Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት

የእግዚአብሄር ሰላም ይብዛላችሁ፡፡
መዝ 33፡6-10
በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ
የባሕርን ውኃ እንደ ረዋት የሚሰበስበው፥ ቀላዮችንም በመዝገቦች የሚያኖራቸው።
ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፍራው፥ በዓለም የሚኖሩ ሁሉም ከእርሱ የተነሣ ይደንግጡ።
እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም።
እግዚአብሔር የአሕዛብን ምክር ያጠፋል፥ የአሕዛብንም አሳብ ይመልሳል።

እስከ ዛሬ አብረን ከኢየሱስ ሕይወትና አግግሎት ስንማር የተለያዩ ጉዳዮችን ዳስሴን ነበር፡፡ በተለይ ባለፈው ሁለት ሳምንት፣ ኢየሱስ እንዴት አድርጎ ለመጣለት አላማ ሲጠነቀቅ እንደነበር አየን፡፡ እጅግ ፈታኝ በሄነ ጊዜና ስከት የሚመስሉ ነገሮች ሲያጋጢሙትም ጭምር፣ በሕይወቱ ዋናና ወሳኝ ለሆነው ተልእኮው እንደሚገባ ይሄድ ነበር፡፡ በእርግጥም የዓምን ሕዝብ ሁሉ ለመድረስ ለመጣው ኢየሲስ በእንድ መንደርና ወረዳ መርካት አልተቻለውም፡፡
ከዚህ የተነሳ፣ ወደ ሌላ መንደርና ሃገር ደግሞ እንሂድ ቢሎ መንደሩን ለቀቀ፡፡
እኛ እንደ ክርስቲያን፣ እንዴ ቤተ/ያንም ማንን መድረስ እንፈልጋለን? አለን ወይ? ለማን ነው መመስከር የምንፈልገው፣ ለማንስ ስለ መዳኑ እንጸልያለን? የማንስ ሕይወት አንጀታችንን ይበላል? ጌታ ሆይ አንተን ሳያውቁ፣ አይለፉ! ስለእነባን እንላለን?
ይህ ደግሞ አሁን ከደረስንበት ጋር ስተያይ፣ ስለ ስከታቻን ምንን ይነግረናል?

