Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት
ማር 2፡ 23-28
23 በሰንበትም በእርሻ መካከል ሲያልፍ ደቀ መዛሙርቱ እየሄዱ እሸት ይቀጥፉ ጀመር።
24 ፈሪሳውያንም። እነሆ፥ በሰንበት ያልተፈቀደውን ስለ ምን ያደርጋሉ? አሉት።
25 እርሱም፦ ዳዊት ባስፈለገውና በተራበ ጊዜ፥ እርሱ አብረውት ከነበሩት ጋር ያደረገውን፥ አብያተር ሊቀ ካህናት በነበረ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ፥
26 ከካህናት በቀር መብላት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደ ሰጣቸው ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው።
27 ደግሞ። ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤
28 እንዲሁም የሰው ልጅ ለሰንበት እንኳ ጌታዋ ነው አላቸው።

እለቱ፡ -የሰንበት ቀን ነበር
- ሁኔታ፡ ኢየሱስ ከደቄመዛሙርቱ ጋር ይሄድ ነበር፡፡

- ደቄ መዛሙርት ተርበዋል፡፡
o ከጌታ ጋር እያለን መራብ ይቻላል?
o በሰዎች ሁሉ ላይ የምደርስ ሁሉ ሊደርስብን ይችላል፣

- ግን እግዚአብሄር የመውጫ መንገድን ያዘጋጃል፡፡
o በተራቡበት ጊዜ በስንዴ ማሳ ውስጥ ተመሩ፡፡
o እግዚአብሄር እረኛዬ ነው፡፡ በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፣ ወደ እረፍወት ውሃ ዘንድም ይመራኛል፡፡ (ይህ አይነት ሁኔታ የሚያስደስተው፣ ተርቦ፣ ተጠምቶ፣ ደክሞትና እረፍት ፈልጎ ለነበረ ሰው ነው)
በዚህ እውነተኛ ታርክ የሆነው ነገር በተልእኮ ላይ ባሉ ያሉ ሰዎችን በተመለከተ የተናሳ ጥያቄ ነበር፡፡
ኢየሱስና ደቄ መዛሙርቱ በጥዋት ወደ አገልግሎት/እምልኮ እየሄዱ ነበር፡፡ ምንልባት የሚሄዱበት ቦታ ሩቅ ስለነበር ቀድመው ተነስተዋል፣ ወይ ደግሞ በማናቸውም ምክንያት ቁርስ ሳይበሉ ካደሩበት ቤት ወጥተዋል ወይ ደግሞ ምሳ ሳይበሉ ቆይቶአል፡፡ በመሆኑም በጣም ተርበዋል፡፡
ኢሱስ በአንድ የስንዴ ማሳ አሳለፋቸው፡፡
ሆኖም ግን በዚህን ጊዜ ኢየሱስና ደቄ መዛሙርቱ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም ሰዎች ነበሩ፡፡ የሚያዩአቸውና የምታዘቡአበቸው፣ የሚከታተሉአቸውና የሚጠይቁአቸው በአከባቢአቸው ነበሩ፡፡
ዛሬም ቢሆን ስናመልክም ሆነ ስናገለግል ብቻችንን እንዳልሆንን ማወቁ ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡ ከእኛ ጋር ያልሆኑ ግን በአከባቢአችን ሆነው የሚያዩ ሰዎች አሉ፡፡ ሰዎች አምልኮኣችንና አገልግሎታችን በእነርሱ ዘንድ ቀተባይነት ባያገኝ እንኳ በምናደርገውና በሚኖረው ኑሮ ላይ ጥያቄ መጠየቃቸው አይቀርም፡፡
ስለዚህም መጽሓፍ ቅዱስ እንዴት መመላለስ እንዴምገባን ይመክረናል ፡፡
‹‹ መልካሙን ሥራችሁን አይተው የሰማዩን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ሁሉ ፍት ይብራ፡፡›› ማቴ.5፡16
‹‹ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ከፊት ይልቅ ልትበዙ፥ በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቀቁ፥ እንዳዘዝናችሁም፥ በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን። 1ተሰ. 4፡10-12
በውጭ ባሉት-- የሚለውን ቃል ከመንግስቱ ውጭ እንደሆነ ብናየው መልካም ነው፡፡
እንግዲህ ዛሬ በምናየው ታርክ ውስጥ ስለህገወጥነት ነበር የተጠየቀው ጥያቄ፡፡ ከሰንበት ጋር በተያያዘ ሕግን ስለመተላለፍ ነበር ኢየሱስ የተጠየቀው፡፡
ሰንበት ማለት-- ሰዎች እንዲያርፉበትና ከእግዚአብሄር ጋር ጊዜ እንዲወስዱ ለሰዎች የተሰጠ ህግ ነው፡፡ ስለዚህ በሰንበት አድካሚ ስራን መስራትን ህግ ይከለክላል፡፡ ከአስርቱም ትእዛዛት አንዱ ይህ ነው፡፡
ዘጸ.20፡10
‹‹ 8 የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ። 9 ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ 10 ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ 11 እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም።››
በእርግጥ የእግዚአብሄር ህግ ክብር የሚገባውና መጠበቅ አለበት፡፡ ፈርሳዊያኑም ከዚህ የተነሳ፣ ሕግን በአግባቡ ለመጠበቅ እንዲያስችላው፣ ከሚመጣውም ቅጣት ለማምለጥ ተጨማሪ ሰው ሰራሽ ስርዓቶችንም ጨማምረው አብዝተውታል፡፡
