Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት

ማር 2፡13-22
13 ደግሞም በባሕር አጠገብ ወጣ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡና አስተማራቸው።
14 ሲያልፍም በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረውን የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን አየና። ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው።
15 በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ ብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጡ፤ ብዙ ነበሩ ይከተሉትም ነበር።
16 ጻፎችና ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ። ከቀራ ጮችና ከኃጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድር ነው? አሉ።
17 ኢየሱስም ሰምቶ። ሕመምተኞች እንጂ ብርቱዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም ኃጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው።
ባለፈው ወር ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ስንማር (ቁ 1-12) ካየናቸው ነገሮች መካከል ጥቅቶቹ፣
ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቃሉን ይነግራቸው እንደ ነበር ቁ.2 እነርሱ የመጡት ምን እንደሚሰራ ለማየት፣ ለመከታተል (አገልግሎቱን የሚያስቆሙበት መረጃ ለመፈለግ)፣ ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ወዘተ… ሊሆን ይችላል፣ እርሱ ግን ቃሉን ነገራቸው፡፡ ከመዝሙረ ዳዊት 107:17-21 ስናነብ፣ ‹‹ቃሉን ላከ፣ ፈወሳቸውም›› በማለት ነው፡፡
17 ስለ ዓመፃቸው ሰነፉ፥ ስለ ኃጢአታቸውም ተቸገሩ።
18 ሰውነታቸው መብልን ሁሉ ተጸየፈች፥ ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ።
19 በተጨነቁ ጊዜም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው።
20 ቃሉን ላከ ፈወሳቸውም፥ ከጥፋታቸውም አዳናቸው።
21 ለሰው ልጆች ስላደረገው ተኣምራት ስለ ምሕረቱም እግዚአብሔርን ያመሰግኑ
o የእግዚአብሄር ቃል ስመጣ ለውጥን ማምጣት ከምችል ጉልበት ጋር ነው፡፡
o በተለይ ደግሞ፣ ሰዎች ከራሳቸው ሓሳብ ወጥቶ፣ ለእግዚአብሄር ራሳቸውን ማስረከብና ለመታዘዝ ፈቃደኝነቱ ካሌ፣ ቃሉ መለኮታዊ ጉልበት አለው፡፡ ያነ ቃሉ ከሰሚዎች ጋር የዋሃዳል ማለት ነው፡፡
o ካልሆነ ግን ሳይጠቅመን ይቀርና ለፍርድ ብቻ ይሆናል ‹‹የሰሙት ቃል ከሰሚዎች ጋር በእምነት ስላልተዋሄደ አልጠቀማቸውም ››የሚል በዕብራዊያን 4፡1-2 ላይ ተጽፎአል፡፡
‹‹1 እንግዲህ ወደ ዕረፍቱ ለመግባት ተስፋ ገና ቀርቶልን ከሆነ፥ ምናልባት ከእናንተ ማንም የማይበቃ መስሎ እንዳይታይ እንፍራ።
2 ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛ የምስራች ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም። ››

o በዮሃንስ ወንጌል 6፡ 62-64 ውስጥ ኢየሱስ ሲናገር ‹‹የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው›› ብሎአል፣
‹‹እንግዲህ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደ ነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት ይሆናል? ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።ነገር ግን ከእናንተ የማያምኑ አሉ። ኢየሱስ የማያምኑት እነማን እንደ ሆኑ አሳልፎ የሚሰጠውም ማን እንደ ሆነ ከመጀመሪያ ያውቅ ነበርና።ብሎአል፡፡
በምዕ. 15 ወስጥ ደግሞ ‹‹ከነገርኩአችሁ ቃል የተነሳ ንጹኻን ናችሁ›› አላቸው፣ ቃሉን በእምነት ካልተቀበለውና ልቡን በሌላ (በክህዴት) ላይ ካሰረው ከይሁዳ በስተቀር ሁሉም ተጠቃሚዎች እንዴሆኑ ከወንጌሉ እናነባለን፡፡
-
- ጌታ የሰዎችን እምነትን እንደሚያከብር ነበር ያየነው፡፡ የታመኑበትን አያሳፍርም፡፡ ቁ.5
- ሰው ከኃጢአቱ እንዲላቀቅ እንደሚፈልግ፡፡ ምህረትንም ያደርጋል፡፡
- ከእግዚአብሄር ጋር አንድ የሚያደርገውን ሥራ መስራቱን አሳይቶአል--በሰዎች ልብ ያለውን በመግለጥ፣ ይቅርም በማለት፡፡
- ኢየሱስ ሁሌ መቅደም ያለበትን እንደሚያስቀድም፡፡ ያንን ዓይነቱን ነገር እንድንለማመድም መከረን ፡-
 ‹‹በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፥ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ።ማቴ5፡25
 ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴ.6፡33
 … አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ። ማቴ.7፡5
 ወይስ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል። ማቴ.12:29
 ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን። እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ አለ። ማቴ.13:30
 እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ። አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፥ ውጭው ደግሞ ጥሩ እንዲሆን አስቀድመህ የጽዋውንና የወጭቱን ውስጡን አጥራ። 23:25-26
 አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል። ማር . 3፥10
 ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር። አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው። ሉቃ . 12:1
 ወይም ሌላውን ንጉሥ በጦርነት ሊጋጠም የሚሄድ፥ ከሁለት እልፍ ጋር የሚመጣበትን በአንድ እልፍ ሊገናኝ የሚችል እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ የማያስብ ንጉሥ ማን ነው? ሉቃ 14፥31