ዛሬ ደግሞ ከኢየሱስ የሪህራሄን አገልግሎት እንማራለን፡፡
ማር 1፡37- 45
37 ባገኙትም ጊዜ። ሁሉ ይፈልጉሃል አሉት።
38 እርሱም፦ በዚያ ደግሞ ልሰብክ ወደ ሌላ ስፍራ በቅርብ ወዳሉ መንደሮች እንሂድ ስለዚህ ወጥቻለሁና አላቸው።
39 በምኵራባቸውም እየሰበከ አጋንንትንም እያወጣ ወደ ገሊላ ሁሉ መጣ።
40 ለምጻምም ወደ እርሱ መጥቶ ተንበረከከና። ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው።
41 ኢየሱስም አዘነለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና። እወድዳለሁ፤ ንጻ አለው።
42 በተናገረም ጊዜ ለምጹ ወዲያው ለቀቀውና ነጻ።
43 በብርቱም ተናግሮ ወዲያው አወጣው፤
44 ለማንም አንዳች እንዳትናገር ተጠንቀቅ፥ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን አቅርብ አለው።
45 እርሱ ግን ሲወጣ ብዙ ሊሰብክና ነገሩን ሊያወራ ጀመረ፥ ስለዚህም ኢየሱስ ተገልጦ ወደ ከተማ መግባት ወደ ፊት ተሳነው፥ ነገር ግን በውጭ በምድረ በዳ ይኖር ነበር፤ ከየስፍራውም ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።
ሰው በሕይወቱ ውስጥ ርህራሔ ካለው፣ ብዙ ሰዎችን መድረስ ይችላል፡፡ ሌሎች ከልካይ የሆኑ ነገሮች ሁሉ ልከለክሉን አይችሉም፡፡ ኣርብ እለት አንድ ምስክርነት በቲቢኤን ቲቪ ላይ አየው፡፡ አይድ ልጅ ከአባቱና ከእናቱ ጋር ሆኖ፣ ለምሽነገሪ አገልግሎት ከዘመናዊ አኗኟርና ከክርስቲና ሪቀው ይኖሩ ለነበሩት ጎሳ ለወንጌል ተልእኮ ሄዴ፡፡ ልክ አባቱ፣ አውሮፕላኑን በምድራቻው ላይ ሲያሳርፍ፣ የአከባቢው ሰው ጦሩን ይዞ ወጣ፡፡ ሰዎቹ የታወቁ ጦረኞች ነበሩ፡፡ እንኳን ሌላ ፣ ከራሳቸው ጎሳም ከ60 በመቶ የሚሆኑት በርስ በርሳቸው ጦር ይሞታሉ፡፡ በጦርነት ከሚሞቱባቸው ሰወዎች 20 በሞቶ ሚሆኑ ብቻ ናቸው፣ በሌሎች የጎረበት ጎሳዎች የሚሞቱባቸው፡፡ ሌላው በራሱ ሰው ይገደላል፡፡ ታዲያ፣ ምሽነሪዎቹ፣ አውሮፒላናቸውን ሲያሰሪፉ፣ ከአነርሱ፣ አንዱ አብራሪ የነበረውን ምሽነሪ በጦር ገደለው፡፡ ከዚያ በሃላ፣ ደግሞ፣ ይህ ልጅ የጦር አጠቃቀም አያውቅምና፣ ጦርም የለውና እንዴት ይሆናል ቢሎ የልጁን እናት ይጠይቃታል፡፡ እርሷም አንተ አባቱን ስለገደልህ፣ አንተው ራስህ አስተምረዋ ትለዋለች፡፡ ሰውየውም፣ ይህንን ልጅ እንደ ልጁ አድርጎ ወሰደውና አስተማረው፡፡ ሴትየዋ ደግሞ ስለሚሻላው መንገድ እነግራችሃለሁ ቢላ፣ ስብከቱን ቀጠለች፡፡ በሃላ ከጎሳው አብዛኛቸው ጌታን ተቀበሉ፡፡ እንግድህ፣ አርብ እለት፣ ያ ገዳይ የነበረውና አባቱ የተገደለበት ልጅ፣ አብረው ሲመሰክሩ ነበር፡፡ የጁ ትልቅ ሰዉ ሆኖአል፡፡ የሁለቱም አሁን በቴሰብ ናቸው፡፡ የእርሱ ልጆች፣ የአባቱን ገዳይ፣ አያታችን ብለው ይጠሩታል፡፡
ይህንን እውነተኛ ታሪክ ስናይ፣ ርህራሄና አላማ ያለውን ሰው የሚከለክል ነገር እንደለሌ ነው፡፡ ‹‹ጥል ክርክርን ታስነሣለች ፍቅር ግን ኃጢአትን ሁሉ ትከድናለች።›› ይላል ቃሉ (ምሳ.10፡12)፡፡

አሁን ባነበብነው የመጽሓፍ ቅዱስ ክፍል፣ ሰውየውንና ኢየሱስን የሚለያዩ በቂ የሚመስሉ ምክንያቶች ነበሩ፡፡ ለምጻም ስለሆነ፣ ከሰዎች ተለይቶ ብቻውን መኖር ያለበት ሰው ነበረ፣ ከሰዎች ጋር መቀላቀል ስለማይፈቀድለት፣ ኢሱስ በነበረበት ደግሞ ሁለም ብዙ ሰዎች ስላሉ፣ ቢያንስ 12ቱ ደቀመዛሙርቱ፣ የግድ ርቀት መገንባት ነበረበት፡፡
ታሪኩን ስንዳስስ፣ በሰውየውና በኢየሱስ አከባቢ የነበሩ ትን የተወሰኑ ገጽታዎች አውጥተን ልንማርባቸው እንችላለን ብየ አምናለሁ፡፡
1. በሽታ--- መንፈሳዊና ህብተሰባዊ መገለልን የሚያስከትል አይነት
(ዘለዋ.13፡45-59

የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው ልብሱ የተቀደደ ይሁን፥ ራሱም የተገለጠ ይሁን፥ ከንፈሩንም ይሸፍን ርኩስ ርኩስ ነኝ ይበል።
ደዌው ባለበት ዘመን ሁሉ ርኩስ ይሆናል እርሱ ርኩስ ነው ብቻውን ይቀመጣል መኖሪያውም ከሰፈር በውጭ ይሆናል።
የለምጽም ደዌ በልብስ ላይ ቢሆን፥ ልብሱም የበግ ጠጕር ወይም በፍታ ቢሆን፥ በድሩ ወይም በማጉ ላይ ቢሆን፥ በፍታ ወይም የበግ ጠጕር ቢሆን፥ አጐዛ ወይም ከአጐዛ የሚደረግ ነገር ቢሆን፥ ደዌው በልብሱ ወይም በአጐዛው ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከአጐዛው በሚደረገው ነገር አረንጓዴ ወይም ቀይ ቢሆን፥ የለምጽ ደዌ ነው ለካህኑ ይታያል። ካህኑም ደዌውን አይቶ ደዌው ያለበትን ነገር ሰባት ቀን ይዘጋበታል። በሰባተኛውም ቀን ደዌውን ያያል ደዌውም በልብስ ላይ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም በአጐዛው ወይም ከአጐዛው በሚደረግ ነገር ቢሰፋ፥ ደዌው እየፋገ የሚሄድ ለምጽ ነው ርኩስ ነው። ልብሱን ያቃጥል ድሩ ወይም ማጉ የበግ ጠጕር ወይም በፍታ ቢሆን ወይም ከአጐዛው የተደረገ ቢሆን፥ ደዌ ያለበት ሁሉ፥ እየፋገ የሚሄድ ለምጽ ነውና በእሳት ይቃጠል። ካህኑ ቢያይ፥ እነሆም፥ ደዌው በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከአጐዛ በተደረገ ነገር ቢሆን በልብሱ ላይ ባይሰፋ፥ ካህኑ ደዌ ያለበቱ ነገር እንዲታጠብ ይዘዝ ሌላም ሰባት ቀን ይዘጋበታል።
ደዌውም ከታጠበ በኋላ ካህኑ ያያል እነሆም፥ ደዌው መልኩን ባይለውጥ ባይሰፋም፥ ርኩስ ነው በእሳት አቃጥለው ምልክቱ በውስጥ ወይም በውጭ ቢሆን እየፋገ የሚሄድ ደዌ ነው።
ካህኑም ቢያይ፥ እነሆም፥ ደዌው ከታጠበ በኋላ ቢከስም፥ ከልብሱ ወይም ከአጐዛው ወይም ከድሩ ወይም ከማጉ ይቅደደው።
በልብሱም ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከአጐዛው በተደረገ ነገር ላይ ደግሞ ቢታይ፥ የወጣ ለምጽ ነው ደዌው ያለበትን ነገር አቃጥለው። አንተም ካጠብኸው ልብስ ወይም ከድሩ ወይም ከማጉ ወይም ከአጐዛው ከተደረገው ነገር ላይ ደዌው ቢጠፋ፥ ሁለተኛ ጊዜ ይታጠባል፥ ንጹሕም ይሆናል። በበግ ጠጕር ልብስ ወይም በበፍታ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከአጐዛ በተደረገ ነገር ላይ ቢሆን፥ ንጹሕ ወይም ርኩስ ያሰኝ ዘንድ የለምጽ ደዌ ሕግ ይህ ነው።

