው፥
15 ድውዮችንም ሊፈውሱ አጋንንትንም ሊያወጡ ሥልጣን ይሆንላቸው ዘንድ አሥራ ሁለት አደረገ፤
16 ስምዖንንም ጴጥሮስ ብሎ ሰየመው፤
17 የዘብዴዎስንም ልጅ ያዕቆብን የያዕቆብንም ወንድም ዮሐንስን ቦአኔርጌስ ብሎ ሰየማቸው፥ የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፤
18 እንድርያስንም ፊልጶስንም በርተሎሜውስንም ማቴዎስንም ቶማስንም የእልፍዮስን ልጅ ያዕቆብንም ታዴዎስንም ቀነናዊውንም ስምዖንን፥
19 አሳልፎ የሰጠውንም የአስቆሮቱን ይሁዳን።
20 ወደ ቤትም መጡ፤ እንጀራም መብላት ስንኳ እስኪሳናቸው ድረስ እንደ ገና ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ።
21 ዘመዶቹም ሰምተው። አበደ ብለዋልና ሊይዙት ወጡ።
22 ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጻፎችም። ብዔል ዜቡል አለበት፤ ደግሞ። በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል ብለው ተናገሩ።
23 እነርሱንም ወደ እርሱ ጠርቶ በምሳሌ አላቸው። ሰይጣን ሰይጣንን ሊያወጣው እንዴት ይችላል?
24 መንግሥትም እርስ በርስዋ ከተለያየች ያች መንግሥት ልትቆም አትችልም፤
25 ቤትም እርስ በርሱ ከተለያየ ያ ቤት ሊቆም አይችልም።
26 ሰይጣንም ራሱን ተቃውሞ ከተለያየ፥ መጨረሻ ይሆንበታል እንጂ ሊቆም አይችልም።
27 ነገር ግን አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃውን ሊበዘብዝ የሚችል የለም፥ ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።
28 እውነት እላችኋለሁ፥ ለሰው ልጆች ኃጢአት ሁሉ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይሰረይላቸዋል፤
29 በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘላለም ኃጢአት ዕዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም።
30 ርኵስ መንፈስ አለበት ይሉ ነበርና።
31 እናቱና ወንድሞቹም መጡ በውጭም ቆመው ወደ እርሱ ልከው አስጠሩት።
32 ብዙ ሰዎችም በዙሪያው ተቀምጠው ነበሩና። እነሆ፥ እናትህ ወንድሞችህም በውጭ ቆመው ይፈልጉሃል አሉት።
33 መልሶም። እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነ ማን ናቸው? አላቸው።
34 በዙሪያው ተቀምጠው ወደ ነበሩትም ተመለከተና። እነሆ እናቴ ወንድሞቼም።
35 የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ ነው እኅቴም እናቴም አለ።