ስለዚህ ኢየሱስ አስቀድሞ ‹‹ኃጢአትህ ተሰረየችልህ›› አለው ከዚያም አልጋህን ተሸክመህ ሂድ›› ሰዎች የተለያዩ ነገሮችን ፍለጋ ሲመጡ እርሱ ደግሞ እነርሱን የሚያስፈልጋቸውን (ቃሉን) አስቀድሞ ይሰጣቸዋል፡፡
- እኛም እግዚአብሄር በሕይወታችን ቅድሚያ እንድሰጠው ለሚፈልገው ለነፍሳችንና ለሌሎ ነፍስ ቅድሚ መስጥት እንዳለብን እንስቼ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ ከመነሳቱ የተነሳ ብዙ ሰው የተለማመደው ‹‹ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል›› የሚለው የኢየሱስ ንግግር መረሳት የለበትም፡፡

ይገኙበታል፡፡

የዛሬውም ክፍል (ማር.2፡13-22) ከባለፈው የቀጠለ ነው፡፡
የታሪኩ ዳራን ስንመለከት
ቦታው፡ በቅፍርናሆም ከተማ አከባቢ ባለው የባህር ዳር የተጀመረ ነበር፡፡ ኢየሱስ ከቤት ወጥቶ ሲሄድ ብዙ ሰዎች እንደገና እርሱ ባለበት ተሰበሰቡ፡፡ እንደ ተለመደው ኢየሱስ ቃሉን ነገራቸው፡፡

በጉዞው ላይ ኢየሱስ ለዊ የተባለውን ማቴዎስን በሥራ ቦታው (ቢሮው፣ የቀረጥ ቦታው) አገነውና ሠራው፡፡
ይህ ጥሪ በተለይም ደግሞ ከጥሪው ቀጥሎ የሆነው ነገር በታወቁ የሃይማኖት መሪዎች እና አንዳንዶች ዘንድ ትልቅ ጥያቄ ፈጥሮ ነበር፡፡

የተሣው ጥያቄ የኢየሱስን ትክክለኛነት ወይም ትምህርቱ ከእግዚብሄር መሆኑን አደጋ ላይ የሚጥል ይመስላል፡፡
ኢየሱስ ግን እነርሱ ባልተገነዘቡት በእግዚአብሄር ቃልና መርሆ ቻሌንጅ አደረጋቸው፡፡ ‹‹ምህረትን እንጂ መስዋእትን አይደለም›› በሚለው የእግዚአብሄር ቃል ነበረ፡፡

