Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት

ማር 2:1-2
1" ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ደግሞ ገብቶ በቤት እንደ ሆነ ተሰማ።
2 በደጅ ያለው ስፍራም እስኪጠባቸው ድረስ ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ፤ ቃሉንም ይነግራቸው ነበር።"

የታሪኩ ዳራ፡ በቅፍርናሆም---
ኢየሱስ በእድገት ሀገሩ በናዘሬት ከተናቀ በሃላ፣ ወደ ቅፍርናሆም ሂዶ መኖር እንደጀመረ በሉቃ.4፡ 16-31 እናነባለን፡፡
በአገልግሎቱ ዘመን ውስጥ ኢየሱስ በቅፍርናሆም ብዙ ተአምርትን አሳይቶአል፡፡
ሆኖም ግን ቅፍርናሆም፣ ኢየሱስ የተቀመጠባት ከተማ፣ ብዙም ተአምር የተሰራባት ከተማ ቢትሆንም፣ ንስሓ መግባት ግን አልተቻላትም ነበር፡፡ ከዚህም የተነሳ፣ ኢየሱስ፣ የተሰጣትን እድል ባለመቀበሏ ነቅፎአታል፡፡ ማቴ. 11፡20-24፡፡ ምናልባት አንዳንዶች ኢየሱስ በከተማቸው ስለተቀመጠ ብቻ፣ ራሳቸውን ፣ ሰማይ የደረሱ እስኪመስላቸው ከሌሎች አብልጠው አይቶ ነበር፡፡ ኢየሱስ ግን ‹‹ወደ ሲኦል ትወርዳላችሁ›› ይላቸዋል፡፡
እኛም ዛሬ ፣ አጋጣሚ እንኳን በሚመስል ሁኔታ፣ እንድናይና እንድንሰማ የተሰጠንን ዕድል ተጠቅመን ወደ ጌታ ለመመለስ፣ እርሱን እንደሚገባ ለማመንና ለመከተል ፈቃደኞች ካልሆንን ራሳችንን እንጎዳለን፡፡
ዛሬም ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ለመማር ብለን የምናየው ታርክ በዚችሁ በቅፍርናሆም ከተማ ከተደረጉት ተአምራት አንዱን ነው፡፡፡
እግዚአብሄር አንድን ነገር በሕይወታችን ሲያደርግ ወይም ደግሞ እንድናልፍበት ሲፈቅድ ለዚያች አንድ ነገር ክንዋነ ብቻ ጓግቶ ሳይሆን ከዚያ ጋር የተያያዙ ብዙ ነገሮችን በሕይወታችን፣ በዘመናችን እና በሌሎችም ለማድረግ ሲፈልግ ነው፡፡
በዚህ ክፍል ወደ ኢየሱስ የተወሰደው ሰውዬ አንድ ችግር እንዳለበት እርሱና እርሱን ከበውት የነበሩ ሰዎች ተገንዝበዋል፡፡ ይህም ችግሩ ከሌላ ቦታ መፍትሄ ሊያገኝበት የዙሚችል ችግር አልበረም፡፡ መስራት ያቆሜ የሰውነቱ ክፍል ነበርና፡፡ ሽባ ይባል ነበር፡፡
የነበረው እድል በዚያ ግማሽ ሽባነት የሞቱን ቀን መጠባበቅ ነበር፡፡ ያም የምሆነው በሌሎች ሰዎች በጎ ፈቃድ መሆን አለበት፡፡ ካልሆነ፣ ራሱን መርዳት የማይችል ስለነበረ፣ ሕይወቱ ከሞት ብዙም የራቄ አልነበረም፡፡