ርኵስ መንፈስ አለበት ይሉ ነበርና።
እናቱና ወንድሞቹም መጡ በውጭም ቆመው ወደ እርሱ ልከው አስጠሩት።
ብዙ ሰዎችም በዙሪያው ተቀምጠው ነበሩና። እነሆ፥ እናትህ ወንድሞችህም በውጭ ቆመው ይፈልጉሃል አሉት።
መልሶም። እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነ ማን ናቸው? አላቸው።
በዙሪያው ተቀምጠው ወደ ነበሩትም ተመለከተና። እነሆ እናቴ ወንድሞቼም።
የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ ነው እኅቴም እናቴም አለ።
በዚህ ክፈል ኢየሱስ ከነበረበት የጌሊላ ባህር ዳር ወደ ላይ/ወደ ተራራማው የገሊላ ክፍል ወጥቶ፣ ይከተሉት ከነበሩት (ሉቃ 6፡12-13) ብዙ ሰዎች መካከል ለሓዋሪያነት አገልግሎ የሚፈልጋቸውን ሰዎች ለይቶ ጠራቸው፡፡
ሓዋሪያው ጳውሎስ ሲጽፍ የተለያዩ አገልግሎቶች አንዳሉ፣ ለአገልግሎቱም የሚጠራው እግዚአብሄር እንደሆነና፣ መንፈሱ ግን አንድ እንዴሆነ ተናግሮአል፡፡
ቁ. 13 ራሱ የወደዳቸውን ወደ እርሱ ጠራ ወደ እርሱም ሄዱ፡፡
ይንን ጥሪና ለጥሪውም የተደረገን ምላሽ ተከትሎ፣ ሹመት/አፖይንትመንት መጣ፡---- ለ12ቱ፡፡ አስራ ሁለት የሆኑበት ምክኒያት ሁሉንም የእስራኤል ወገን ለመወከል ነው፡፡
ለሁለት ምክንያቶች፡
1. ከእርሱ ጋር እንዲሆኑ (ከእርሱ እንዲማሩ፣ እነዲሰለጥኑ)
2. ሂዴው ወንጌልን እንዲሰብኩና አጋንንትን (ክፉ መናፈስትን) እነዲያስወጡ
የእያንዳንዱ ሓዋሪያት ስም ዝርዝር በዚህ ክፍል እናያለን፡፡ በሓላ የእነዚህን ሰዎች ሕይወትና አገልግሎ ስንገመግም፣ ኢየሱስ መአመራረጡ ሙሉ በሙሉ ያልተሳካለት መስሎ ሊታየን ይችላል፡፡ እነይሁዳም እዚያ ምጫ ውስጥ ስለገቡ፡፡ ኢየሱስ ግን ይህንን ጥሪ ከማድረጉ በፊት ከአባቱ ጋር ስብሰባ አድርጎ ነበር፡፡ ከአባቱ ጋር ተነጋግሮ ነበር የወሰነው፡፡ ስለዚህ ፍጹም ልክ የሆነ፣ ምርጫ ተካህዶአል፡፡ እድል ለሁሉም ተሰጥቶአል፡፡ ይሁዳም እድልም ሥራም ነበረው፡፡ የእግዚብሄር ዓላማ በእርሱ መፈጸም ነበረበት፡፡
- በተጠሩት መካከል፣ ከተለያዬ የስራና የአስተሳሰብ አከባቢ የተሰበሰቡ ነበሩ፡፡ በዚያ መካከል፣ አሳ አጥማጆች፣ ገበረዎች፣ ቀራጮች፣ የፖለቲካ ሰዎች(ቀናተኛው ይሁዳ)፣ ሃይማኖተኞች(እንዴ ናትናኤል)፣ ነጋደዎች(እንደ ይሁዳ) ነበሩበት፡፡
- ሕይወታቸው ስመረመሪም አንድ አይነት ባህሪይ የነበራቸው ሰዎች አልነበሩም፡፡ አንዳነዱ ስልጣን ወዳድ፣ አንዳነዱ ገንዘብ ወዳድ፣ አንዳነድ፣ ፈጣን ሌሎች ደግሞ ድምጻቸውም ያልተሰሙ ሰዎች ነበሩ፡፡ ኢየሱስ ለሁሉም ዓይነት ሰው በመንግስቱ ሥራ ውስጥ አድል ሰጥቶአል፡፡
- ሰዎቹ ይለያዩ እነጂ የተጠሩበት አገልግሎት፣ ይህ አድስ ጥሪ፣ ዐላማው አንድ ነው፡፡