- ማቴዎስ ቀረጥ የሚሰበስበው ምናልት ባህር ተሸግራው ወደ ቅፍርናሆም ከተማ ከሚገቡ ነጋደዎች
- የሮማውያን ወኪል ነበረ፣ ጥሩ ስ ራ/ሁለም ገቢ የሚያስገኝ ቋሚ ስራ ነበረው--- ግን ደግሞ በሕዝብ አይወደድም ነበር-- የኢየሱስን ድምጽ ስሰማ ወዲያው ተከተለው፡፡
- ምናልባት፣ በሕይወቱ ውስጥ ያለው ጦርነት ሰልችቶት መውጫ መንገድ አግኝቶ ይሆንን፣ ምናልባትስ የኢየሱስ የጥሪ ድምፅ ጠልቆ ወደ ልቡ ገብቶ ይሆናል
- ግን ኤልሳይ ያደረገው አይነት ውሳኔን ያደረገ ይመስላል፡፡ ሊዩነታቸው፣ ኤልሳይ ላለመመለስ ቆርጦ ሲነሳ፣ ለዊ ደግሞ በመደሰት (ተቀባይነት ስላገኘ) ሳያደርገው አልቀረም፡፡
- ግን ደግሞ ኢየሱስን ወደ ቤቱ ሲጋብዝ መሰሎቹን በብዛት ጋብዞታል፡፡ እርሱን የሚመሰሉና እንደእርሱ የተገለሉ፣ ወደ ቤቱ ተጠርቶአል፡፡
- በጌታ ፍትም ንስሃ ገባ
- ኢየሱስ የሓጢአት ሳይሆን የሃጢአተኛ ወዳጅ ነው፡፡ ይህ ባህሪው ዛሬም አልተለወጠም፡፡
- ሰዎችን ከሓጢአታቸው መሸሽ መጽሓፍ ቅዱሳዊ አይደለም ግን ከሃጢአኝነት ሥራቸው ጋር አለመተባበርና ያንን አለማድረግ እንጂ፡፡
- ከማያምኑት ጋር በማይሆን አካሄድ አትጠመድ ይላል እንጂ ያላመኑትን ሽሽ የሚል አልተጻፈም፡፡ ቢሆንማ ወአ አለም ሁሉ ሂዱ የሚለው ትእዛዝ ትርጉም አይኖረውም ነበር፡፡
ለምን: ሓጢአተኞችን ለመፈለግና ለማዳን መጣ
-
ማን: ኢየሱስ፣ ደቄ መዛሙርቱ፣ ቀራጮች ና ሓጢአተኞች አብሮ ይበሉ ነበር፡፡ ይህ በዚያን ጊዜ በነበሩት የሃይማኖተ ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት የለውም፡፡ ኢየሱስ ግን ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ እንርሱና ደቄ መዛሙረቱ ከሃጢአተኞች ጋር በሉ፡፡ (በሃላ ይህ ችግር አምጥሮአል የሐ.ሥ.11፡3፣ ገላ.2፡12)፡፡ የጌታ ደቄ መዛሙረት ስንሆን ከእርሱ የምንማረው የምስማማንና ሕብረተሰቡ የሚቀበልልንን ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሄር ከእኛ የሚፈልገውን ሁሉ ነው፡፡
ፈርሳዊያንና ሳዱቃውያን ደግሞ አይተው ደቄ መዛሙረትን ጠየቁ፡ት
ባለፈው ጊዜ ካየነውና ዛሬ የምናየውን ታርክ የሚያገናኙ የተወሰኑ ነገሮች አሉ፡-
1. ብዙ ሕዝብ ከበውት ሳሉና እያስተማራቸው እያለ፣ ኢየሱስ ሽባ የነበረውን ሰው ካመጡት ሰዎች እምነት የተነሳ ትኩረት ሰጠው፡፡ በዚህም ክፍል ብዙ ሕዝብ ተከትሎት እያለ፣ የራሱን ስራ መስረታ ላይ የነበረውን ለዊን ትኩረት ሰጠው፡፡
2. በሁለቱም ቦታ በሓጢአተኛነት መፈረጅና መገለል በሰዎች ዘንድ ግልጽ ሆኖ ሲታይ ግን ሁለቱንም ኢየሱስ ይቅር እንዳላቸው በሠራ ገለጠ፡፡ ማቴዎስን ወአ ቤቱ ሂዶ ከእርሱ ጋር መብላተት ወደደ
3. በዚህም ሆነ ባለፈው ባየነው ክፍል፣ ፈርሳዊያንና ሳዱቃውያን ኢየሱስን ከመጠየቅ ይልቅ በልብ ማሳብ፣ እርስ በርስ ማጉረምረም ወይም ደቄ መዛሙረትን መጠቅ የሚመርጡበት ነበረ፡፡ ኢየሱስ ግን ጥያቄዎቻቸውን ባወቀ/በሰማ ጊዜ ቀጥታ ለእነርሱ ተናገራቸው፡፡ ዛሬም አንዲሁ ይናገራል፡፡
4.
ኢየሱስን የሚከተሉት ብዙ ሕዝብ እያለ፣ ኢየሱስ ለዊን ‹‹ተከተለኝ›› አለው፡፡ ይህም ከእኔ ጋር ሂድ ማለቱ ነበር፡፡
