Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት

አላማ ይዞ የተሰለፈ፣ የሚያስፈራ ያንቴ ሰራዊት፣
ጠላቱን ሁሉ፣ እያሸነፈ፣ በአንቴ መርነት
ቀንና ሌሊት፣
ብለን እንዘምራለን፡፡
ምንም እንኳ መዝሙሩ፣ ስለአማኞች ድል ቢናገርም፣ እውነቱ ግን ያሸፈውና በአሸናፋነት የሚያስከደን፣ ድል ነሽው አምላካችን ነው፡፡ እርሱ ደግሞ በእርሱ በተገኝ ድል ያዞረናል፡፡

መቼም ጦሪነት/ወይም ትግል ሳይኖር ስለድል መናገር የለም፡፡
1 ቆሮ. 2: 14-15
‹‹ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን፤ በሚድኑቱና በሚጠፉቱ ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነንና፤››
ድል በመንሳት ያዞረናል የሚለውም ደግሞ በየደረስንበት ቦታ ሁሉ፣ እኛን የምገዳደር፣ ከእኛ ጋር የሚታገል፣ ጦሪነት የሚከፍትብን ይኖራል ማለት ነው፡፡
ሆኖም ግን ኢየሱስ ራሱ በቃሉና በመንፈሱ ከእኛ ጋር በመሆን ድልን አያቀዳጀን ያመላልሰናል፡፡
አንዳነድ ጊዜ፣ <<የእኔ ፈተና እኮ ባዛ፣ አንዱ ከአንዱ ቀጥሎ መጣ>> እንል ይሆናል፡፡ አዎን እውነትም በትግል ሕይወት ልንኖር እንችላለን፡፡
በዚያ ሁሉ ውስጥ ግን ሳንጠፋ ተርፈን ለዛሬ መድረሳችን፣ ከድል ነሽው እግዚአብሄር የተነሳ ነው፡፡ ይንን ስል፣ ስለ መሰንበታችን ብቻ ኢያልኩ አይደለውም፣ ነገር ግን በእግዚአብሄር ቤት ስለመሰንበታችን እንጂ፡፡ በመስቀሉ ስር፣ በእምነት ሕይወት፣ በዘላለም ሕይወት ጎዳና ላይ ስለመሰንበታችንም ማለት አንጂ፡፡
ማርቆስ 1:32-39
‹‹ፀሐይም ገብቶ በመሸ ጊዜ፥ የታመሙትንና አጋንንት ያደረባቸውን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ ከተማይቱም ሁላ በደጅ ተሰብስባ ነበር። በልዩ ልዩ ደዌም የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፥ ብዙዎችንም አጋንንት አወጣ፥ አጋንንትም ክርስቶስ መሆኑን አውቀው ነበርና ሊናገሩ አልፈቀደላቸውም። ማለዳም ተነሥቶ ገና ሌሊት ሳለ ወጣ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ በዚያ ጸለየ። ስምዖንና ከእርሱ ጋር የነበሩትም ገሥግሠው ተከተሉት፥ ባገኙትም ጊዜ። ሁሉ ይፈልጉሃል አሉት።
እርሱም፦ በዚያ ደግሞ ልሰብክ ወደ ሌላ ስፍራ በቅርብ ወዳሉ መንደሮች እንሂድ ስለዚህ ወጥቻለሁና አላቸው። በምኵራባቸውም እየሰበከ አጋንንትንም እያወጣ ወደ ገሊላ ሁሉ መጣ። ››
ኢየሱስ በዚህ ምድር ድል ካገኘባቸው ነገሮች አንዱ፣ ከዓላማው አለመሳቱ ነው፡፡ ይህንን ደግሞ፣ የራሱ ኣላማ ስለ ሆነ ብቻ ሳይሆን፣ ከአባቱ አላማ ጋር መተባበሩን እያረጋገጠና፣ እየመሰከረ ነበር የኖረው፣ ያደገው፣ ያገለገለው፣ የሞተውና የተነሳው፣ ወደ ሰማይም የወጣው፡፡ እርሱ ራሱ ሲናገር፣ ‹‹ለዚህ ደግሞ መጣው›› ይላል፡፡ ለምን? ስከትን ለማግኘት ሳይሆን፣ ፈቃዱን ለማድረግ፡፡
እኔና እናንቴ፣ ብዙ ጊዜ የምንቸገረው እዚህ ላይ ይመስለኛል፡፡ በተለይ ስከት የምመስልን ነገር፣ ትቶ ማለፍ አንችልም፡፡ ያንን ደግሞ፣ የምናደርገው፣ አጥርተን እግዚብሄር የሚፈልገው ምንድን ነው የሚለውን ባለማወቃችን ና እርሱን ራሱ ባለማወቃችን ይመስለኛል፡፡
ዛሬ ከእየሱስ ሕይወት የምንማረው፣ ይህንን ነው፡፡
በለፈው ክፍለ-ጊዜ ስለ ኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ስንመለከት፣ ጌታን ስለመከተል አይተን ነበር፡፡ ጌታ ሲጠራ አስቀድሞ ለማዳን ከዚያም ሌሎች ወደ ማዳኑ እንድመጡ እንድናደርግ ለተልዕኮ እንደሆነም አይተናል፡፡ ‹‹ተከተሉኝ ሰዎችን የምታጠምዱ አደርጋችኃለሁ›› እያለ ሲጠራ ፡፡
አንድ ሰው ወንጌል ሲመሰከርለት ሁለት አማራጮች ይቀርቡለታል፡፡ ሞትና ሕይወት፡፡ መስካሪውም፣ ሕይወት እንድትመረጥ መረጃ ለመስጠት ይጥራል፡፡ በእርምጃ ደረጃ፣ ወንጌል የሚመሰከርለት ሰው የራሱን ውሳኔ ያደርጋል፡፡
ምሳሌ፡ ስለ አንድ የተሰበረ ድልድይ መረጃ ያለው/ያየው ሰው በመንገድ ላይ ቆሞ ሌሎች በድልድዩ እዳይሄዱ ሊነግራቸው ይሞክራል፡፡ ይህ ሰው ማንንም እንዳይሄድ የመከልከል አቅም የለውም፡፡ ብቻ ጽፎ እየለጠፈ፣ እጅ እያወራጨ፣ ጮክ ብሎ እየተናገረ፣ ‹‹ድልድዩ ሰባራ ነው፣ ብትሄዱበት ሞት አለ›› ይላል፡፡ እንዳንዱ መኪናውን ቀዝቀዝ አድርጎ ይሰማውና መኪናውን አዙሮ በሌላ መንገድ ይሄዳል፡፡ ሌላው ደግሞ፣ በመረጃው እውነተኝነትን ስለሚጠራጠር፣ ትንሽ ጠጋ ቢሎ አይቶ/ሌሎችንም ጠይቆ ጨማሪ መረጃ ካገኘ በሃላ ይመለሳል፡፡ አብዛኛው ግን፣ ተናጋሪውንም ተጨማሪ መረጃ ሠጭዎችንም ንቆ ይሄድና፣ ራሱን በሰባ ድልይ ላይ ያኖራ፣ ላይመለስና መንገዱን ላያስተካክም ለዘላለም ይሄዳታል፡፡
ስለዚህ ኢየሱስ፣ እንዲከተሉት ለጠራቸው አማኞች፣ ‹‹ሰዎችን ከዘላለም ሞት እንድታስተርፉ አደርጋቸችሁለሁ፡፡›› ይላል፡፡ ባለፈውም እንዳየነው፣ እኛ ራሳችን ሰዎኝ አስተራፊዎች ልንሆን አንችልም፡፡ ነገር ግን እኛ ፈቅደን ኢየሱስን ከተከተልን፣ እርሱ ራሱ ‹‹አጥማጆች›› ያደርገናል፡፡ ያኔ አብረን የጠየቅነው ጥያቄ፣ ‹እኔ የሰዎ አጥማጆች ተደርገአለሁ ወይ?›› የምትለዋን ነገር ነው፡፡
መልሳችን ‹‹አዎን እኔ ተደርገአለሁ›› የሚል ከሆነ፣ ተልእኮውን እየተወጣን ስለሆነ፣ የድል አክልል እንደሚጠብቀን ከወድው እኔግራቸሃለሁ፡፡ መልሳችን ግን ‹‹አይ ገና አልሆንኩም›› ከሆኔ፣ እርሱን እየተከተልን መኖራችንን መፈተሽ እንደሚያስፈልገን ተናግሬ ነበር፡፡
በተጨማሪም አንድ በቤተ/ያን የሚደረገው አገልግሎት ሰዎችን ወደ እግዚአብሄር መንግስት ማምጣት ነው አንጂ አንድ ሃይማኖታዊ ቢሮ ይዞ መቀመጥ እንዳልሆነ፣ ተነጋግረናል፡፡
ምስክትነት ስጦታይ አይደለም ማለት ልክ አይደለም፡፡ ምክንያቱም በተሰጠኝ ማንኛውም ሥጦታዎች፡፡
ምክንያቱም ጌታ አደርጋለሁ ያለውን ሁሉ ያደርጋልና፡፡