o ከጌታ ጋር በመሆን ሌሎችንም ወዴ እርሱ መጥራት ነበረ፡፡ ይህን ጥሪ የሚከለክል ነገር ቢኖር የአጋንንት የሰዎችን ሕይወት መያዝ ነው፡፡ በአጋንንት የተያዜ ሰዎ ለራሱም ሆነ ለእግዚአብሄር እንደሚገባ መኖር አይችልም፡፡ ራሱንና ሌሎችን ከመጉዳትም አይመለስም፡፡ የሚያደርጋቸው ነገሮች ከእርሱ የሕይወት አላማ ገር የሚሄድና የፈለጋቸው ነገሮች አይደሉም፡፡ እርሱን የሚገዛው/ የተቆጣጠረው መንፈስ መጠቀሚያ ስለሚያደርገው፡፡
o እግዚአብሄር ግን ሰውን ሲፈጥር በነጻነት እነዲኖሩ ነበር፡፡ ሰው ግን ከእግዚአብሄር እየራቄ ሲሄድ ራሱን ለማይራራለት ጨካኝ መንፈስ/ ለሰይጣን ይሰጣል፡፡ ሰይጣን ደግሞ ያስጨንቃል፣ ያሰቃያል፣ ወደ ሞትም ይነዳል፡፡ ነገሮቹን ሁሉ ያበላሽታል፡፡ ታስታውሳላችሁ ለግዮን የነበረበትን ሰዉዬ ያን ይህል ቁጥር አጋንንት ተሸክሞ ምንም አልተጠቀመም፡፡ ግን ራሱንና ሉሎችን በሚጎዳበት ሁኔታ ውስጥ ነበረ፡፡ ዛሬም ኢየሱስስን የሕይወታችሁ ጌታ ያላደረጋችሁ፣ ወይ ደግሞ ከጌታ ፍታችሁን ያዞራችሁ ሰዎች በዚህ ካላችሁ አሁን ቶሎ ብላችሁ ምርጫቸሁን እንዲታስተካክሉ እመክራችሃለው፡፡ መጽኃፍ ቅዱስ ሲናገር፣ ሰይጣን ሊሰርቅ፣ ሊያርድና ሊያጠፋ እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፡፡ ይላል፡፡ ጌታ ኢየሱስ ግን ‹‹ሕይወት እንዲሆንላችሁ፣ እንዲበዛላችሁም መጣው›› ቢሎ ነበር የተናገረው፡፡
o እንግዲህ ኢየሱስ ደቄመዛሙርቱን ከማናቸውም ከሕይወት ጎዳና ጠርቶ ለሥራው ሲያዘጋጅ፣ በሁሉም የህይወት ጎዳና ውስጥ ያሉ ሰዎች ሊሳተፉበት የሚገባና በነዚያ የህይወት ጎዳናዎች ውስጥ ያሉ ሰዎችም አንዲደረሱ እንደሚፈልግ ግልጽ ነው፡፡
- የጸሃፍት 85 milees ተጉዘው ወደ ኢየሱስ መምጣት ለመልካም አልነበረም፡፡በሁለት ነገር ከሰሱት፡
1. አጋንንት አለበት
2. አጋንንትን የሚያወጣው በአጋንንት አለቃ ተጠቅሞ ነው፡፡
በማለት ስሙን ሊያጠፉ፣ ሊከሱት፣ ደግሞም ሊያስገድሉት ነው፡፡ ክፉ መንፈስ አለበት ያሉትም እንዴ መንፈሳዊ መሪዎች አጋንንቱን ሊያስወጡለት አስበው ሳይሆን፣ በዚህ አይነት የሚከሰሱ ሰዎች በሞት መቀጣት እንደነበረባቸው ህጉ ስለሚናገር (ዘዳግ.13፡5፤ 18፡20) በቀላሉ ተወግሮ እንዲሞት ለማድረግም ይመስላል፡፡
o በዚህ በማርቆስ ወንጌል ከ2፡1- 3፡6 ድረስ ኢየሱስ ሰለ ሓጢአት ማስተሰረይ፣ ስለሰንበት፣ ስለመጾም ያስተማራቸውን ሁሉ ለመበቀል የሚያስችል ችግር አድርገውታል፡፡ ምናልባት በአከባቢው ያሉ ጸሓፍት ከአቅማችን በላይ ነው ቢለው ኢየሩሳለም ወደአሉት ማስተላለፋቸው አልቀረም፡፡ ወይ ደግሞ የኢየሱስ ሥራና ትምህር ተወርቶ ወደ ኢየሩሳለም ስለደረሰ ፤ ሰዎችም ሁሉ ወደ እርሱ እየመጡ ስለሆኑ፣ ሊያስቆሙት ፈልገው መጡ፡፡