እግዚአብሄር ብዙ ጊዜ ሰዎችን ሲጠራ፣ ከዓላማና ከሰውዬው ላይ መስራት በሚፈልገው ነው፡፡ ወንድሞቹ እያሉ፣ ዳዊት ተጠራ፣ ሕዝብ እያሉ፣ ገድኦን ተጠራ፣ ሌሎች እያሉ ማቴዎስም ተጠራ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለእያንነዳዳችን ያለው የእግዚአብሄር ጥሪን መመርመር ጥሩ ነው፡፡ ሰው ስለጠፋ እግዚአብሄር አልጠራንም፡፡ እኛም ደግሞ ከሌሎች ተሸለን ስለተገኘን አይደለም፡፡
ማቴዎስ የመጣለትን ጥሪ ችላ አላለም፤ --በፊቱ ትቆሙና ታጠኑለት ዘንድ ጠርቶአችሃልና ችላ አትበሉ፡፡
በተጠራም ግዜ ጓደኞቹ ላይ ግብዝ መሆን አልፈለገም፣ ግን ወደ ቤቱ መጥተው እንድበሉና የተደረገለትን እንዲያዩ አደረጋቸው፡፡
ፈርሳዊያን ጭፍን ማግለልን ያካሕዱ ነበር፡፡ በህግ ቢመኩም እግዚአብሄር የሚወደውን ግን ፈጽመው አላወቁትም ነበር፡፡
አንዳነድ ግዚ መልካም ያደረግን እየመሰለን እንገበዛለን፡፡ በእውቀታችን ወይም ልምምዳችን ላይ ብቻ ስለምንደገፍ፣ በጊዜው እግዚአብሄር ማድረግ የሚፈልገውን ለመስማትና ለመደገፍ ልቡም ጆሮውም አይኖረንም፡፡
ኢየሱስ የሆነውን አልሆነም አላለም፣ ቀራጩን ማቴዎስ ጻድቅ ነው ብሎ አልተከራከረለትም ነገር ግን ለእርሱ ስል መጥቻለው አለ እንጂ፡፡ የተልኮዬ ዋና ተጠቃሚ ለመሆን መስፈርት ያሟላል አለ እንጂ፡፡
ኢየሱስ ለተጠየቀው ጥያቄ ስመልስ እንደ ዳኛ ሳይሆን ራሱን እንደ ባለመድሃኒት አድረጎ ነበር፡፡
አንድ የሰባኪ ሲናገር፣ ‹‹ለሓኪሞች መፍረድ ይቀላቸው ነበር፣ እኛ ጤናችንን መጠበቅ ስንችል ለበሽታ አጋልጠን ስንሰቃይ ስለሚአዩን፣ ግን እነርሱ መክርንና መድሃንትን ሰጥተው ይለቃሉ፡፡ ዓላማቸው ማዳን መሞከርስለሆነ›› ብሎአል፡፡
እንደ ባለመድሃንት ኢየሱስ ሊረዳቸው የሚችለው እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ለሚያውቁ በራሳቸው ጽድቅ የማይመኩትን ብቻ ነው፡፡
ፈርሳዊያን ጣት ጠቋሚዎች እንጂ ንስሃ መግባት እደሚያስፈልጋቸው አያውቁም ነበር፡፡
ኢየሱስ ግን ባለፈው ባየነው ክፍልም እጅ ዘርግቶ ይጠራቸው ነበር፡፡ እነርሱ ግን ራሳቸውነ ጻድቅ አድርጎ መቁጠርና ሌሎችን ማግለል መቼም አልተውም፡፡
ማቴዎስም ሆነ፣ ሌሎች ስለ ፈርሳዊያንና ጻፎች ጥያቄ መልስ ስሰጡ አታዩም፣ እነርሱ አስቀድሞውኑ አመለካከታቸውን ያውቁ ነበርና (ተቀብለውትማል)፡፡ ይህ ኢየሱስ ኢያደረገ ያለው ነገር አለእነርሱ ራሳው እንግዳ ነው፡፡ ማቴዎስ በደስታ ግብዣ አዘጋጅቶ ኢየሱስን ወአ ቤቴ ወሰደው፤ ይህም ተግባሩ፣ ሉሎች ሓጢአተኞች ስለኢየሱስ የሚሰሙበት፣ በማዕድ ከእርሱ ጋር ተቀምጠው የሚበሉበትን አጋጣሚ ፈጠረላቸው፡፡
አንድ ጊዜ በዚህ ሓገር ከንጉስ በታች ሆኖ ሀገርን የሚያስተዳድር ሰው (ዱክ ኦፍ ክንት) ሊሞት ስቃረብ ሓክሙ ሊያበረታታው ፈልጎ፣ እንቴ እኮ የታወቅና ዝነኛ ሰው ነህ አለው፡፡ ሰዉየው ግን፣ ‹‹አይደለም፣ ተወኝ፣ መዳን ካለብኝ እንደ ዋጋ ሳይሆን እንደ ሓጢአተኛ ነው›› አለው ይባላል፡፤

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?