Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት

ኢሳ.52፡1-2

ሰባለፉት መጨሻዎቹ ሁለት ክፍሌ ጊዜያት ስለኢየሱስ ስናጠና፣ ስለእርሱ ሥራና ንግግር በሚቃወሙት ዘንድ ጥያቄ ሲያስነሳ እንደነበር አይተን ነበር፡፡
በተለይ ‹‹ሓጢአትህ ተሰረየልህ›› ባለውና ‹‹ወደ ማቴዎስ ቤት ገብቶ ከሓጢአተኞች ጋር መብላቱ›› በፈርሳዊያንን ጻሓፍት ዘንድ ትለቅ ችግር ፈጥሮ ነበር፡፡
ኢየሱስ ግን የሚያደርገውንና የምናገረውን ሁሉ በትክክል ያውቅ ስለነበርና እነርሱ ሊቃሙት በማይችሉ መልኩ ስለተናገራቸው፣ አሁንም በሌላ መንገድ ስለእርሱ አስተምህሮት ጥናት/ግምገማ እየተደረገ ያለ ይመስላል፡፡
ዛሬ በምናየው ክፍል ደግሞ ኢየሱስ በደቄ መዛሙርቱ ሃይማኖተኝነት ላይ በተደረገ ጥያቄ ዙሪያ ያውጠነጥናል፡፡
ማር 2፡18-22
18 የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና ፈሪሳውያን ይጦሙ ነበር። መጥተውም። የዮሐንስና የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት የሚጦሙት የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው? አሉት።
19 ኢየሱስም አላቸው። ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎች ሊጦሙ ይችላሉን? ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊጦሙ አይችሉም።
20 ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ወራትም ይጦማሉ።
21 በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚጥፍ የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አዲሱ መጣፊያ አሮጌውን ይቦጭቀዋል፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።
22 በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል የወይኑም ጠጅ ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ።
በግዜው፡ ፈርሳዊያንና የዮሃንስ ደቀ መዛሙርት ይጾሙ ነበር፡፡
የህንን በማድረጋቻቸው የጋራ የሆነ ልምምድ ስለነበራቸው፣ ከእነርሱ ሌየት ያለ ነገር ይዘው የተገለጡትን የኢየሱስን ደቀ መዛሙርት በተመለከቱ ጊዜ አልተደሰቱም፡፡
ስለዚህ ነገር ደግሞ መጠየቅ ያለበት ኢየሱስ ራሱ እነደሆነ አስበው ወደ እርሱ መጡና ጠየቁት፡፡
ለምን ኢየሱስ ተጠየቀ? ደቀ መዛሙርቱ ያልተጠየቁት ለምንድን ነው?
ምናልባት፣ እንደ ሌሎቹ አስተማሪዎችና ፈሪሳዊያን፣ ደቀ መዛሙረቱ እንዲጾሙ ያላስተማራቸው/ጫና ያላደረገባቸው እርሱ እንደ ሆነ ስለሚታመን ነው፡፡
ደቀ መዛሙርቱ በራሳቸው ስልጣንና ፍልስፊና ቢያደርጉት ኖሮ ራሳቸው ተጠያቂ ይሆኑ ነበር፣ አሁን ግን በራሳቸው መንገድ ሳይሆን ኢየሱስን እየተከተሉት ስለሆኑ፣ ስነእነርሱ እርሱ ሓላፊነቱን ወስዶ ነበር፡፡
ጌታንና ትምህርቱን ስንከተል፣ እርሱ ራሱ ስለእኛ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል፡፡
‹‹የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማየጦሙት ስለምነድን ነው?
ኢየሱስ የእነርሱን ጥያቄ ለመመለስ በጣም መንፈሳዊ ወይም ሰማያዊ የሆነውነ ነገር አልነገራቸውም፡፡ ነገር ግን ለጥያቄአቸው መልስ ማግኘት እንዲችሉ፣ እነርሱ በባህላቸው ውስጥ የሚያውቁትን ምሳሌ ነገራቸው፡፡
በወቅቱ በነበረው የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት/ባህል ውስጥ የነበረው አንዱ ኤሌመንት ይህንን ነገር ያስረዳል፡፡ ጋቢቻ ሲካሄድ በተከታታይ ለ7 ቀናት ግብዣ እንደሚደረግ (እንደሚደገስ) ይነገራል፡፡ በዚያን ወቅት እግዶች/ሚዘዎችም እድራቡ፣ እንዲያዝኑ፣ በሌላ ስራም እንዲጠመዱ አይፈቀድም ነበር፡፡ ስለዚህ ፆምም አይታሰብም ነበር፡፡
ምዜዎች ሙሽራው እስኪመጣ ድረስ ምግብ ከመብላት ራሳቸውን ከልክለው፣ የሙሽራውን መምጣት ይጠባበቃሉ፡፡
ልክ ከሙሽራው ጋር ሲሆኑ፣ መጾማቸው ያበቃና ከእርሱ ጋር መብላት መጠጣት ይጀምራሉ፡፡
ሙሽራው(ኢየሱስ) ሲወሰድባቸው (ሲሰቀል) ግን ማዘንና መጾም የግዱን ይመጣል፡፡
ከዚህ የኢየሱስ አገላለጽ ነገር ሁለትነገሮችን መገንዘብ እንችላለን፡፡
1. በጥያቄ ተወጥረው ወደ እርሱ ለመጡት ሰዎች፣ እነርሱን ሊገባቸው በሚችል መልኩ ይናገራቸው ነበር፡፡ (በሽተኛ ብቻ ሃክምን እንደሚፈልግ፣ በድግስ መካከል ሆኖ ጾም እንደማይታወጅ፣…)