o ወረው በኢየሱስ በተሰቦች አከባቢም ችግር ፈጥሮ ነበር፡፡ እንደ ወረኞቹ ከሆነ፣ ኢየሱስ እንግዳ ነገር እያደረገ፣ እየተናገረ ስላለ፣ ሰዎች ሊያዩት ወደ እርሱ እየመጡ ነው፡፡ እርሱ ደግሞ ለመብላት ሁሉ ጊዜ አልነበረውም፡፡
o ይህ ደግሞ ስጋት ሰለፈጠረባቸው፣ ብዙዎች አብዶአል አሉት፡፡
o ስለዚህ ወዳጆቹ ቀድመው መጡ፣ ሌሎች የሚሉትን ሰምተው ነበርና፣ አእምሮውን እንዴለቀቀ ሰው ቆጠሩት፡፡ በኃላም እናቱና ወንድሞቹ መጡ፡፡
o ይህ ታሪክ በቅፍርናሆም የሆነ ነው፡፡ ይህቺ ከተማ ኢየሱስ ካደገቤት/ቤቴሰቦቹ መሚኖሩበት 40ኪሜ (25miles) ያክል ይርቃል፡፡ ስለዚህ ወላጆቹ ምናልባት ያንን ሁሉ ርቀት ተጉዘው መጥቶ ነበር እርሱን ፍለጋ፡፡

o የሚገርማችሁ፣ ከማናቸውም ሰው ይልቅ፣ ከአወላለዱ ጀምሮ ስለኢየሱስ የምታውቀው ማሪያም ነበረች፡፡ ስለኢየሱስ የሰማችሁ የሚያስገርም ብዙ ነገር ስለነበር፣ በልቧ ይዛ የሚትጠባበቅ ሰው ነበረች፡፡ ዛሬ ግን በሀገሩ የሚወራ፣ የመንደሩም ወረ ሁሉ ገራ ስለአጋባት፣ ከሌሎች የኢየሱስ ወንድሞች ገር እርሱን ፍለጋ መጥታ ትገኛለች፡፡
 አሁን ግን የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማድረግ፣ በእግዚአብሄር ተነድታ አልመጣችም፡፡ በወሬ ደንግጣ፣ ወረኞች የሚሉትን አምና መጣች፡፡ ስለዚህም ኢየሱስ፣ ‹‹የመጣችበትን መንፈስ ላለመቀበል፣ ወደ እርሷ አልሄም፡፡ መፅኻፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ የጠየቀችሁ ሆኖላት እናገኛለን፡፡ በዚህ ቦታ ግን አልተሳካላትም፡፡ ‹‹እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ አንዳች ብንለምን እግዚአብሄር እንደሚሰማን እናውቃለን›› (1ዮሃ.5፡13) በዚያ ሰዓት፣ በዙሪያው የሚቀመጡ፣ በእውነተም ከእርሱ ለመስማትና እርሱ የሚያስተምራቸውንም በሥራ ለማሳየት የተነሱ ምስክን ሰቶችንና ወንዶችን፣እናቴና ወንድሞቼ ናቸው ቢሎ አላቸው፡፡
• አንተ የጌታን ትኩረት ለማግኘት ከፈለክ፣ በእግዚብሄር ፈቃድ ውስጥ ራስህን አስገባ፣ በዚያም ቆይ፡፡
• በልምምድ ብቻ፣ በመላመድ ብቻ፣ በብዙ የአገልግሎት ዘመን ብቻ፣ አብሮ በመወለድ ብቻ የጌታን ትኩረት አናገኝም፡፡
• ፈቃዱን ለማወቅና ለማድረግ ወስነው እግሩ ስር የተቀመጡ ‹‹ከእርሱ ሩቅ ናቸው›› የሚባሉ ሰዎች ይልቁን ይቀርቡታልና፡፡ ጌታም ለእነርሱ ትኩትን ይሠጣል፡፡
• አንተ ስለጌታህ፣ የትኛውን ታምናለህ? መንፈስ ቅዱስ የተናገረውን፣ መላእክት የመሰከሩለትን፣ መጽሓፍ የሚናገረውን፣ እርሱም የገለጠልህን ነው ወይስ የጠላትን ወሬ ነው? ኢየሱስ በሕይወትህ ምንድን ነው?