ሉቃ 17፡ 11-15 ‹‹ወደ ኢየሩሳሌምም ሲሄድ በገሊላና በሰማርያ መካከል አለፈ። ወደ አንዲት መንደርም ሲገባ በሩቅ የቆሙት አሥር ለምጻሞች ተገናኙት፤ እነርሱም እየጮኹ። ኢየሱስ ሆይ፥ አቤቱ፥ ማረን አሉ። አይቶም። ሂዱ፥ ራሳችሁን ለካህናት አሳዩ አላቸው። እነሆም፥ ሲሄዱ ነጹ። ከእነርሱም አንዱ እንደ ተፈወሰ ባየ ጊዜ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን እያከበረ ተመለሰ››
የተለያዩ ዓይነት ሰዎችን ከሶቻልና መንፈሳዊ ህብረቶች የሚከለክሉ በሽታዎች አሉ፡፡ ኢቦላ፣ ኤድስ፣ ሌሎችም ተላለፊ የሚባሉ በሽታዎች ቢቻ ሳይሆን፣ ሌሎች ግላዊ፣ ማህበረሰባዊና ፖለቲካዊ በሽታዎችም ጭምር አሉ፡፡ የኑሮ፣ የትዳር፣ የኢኮኖመሚ፣ እንዲሁም ስነልቦናዊ አግላዮች አሉ፡፡
አንዳነዶችን ሰዎች ርከግናይዝ አድርገው የሚያገሉ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ በሽተኛው ራሱ ከደረሰበት ነገር የተነሳ በስነ ልቦናዊ ችግር የተነሳ ራሱን የሚያገልበት ሁኔታ ይሆናል፡፡

2. እምነት-- በኢየሱስ ችሎታ ላይ ጥርጣሬ አልነበረውም፡፡ ይህ በከንቱ ከሰውየው የመጣ ነገር ብቻ አይደልም፣ የእግዚአብሄርም ቃል ያንኑን ያረጋግጥልናል፡፡

ዘፍ 18፡13-15‹‹እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው። ካረጀሁ በኋላ በውኑ እወልዳለሁን? ስትል ሣራ ለምን ሳቀች? በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ ሣራም ልጅን ታገኛለች። ሣራም ስለ ፈራች፦ አልሳቅሁም ስትል ካደች። እርሱም፦ አይደለም፥ ሳቅሽ እንጂ አላት።››

ማቴ 28፡18 ‹‹ ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።››

3. የስግደት/ጸሎት ገጽታ--- ‹‹ተንበረክኮ፣ጌታ ሆይ›› አለ በማቴ.2፡8

4. ጥርጣረ/ፍርሃት--በኢየሱስ ለእቅርታ ለፈውስ፣ ለማዳን ፈቃደኝነት ላይ -- ምናልባትም ከራሱ ሓጢአት ጋር የተያያዜ ሊሆን ይችላል፡፡
ይህ አይነቱ ጥርጣሬ ዛሬም በዘመናችን እንግዳ አይደለም፡፡ አብዛኛው ሰው፣ በተለይ በክርስቲያኑ ማህበረሰብ፣ በእግዚአብሄር ያምናል፣ ማድረግ እንደምችል ያውቃል፡፡ ጸሎትን ይጸልያል፣ የተለያዩ የአምልኮ ስርአቶችን ይፈጽማል፡፡ ነገር ግን፣ ወደ ግል ሕይወቱ ሲመጣ፣ ምን ያክል እግዚአብሄር ሊረዳው እንደምፈልግ/ እንደሚፈቅድ ይጠራጠራል፡፡ ምናልባት፣ የራሱን ማንነት ስለምረዳ፣ ያደረገውን የበደል ክብዴት ብቻ ስለሚያውቅ፣ ወዘተ.
በኢሱስ ጋ ደግሞ የከፈተ
1. ርህራሄ ልብ ነበረ፡፡
2. ለመቀበል ፈቃደኝነት ነበረ
3. ሊረዳው የሚችልም ቃል ነበረ (ፈውስን የሚጠራ ቃልና ፍቅሩን የሚያረጋግጥ ቃል)
4. የማዳን/የማንጻት ብቃት/ ችሎታ
5. ለዚህ አንድ ሰው በግል የሚደረገው ደግሞ ለዋናው አጀንዳው ጋር እንዳይጋጭ መጠንቀቅም ነበረ፡፡ ጊዜው እስክደርስ ድረስ እንደ መስሂው/አንደሚጠበቀው ነፃ አውጪ ራሱን ከማስተዋወቅ መጠበቅ---እንዳትናገር

እንግዲህ ከኢየሱስ ህይወትና አገልግሎት መማር ከለብን ነገሮች አንዱ የርህራሔን አገልግሎት ነው፡፡
1. ኢየሱስ በርህራሄ ወደ አለም መጣ--- ማንም እንዳይጠፋ --ዮሓ.3፡17