በዙሪያው ያሉ ስማቸው ያልተጠቀሠ ግን በእምነታቸው ጌታን ያስደነቁ ሰዎችንም እናያለን፡፡ እነዚህ ሰዎች ይንን ችግረኛ ለምን እንደተሸከሙት ባናውቅም (ምናልባት በዝምድና፣ ወይም በጉርብትና ሊሆን ይችላል) ግን በእምነት እንደተሸከሙትና ወደ ኢየሱስ እንዳመጡት እንመለከታለን፡፡ ወገኖች መሸካከምና ይልቁንም በእምነት ወደ ጌታ የተቸገሩትን ማምጣት መልካም ነው፡፡ አካላዊ ብቻ ሳይሆን፣ ሰዎች በተሌያየ ሁኔታ ሽባ ሆኖ በዙሪያችን ሊኖሩ ይችላሉና፡፡ ኢየሱስ ግን ፈዋሽ ነው፡፡
ስለዚህ ሰዎቹ ወደ ሞት የተቃረበውን ይህንን ችግረኛ የመጨረሻ መፍትሄ ነው ወደሚሉት፣ ብዙዎችን ይፈውሳል ተብሎ እየተወራለት ወደነበረው ወደ እየሱስ መውሰድ ነበር፡፡
ሰዎቹ ይህ የመጨረሻና ብቻኛ የመዳን እድሉን ለሌላ አመቺ ጊዜና ሁኔታ ማስተላለፍ አልፈለጉም፡፡ ማንኛውንም ነገር ኢየሱስን ከማግኘት ሊከለክላቸው የሚችል ምክንያት አድርገው አልወሰዱም፡፡ ልክ ያዕቆብ ካልባረከን አልለቅህም ቢሎ ከመልአኩ ጋር እንደታገለ፣ እነርሱም ከቤቱ ጣሪያ ጋር ታገሉ፡፡
ቢሆንም ግን ከሰው ብዛት የተነሳ፣ በተለመደው መልኩ ወደ እየሱስ ለመድረስ አልተቻለም ነበር፡፡ አንዳንዶች ለማይጠቀሙበት ቦታ ያጣብባሉ፡፡ ኢሱስም ያውቃቸዋል፣ ያዝንላቸዋልም፡፡
ሲለዚህ ኢየሱስን ለማግኘት ሲባል ያልተለመደ ነገር፣ እንዲያውም ሕገ-ወጥ የሚመስል ሥራ ተሰራ፡፡ የሰውን ቤት ጣሪያ አፍርሶ ሰውየውን በጣራ በኩል አስገቡት፡፡ ኢየሱስ በቤቱ ሆኖ አንዲድያገለግል የፈቀደው ሰው ራሱ ያልጠበቀው ነገር መጥቶበታል፡፡ አንዳነድ ጊዜ፣ በውጭ ባሉት ብቻ ሳይሆን፣ ጌታን እናገልግል ካልን፣ ጌታ በቤታችንና በህይወታችን እንዲሰራ ስንፈቅድለት እኛ ያልጠበቅናቸው ጥቃት የሚመስሉ ነገሮች ሊደርሱብን ይችላሉ፡፡
በሰዎቹ ዘንድ አንድ ጌታን ያስደነቀው ነገር ነበረ፡፡ እምነታቸው፡፡ በማያምን ትውልድ መካከል ሆኖ በእምነት ወደ እርሱ የሚቀርብ ሰው ጌታን ያስደንቀዋል፡፡ የፈውስና የእውነተኛ ደስታ መንገድ በእምነት መንገድ ነውና፡፡
ሰዎቹ በአራት ሰዎች ጫንቃ ላይ ተኝቶ የመጣውን ያንን ሰው ወደ ኢየሱስ በዚያ ጥያቄ በሚፈጥር አኳን ሲያመጡ፣ የሌሎችንም የኢየሱስንም ትኩረት የሚስብ ይመስላል፡፡
ሆኖም ግን ኢየሱስ ግን ከዚያ ይልቅ የበለጠ ትኩረት የሚስብን ነገር ተናገረ፡፡ ‹‹አንተ ልጅ፣ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ›› አለው፡፡ ቁ. 5
ያ ንግግሩ ለሚሰሙት አይውዳዊያን፣ በተለይ ደግሞ ለጸፎች ‹‹የስድብ ንግግር›› ተደርጎ የሚቆጠር ነው፡፡
ምክንያቱም ይህ ኢየሱስ የተናገረው ነገር፣ በሰው ዘንድ የሚቻል አይደለም፣ እነርሱ እንደሚሉት፡፡ ነገር ግን መለኮታዊ ችሎታን የሚጠይቅ ነገር ነበር፡፡