- ኢየሱስ በእነዚህ አልተደነቀም፡፡ ነገር ግን ሌላ መረዳት ነበረው፡፡ እርሱን የሚያሳስበው ሌላ ነገር ነበረ፡፡ እነዚህ ሰዎች ወደ ልባቸው መመለስ አለባቸው፡፡ ከእግዚአብሄር ገር መታረቅ አለባቸው፡፡ ልካቸውን አልፈው ነበርና፡፡
o ለዘላለም ወደሚጠየቁበት እዳ እንዳይገቡ መከራቸው፡፡
o መንፈስ ቅዱስን አትስደቡ አላቸው፡፡
o ሰው በጥፋት መንገድ ሲራመድ ባለበት ቢቸኛ መካሪና መላሽ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን ቢሳደብና ቢያሳዝን ማን ከጥፋት ሊያድነው ይችላል?
o ጌታ ኢየሱስ ሲጠመቅ መንፈስ ቅዱስ ለመመስከር መጣና ወረደበት፡፡ ኢየሱስም ከአረገ በኃላ ለመምራት፣ ለማስተማር፣ ማጽናናትና ለመምከር ለማስታወስም፣ መጣ፡፡ እንግድህ ሰው ይህንን ሁሉ ንቆ የሚሄድ ከሆነ፣ እንዴት አድርጎ ምህረት ያገኛል?
o እቅርታ የማይደረግለት ሓጢአት የተባለው-- የቃል ማምለጥ ብቻ አይደለም፡፡ ነገር ግን በኢየሱስ አስተምህሮት መሠረት፣ ‹‹ከልብ የተረፈውን አፍ ይናገራል››፡፡ ስለዚህ የልብ ክህዴትና ጠማማነት እንደዚህ ያሉ ስድቦች ይወጣሉ፡፡ ማቴ 12፡
33 ዛፍ ከፍሬዋ ትታወቃለችና ዛፍዋን መልካም፥ ፍሬዋንም መልካም አድርጉ፥ ወይም ዛፍዋን ክፉ ፍሬዋንም ክፉ አድርጉ።
34 እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።
35 መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።
36 እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤
37 ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ።
• የመንፍስ ቅዱስ አገልግሎት የመጨረሻ እድል አገልግሎት ነው፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት በሃላ የጌታ ደግም ምጽአት ነው፡፡ ሰው ሌላ ሓጢአት ብሰራ መንፈስ ቅዱስ ወቅሶት ንስሓ ይገባል፣ ግን ከመንፈስ ቅዱስ ገር የተጣላ ሰው የንስሃ እድል የለውም፡፡

ትምህርታችን፡
- በመጠላተትና በመገፋት (ስዴትም) ውስጥ አገልግሎት ይቀጥላል
- ጌታ የሚመርጠው በፈቃዱ ነው--ለመልካም ሥራ
- የጥሪ ምክንያት-- መስበክ፤ ነጻ ማውጣት
- መለያየት አቅም ያሳጣል
- እግዚአብሄርን መፍራት ያስፈልጋል፡፡
o በመንፈስ ቅዱስ ላይ ከመናገር ተጠበቁ-
o
- የእግዚብሄርን ፈቃድ ማድረግ ከኢየሱስ ጋር ያቀራርባል፡፡

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?