የእግ/ር ፍቅር
የተዘጋጀ መንግስ
የሓጢአተኝነት ክልከላ
የኢየሱስ እርዳታ-- ሰው ሆኖ ተወለደ፣ አስተማረ፣ ራሱን መስዋእት አድርጎ ሰጠ
መንግስት ይዞ መጣ፣ የንስሓ ስብከት ሰበከ፣ ሌሎችንም ለዚህ አገልግሎት ሾመ፡፡
እግዚአብሄር ማንንም ሲያስነሳ፣ ለዓላማ ነው፡፡ ለዓላማ ዛሬ እያንዳንዳችን እዚህ አለን፡፡
ሰዎች ስንባል በቀላሉ ከምናያቸውና ከሁኔታዎች የተነሳ ዓላማችንን ልንረሳ እንችላለን፡፡ አንዳነድ
ጊዜም ላንገነዘብ እንችላለን፡፡ ለዚያ ነው መርዶክዎስ አስተርን ያሰጠነቀቃት፡፡
የዮሴፍ ወንድሞችም አንድ ጊዜ እንኳን ለዮሴፍ እስቤው በእርሱ ላይ ያደረጉትን አላደረጉም፡፡ መልካም አስበውለት ከሆነ፣ ‹‹በሕይወት ይኑር›› የምትለውን ብቻ ነው፡፡



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?