በዚህ ክፍል ኢየሱስም ሆነ፣ ሰዎቹ የተናገሩት ንግግር በጣም ጥቅት ነው፡፡ ነገር ግን የነበረው ልዩነትና ክርክር በጣም ከባድ ነበር፡፡
ኢየሱስ የሰዎችን ልብ ያውቅ እንደ ነበር ተደጋግሞ በዚህ ክፍል ተገልጸዋል፡፡ በሽተኛውን ያመጡት ሰዎች ስለነበራቸው እምነት ሲናገርና በዚህ ቦታ ደግሞ ‹‹በልባችሁ ይህን ስለ ምን ታስባላችሁ?›› ብሎ ሲጠይቅ፡፡
ዛሬም ቢሆን በመካከላችን ያለውና ሊናመልከው የመጣነው ጌታ የእያንዳነዳችንን ልብ ያውቃል፡፡ ሲያየን ደስ ይለው ይሆን ወይስ ‹ስለምን እንዲህ ታስባላችሁ?› ይለን ይሆን?
ይህ ቢቻ ደግሞ አይደለም፣ ስለበሽተኛውም ሲናገር ‹‹የሰውየውን ዋነኛ ችግር›› ቅድሚያ ሰጥቶት መናገሩ ነው፡፡
መጽሓፍ ቅዱስ ሲናገገር፣ ‹‹የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው›› የእግዚአብሄር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ነው›› ይላል፡፡ ሮሜ.6፡23፡፡
ይህ ሰው ለጊዜው በስዎች የተከበበ ቢሆንም (ተሸክሞ ወደሚረዳበት የሚያደርሱት አሉ) ግን ከእግዚእብሄር የተለየ ነበር፡፡ ምክንያቱም ኋጢአት ከእግዚአብሄር ይለያልና፡፡ ኢሳ. 59፡1-2::
ሰው ደግሞ ከፈጣሪው ከተለዬ፣ ዘላለሙ አደጋ ላይ ወድቆአል፡፡
ወደ ኢየሱስ ግን መሄድ ቢችል ሰው ዘላለሙን ይዋጃታል፡፡ ኢየሱስ ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶውኑ ወአ ውጭ አላወጣውም ቢሎአል፡፡ በጎቼ ደምጸን ይሰማሉ፣ ይከተሉኝማል፣ እኔም የዘላለምን ሕይወት እሰጣቸዋለሁ፡፡ (ዮሃ.10፡25-30)፡፡
ስለዚህ ይህ አካላዊ በሽታ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ችግርም ያለበትን ሰው ኢየሱስ ለዘለኣለም ፈቶ ለቀቀው፡፡ ‹‹አንተ ልጅ፣ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ›› አለው፡፡ ቁ. 5
ይህ ለሰዉየው ትልቅ እረፍትና ነጻነት ነው፡፡ የሚታየው ቢቻ ሳይሆን የማይታየው ችግሩም መፍትሄ አግኝቶለታል፡፡
በሌላ አንጻር ደግሞ ይህ አብዛኞችን ይቆረቁራል፡፡ አይዋጥላቸውም፡፡ ባይዋጥልንም እግዚአብሄር የሚያደርገው ነገር ሁሌም ትክክል ነው፡፡
ኢየሱስ ግን ይህንን ሲያደርግ ለሌሎች ራሱን ለማቅረብ ነበር፡፡ እየከበቡት ግን ያልተጠቀሙበት እንዲጠቀሙ፣ ከወንዝ ዳር ቆሞ በጥም እየሞቱ ላሉት፣ ከይቅርታ ሰጪ ጋር እየተጋፉ ግን በኃጢአት ጎብጠው ለነበሩት በር መንገድ ለማሳየት ይፈልግ ነበር፡፡