2. በርህራሄ የተቸገሩትን ይረዳ ነበር (ለምጻምን አነጻ፣ ጎባጣን አቀና፣ የተራቡትን አበላ፣ የሞቱትን አስነሳ)
ሉቃ.7፡11-15 ‹‹በነገውም ናይን ወደምትባል ወደ አንዲት ከተማ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም ብዙ ሕዝብም ከእርሱ ጋር አብረው ሄዱ። ወደ ከተማይቱም በር በቀረበ ጊዜ፥ እነሆ፥ የሞተ ሰው ተሸክመው አወጡ፤ እርሱም ለእናቱ አንድ ልጅ ነበረ፥ እርስዋም መበለት ነበረች፥ ብዙም የከተማ ሕዝብ ከእርስዋ ጋር አብረው ነበሩ። ጌታም ባያት ጊዜ አዘነላትና። አታልቅሽ አላት። ቀርቦም ቃሬዛውን ነካ፥ የተሸከሙትም ቆሙ፤ አለውም። አንተ ጐበዝ፥ እልሃለሁ፥ ተነሣ። የሞተውም ቀና ብሎ ተቀመጠ ሊናገርም ጀመረ፥ ለእናቱም ሰጣት።››
3. በርህረሄም ያስተምር ነበር (ማቴ 9፡ 36-38 ‹‹ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር። ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው። በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን። መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት አላቸው።››
ማር 6፡34-42 ‹‹ ኢየሱስም ወጥቶ ብዙ ሕዝብ አየና እረኛ እንደሌላቸው በጎች ስለ ነበሩ አዘነላቸው፥ ብዙም ነገር ያስተምራቸው ጀመር። በዚያን ጊዜም ብዙ ሰዓት ካለፈ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው። ቦታው ምድረ በዳ ነው አሁንም መሽቶአል፤ የሚበሉት የላቸውምና በዙሪያ ወዳሉ ገጠሮችና መንደሮች ሄደው እንጀራ ለራሳቸው እንዲገዙ አሰናብታቸው አሉት። እርሱ ግን መልሶ፦ እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው አላቸው። ሄደን እንጀራ በሁለት መቶ ዲናር እንግዛላቸውን? እንዲበሉም እንስጣቸውን? አሉት። እርሱም፦ ስንት እንጀራ አላችሁ? ሂዱና እዩ አላቸው። ባወቁም ጊዜ። አምስት፥ ሁለትም ዓሣ አሉት። ሁሉንም በየክፍሉ በለመለመ ሣር ላይ እንዲያስቀምጡአቸው አዘዛቸው።
መቶ መቶውና አምሳ አምሳው እየሆኑ በተራ በተራ ተቀመጡ። አምስቱንም እንጀራ ሁለቱንም ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረከ፥ እንጀራውንም ቈርሶ እንዲያቀርቡላቸው ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ ሁለቱን ዓሣ ደግሞ ለሁሉ ከፈለ። ሁሉም በልተው ጠገቡ፤››

አብዛኛው መሪ/አስተማሪ ሕዝቡን የሚያስተምረው፣ ራርቶለት አይደለም፣ ነገር ግን ለራሱ ዓላማና አሠራር እንዲመቻቸው ነው፡፡ ኢየሱስ ግን ራርቶ ይረዳል፣ ራርቶ ያድናል፣ ራርቶ ያስተምራል፡፡
ዛሬም በርህርራሄ እያስተማረን ነው፡፡ እውነተኛና አስተማማኝ የሆነውንም ፍቅሩን ሊገልጥልን ይፈልፋል፡፡ እንድንከተለውም የምጠራን የተከተታዮቹን ብዛት በቁጥር እንድናሳድግ ሳይሆን ያለ እርሱ ምንም እንደማንችል ስለሚያውቅ ነው፡፡

4. በርህራሄ የለሎችን ድካም ያግዝ ነበር (እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ ማለድሁ)

እንግዲህ ‹‹እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውናያለው ኢየሱስ ይህንን የእርሱን ባህርይ እንድንወስድ ይፈልጋል፡፡ በእርሱ ስም ሌሎችን በርህራሄ እየዳሰስን፣ ከጥፋት እንድናስመልጣቸውም ይፈልጋል፡፡

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?