ሆኖም ግን ችግሩ ሕግም ኖሮ፣ ተጨማሪ ህግም ወጥቶ፣ የሰው ልብ ካልተለወጠና እግዚአብሄርን መፈለግ ከለሌ፣ ከእግዚአብሄር ጋር እየተያዩ መተላለፍ ይመጣል፡፡ እግዚአብሄር ይርዳን!
ለዚህም ነው የህጉ ባለበት፣ ሕጉ የሚፈጸምበትንና ሰዎችም በእርሱ ጸጋ ሊጸድቁበት የሚችሉበትን መንገድ የገለጠው፡፡ ሰዎቹ ግን ኢየሱስን አላወቁትም ነበር፡፡
እኛም ዛሬ ብዙ ሓይማኖታዊ ሥርኣቶችን እየፈጸምንና እያስፈጸምን ከጌታ ጋር ላንተዋወቅ እንችላለን፡፡ ሰው ጌታን ካላወቄ፣ መልካም እየመሰለው ጌታንና መንገዱን ያሳድዳል፡፡ ልክ ሳውል የተባለው ጳውሎስ ሲያደርግ እንዴ ነበር ማለት ነው፡፡ እርሱ ከእነዚሁ ከፈርሳውያን አንዱ ነበርና፡፡
እንግዲህ ሙሉ ስእሉን ለመመልከት ብንሞክር፣ የጌታ ደቄ መዛሙርት፣ ድምጹን ሰምተው፣ ያላቸውን ሁሉ ትተው፣ ኢየሱስን እየተከተሉና ከእርሱ እየተማሩ ያሉ ሰዎች ናቸው፡፡
በአጭሩ ብናስቀምጠው በተልእኮ ላይ ያሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ፍጹማን ደግሞ አይደሉም፡፡ እንደማናችም ለሰው የሚያስፈልገው ሁሉ ያስፈልጋቸው ነበር፡፡ ስለዚህም ስራቡ፣ በማሳ በኩል እያለፉ ስለነበር፣ እሸት ቀጥፈው በሉ፡፡
ያንን የተመለከቱ ወግ አጥባቂዎች፣ በኢየሱስና በትምሀርቱ ላይ ጥያቄ አነሱ፡፡ ስለደቄመዛሙርቱ ባህሪይ ኢየሱስን ተጠያቂ አደረጉት፡፡
በዚህም ክፍል፣ ደቄ መዛሙርቱ ስለራሳቸው ምንም መልስ እንደ ሰጡ አናይም፡፡ ለምን?
- ምናልባት ጥፋተኝነታቸውን አምነውበት፣ አሁንስ ተያዝን ማለታቸው አልቀረም፡፡
- ወይ ደግሞ፣ ይንን መመለስ ብንሞክር በድንጋይ ተወግረን መሞት ስለመንችል ዝምታው ይበጃም ብለው ይሆናል፣
- ወይ ደግሞ፣ ኢየሱስ ራሱ ይህንን ነገር ምን ማለት እንደምችል ጠብቀውታል፡፡
ሁኔታቸው ምንም ብሆን፣ ኢየሱስ ግን ጣልቃ ገብቶላቸዋል፡፡
ኢየሱስ ስመልስ፣ እነርሱ ያደረጉት ነገር ሕግ መተላለፍ አይደለም ብሎ ክርክር አልጀመረም፡፡ ነገርን በግልጽና በጥበብ ነበር የመለሰላቸው፡፡ እነርሱ ሁሉ የምያውቁትናና የሚወሩትን ታርክ ተጠቀሜ፡፡ ዳዊት ስላደረገው ነገር (1ሳሙ 21)፡፡
ግን ደግሞ ‹‹አላነበባችሁምን?›› በምል ጥያቄ ጀመረላቸው፡፡ ይህንን አይነት ነገር ኢየሱስ ብዙ ጊዜ ተጠቅሞአል (ማቴ 19፡4፣21፡16፣42፤22፡31 ማር.12፡10፣26፣ሉቃ10፡26)፡፡
ይህ ማለት፣ መጽሓፍ ቅዱሳችንን ማንበብ ለብዙ ጥያቄዎቻችን ተገቢውን ምላሽ እንድናገኝ ያደርገናል ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም፣ በቃሉ ላይ የሚናነበው ነገር ሊንጠቀምበት የምንችል ሕያው ቃል እንጂ ስርኣትን ለመፈጸም የምናነበንበው ነገር እንዳልሆነም ይጠቁማል፡፡
ዳዊት ፡- ለንግስና ተቀብቶ ነበር፡፡ ሰኦል ግን ሊገድለው ይፈል ስለነበር ዳዊት ሸሼ፡፡ በዚያን ቀን፣ ወደ ቤተ መቅደስ ሂዶ ለራሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት እንጀራ ለምኖ ነበር፡፡ የሚሰጠው እንጀራ ሲታጣ፣ የተቀደሴ እንጀራ ከካህኑ ተሰጠውና በላ፡፡
ኢየሱስ ይህን ታርክ በማስታወስ፣
- ደቄ መዛሙርቱ እሸቴን የበሉበትን ልዩ ሁኔታ እንዲረዱ ተናገረ፡፡
- ጌታ መቼም ብሆን ስህተትን ትክክል ነው አይልም፣ ደግሞም እንደአየ አይፈርድም፣ ይላል ቃሉ፡፡ ነገር ግን የሚህረትን ያደርጋል፡፡
- ሁኔታውን ልዩ የሚያደርገው
o ለተለየ ተልእኮ ወጥቶአል፤ ሌላ አማራጭ አልነበራቸውም፡፡ እነርሱም ለተለየ ሥራ/አገልግሎት የወጡ ነበሩ፡፡ እንጄራወም ለተለዩ ሰዎች ብቻ ነበር የተፈቀደው፡፡
o ከጌታ ጋር በመስማማት የሚሄዱትና ለእርሱ ራሳቸውን የለዩ ከተቀደሰው ማእዱ ይበላሉ፡፡ ሲያደርጉትም በፍርሃትና በአክብሮት እንጂ በንቀትና በይገባኛል አይደለም፡፡
o ምግቡ በፍጹም መታመን እግዚአብሄርን ለማገልገል ለተለዩ ሰዎች ብቻ ነበር፡፡ እነዚህ ለሁሉም ነገር፣ የእለት ጉርሳቸውን ጨምሮ፣ በእግዚአብሄር ላይ የታመኑ ነበሩ፡፡
o ስትታመነው እርሱ ደግሞ በረሃብ እንድትሞት አይተውህም፡፡ ገበታን ያዘጋጅልሃል፡፡
ሰዎቹ ህግን ለክስ መጠቀም ሲፈልጉ፣ ኢየሱስ ግን ወደ መጀመሪያው እንድመለሱ ያሳስባቸዋል፡፡ (ሕይ የተሰጠበት ምክንያት)፡፡ ሕግ የመጣው ወደ እግዚአብሄር እንድንቀርበበት እንጂ እንድንጠፋበት አልነበረም፡፡ ሰው ግን ከአምላኩ ጋር ካሌ፣ እርሱን የሚከለክል ምንም ህግ አይኖርም፡፡ በነጻነት መኖር ይችላል፡፡
ይንን አይነቱን ሰው የምበዛበት ምንም ነገር አይኖርም፡፡
ወደ ጌታ ከምንቀርበበትና ከብዙ ሕግ ባርነት ከምንወጣበት መንገድ አንዱና ትልቁ፣ ጌታን መስማትና መታዘዝ ነው፡፡ ልክ ደቄ መዛሙርቱ ጥርውን ሰምተው ሁሉንም ትተው እንደ ተከተሉት፡፡
ደጁን ብከፍትልኝ ወደ እርሱ እገባለሁ፣ ከእርሱ ጋር እራት እበላለሁ፡፡