እኛም ሌሎች ላላቸው ጥያቄና ችግር መልስ ለመስጠት ስናስብ ነገሮችን ከማወሳሰብና መንፈሳዊ ብቻ ከማድረግ ይልቅ የምገባቸውን አገላለጽ መፈለግ ይጠቅመናል፡፡

2. ይህንን የሰዎች ጥያቄ ተጠቅሞ፣ ለአይምሮ እውቀት ብቻ የሚጠቅማቸውን ሳይሆን ለሕይወት ለውጥ የሚጠቅማቸውን ይነግራቸው ነበር፡፡ (እውነተኛ ለውጥ እንደሚያስፈልግ) የነገሮችን ስም ቀይሮ ብቻ አሮገውንና አድሱን መቀላቀል መሞከር ሁለቱንም ነገሮች እንደሚያበለሽ ኢየሱስ ጨምሮ ነገራቸው፡፡

ያም ማለት፣ ለነገሮች ሁሉ የሚገባቸውን ሥፍራ መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ማወቅ አስፈላጊ ነው ማለቱ ነው፡፡ አድስን በአድስነት፣ አሮገን ነገር ደግሞ አንደዚያው በአሮገነቱ ሊደረግለት የሚገባውን ካላገኘ፣ አድሱም ሆነ አሮገው ሊንጠቀምባቸውን የምንችለውን ጥቅም እንዳናገኝ ያደረገናል፡፡

3. በዚህ ክፍል ኢየሱስ አብሮ ስለማድረግ /ስለኮምፓተብሊቲ እንጂ ስለ አንዱ ከሌላው መሻል አልነበረም የተናገረው፡፡ ዋናው ግን የሰውን ወግና የእግዚአብሄርን አሠራር ለይቶ ማየት ነው፡፡ ኢየሱስ ምሳሌ የሚያሳየው፣ የአይውድን ሃይማኖታዊ አሠራርና ኢየሱስ ያመጣውን የአድስ ክዳን ትምህርት መቀላቀል መሞከር በአሮገው ላይ አድስን የመስፋት ያክል ነው፡፡

ኢየሱስ አድስ ሕይወት ለሙታን ይዞ መጥቶአል፡፡ ይህ ሕይወት ደግሞ በራሱ ሊቆም የሚገባው አይነት ነው፡፡
ሉቃ.22፡19-20
19 እንጀራንም አንሥቶ አመሰገነ ቆርሶም ሰጣቸውና። ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ።
20 እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ፦ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።
ዕብራ.8፡13
አዲስ በማለቱ ፊተኛውን አስረጅቶአል፤ አሮጌና ውራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቦአል።

እኛ በእግዚአብሄር ቤት ሰንሆነ፣ እውነተኛ ና መሠረታዊ ለውጥን ለመቀበል እንፈልጋለን?


አድስ ኪዳንን ስናነብ ስለ ለውጥ ምን ይመክረናል

2ቆሮ. 5፡17 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።

ገላ. 6፡15 በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።

ኤፌ. 4፡ 17-32
17 እንግዲህ አሕዛብ ደግሞ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ በጌታም ሆኜ እመሰክራለሁ።
18 እነርሱ ባለማወቃቸው ጠንቅ በልባቸውም ደንዳንነት ጠንቅ ልቡናቸው ጨለመ፥ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ራቁ፤
19 ደንዝዘውም በመመኘት ርኵሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ።
20 እናንተ ግን ክርስቶስን እንደዚህ አልተማራችሁም፤
21 በእርግጥ ሰምታችሁታልና፥ እውነትም በኢየሱስ እንዳለ በእርሱ ተምራችኋል፤
22 ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥
23 በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥
24 ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።
25 ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ።
26 ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤
27 በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።
28 የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።
29 ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ።
30 ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።
31 መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።
32 እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።

 

ሮሜ. 13፡ 11-14
11 ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።
12 ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ።
13 በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤
14 ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ።

1ጴጥ. 2፡2-3
ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።

ራእይ 21፡5
በዙፋንም የተቀመጠው። እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ። ለእኔም። እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ አለኝ።

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?