በጎቼ ድምጸን ይሰማሉ፣ ይከተሉኝማል፣ እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፡፡ ዮሃ. 10
ጌታ ከእኛ ጋር ሲኖር ችግሮች ለገጥሙን ብችሉም፣ እርሱ ግን ከሁሉም ያድነናል፡፡
ብቻ ወደ መጀመሪያው የጌታ ሓሳብ መመለስ ብንችል ከማንናውም እስራትና ክስ ነጻ ሆነን ራሳችም ተደስተን ጌታን የሚያስደስት ሕይወት መኖር እንችላለን፡፡
ሰንበት ለሰው እነጂ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም፡፡
ጌታ (ሰንበትን የፈጠረው ጌታ) በሰንበት ላይ ጌታ ነው፡፡
ሕግ አውጪው ትክክለኛውን የሕጉ አስፈላጊነት ስለሚያውቅ፣ አንድን ክስተት በትክክል ካወቄ፣ በማያቀላውል መልኩ ትክክለኛ ብይን ሊሠጥ ይችላል፡፡
ነገሥታት የወታ ህግ በእነርሱ ይሻራል፡፡
እግዚአብሄርስ እንዴታ!

የዘማሪ ጸሎት መዝሙር፡
ስምህን ጠርቶ ማን አፍሮአል ጌታ፣
አንተን ይዞ ወጥቶ ማንስ ተረታ
ክንዴ ብርቱ ነህ ጌታ አምላካችን
ስታግዝ አይተናል በሕይወታችን
ስታጽናነ አይተናል እኛም በአይናችን
ስትሠራ አይተናል በዘመናችን
-


እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?