ቢሆንም ግን የሃገረው ሰው ‹‹ማረኝ!›› እያሌ እግሩ ሲር ከመውደቅ ሌሎች ጥያቄዎች ነበሩአቸው፡፡ መቀበል ከበዳቸው፡፡ ‹‹ሃጢአት የማስተሰረይ ስልጣን እንዳለን ታወቁ ዘንድ እወዳለው አለ፡፡ቁ 9፡፡
ወገኖቼ፣ እያንዳነዳችን፣ እኔንም ጨምሮ፣ በዚህ እንድንገኝ የእግዚአብሄር ፈቃድ ሆኖአል፡፡ ሁለትና ሶስት ሆናችሁ በስሜ በሚትሰበሰቡበት በዚያ በመካከላችሁ እሆናለው ያለው ጌታ በመካከላችን እንዳለ አምናለሁ፡፡ ምናልባት፣ ግን ይንን እድል ተጠቅመን ከእርሱ የምናገኘውን እረፍትና ሰላም ትተን ከነሸክማችን እንዳንኖር እሰጋለሁ፡፡
ምናልባት አንዳንዶቻችን፣ እባክህ ተወኝ፣ እኔ አሁን የሚፈልገው ይህ ነው፣ ያ ነው ልንል አንችላለን፡፡ አዎን የተለያየ ነገር ልፈልግና ቅድሚያ ልንሰጣቸው እንችላለን፡፡ ቢሆንም ግን ከእኛ ይልቅ ደግሞ ለሕይወታችን የሚያስብና የሚየውቅልን ጌታ፣ ‹‹ለምን ከእኔ ሓጢአታችሁ ትሞታላችሁ›› ይለናል፡፡ በእርሱ ፍት የሞቴውን ማንነታችንን (ሽባነታችንን) ቢናቀርብ እርሱ ሊረዳን ፈቃዱም ስልጣኑም፣ ችሎታውም አለው፡፡
ሁሉም ሰው እኩል ሰው የለውም፣ አንዳነዶቻችን በወዳጆች ተከበን ልንሆን እንችላለን (ስለእኛ በእግዚአብሄር ፍት የአቅማቸውን የሚያደርሱን አሉ)፡፡ ሌሎቻቸንን ደግሞ ‹‹ሰው የለኝም›› ልንል እንችላለን፡፡ ጌታ ግን ለማንኛችም ፍቅር አለው፡፡ ሊረዳንም ይፈልጋል፡፡

ቁ.11-12 ላይ ‹‹ሽባውንም፣ አንተን እልሃለው፣ ተነሳ፣ አልጋህንም ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ አለው፡፡ ተነስቶም ወዲያው አልጋውን ተሸክሞ በሁሉ ፊት ወጣ ስለዚህ ሰዎች ሁሉ ተገረሙና እንዲህ ያለ ከቶ አላየንም ብለው እግዚአብሄርን አከበሩ፡፡››
ከዚህ ክፍል ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ምን እንማራለን
- ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቃሉን ይነግራቸው ነበር ቁ.2 እነርሱ የመጡት ምን እንደሚሰራ ለማየት፣ ለመከታተል፣ ለመጠየቅ… ሊሆን ይችላል፡፡
- እምነትን ያከብራል፡፡ የታመኑበትን አያሳፍርም፡፡ ቁ.5
- ሰው ከኃጢአቱ እንዲላቀቅ ይፈልጋል፡፡ ምህረትንም ያደርጋል፡፡
- መለኮታዊነቱንም አሳይቶአል፡፡
- ኢየሱስ ሁሌ መቅደም ያለበትን ያስቀድማል፡፡ ‹‹አስቀድሜህ… ታረቅ፣ አስቀድማችሁ የእግዚአብሄርን መንግስትና ጽድቁን ፈልጉ፣ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ከዚያም አልጋህን ተሸክመህ ሂድ›› ሰዎች የተለያዩ ነገሮችን ፍለጋ ሲመጡ እርሱ ደግሞ እነርሱን የሚያስፈልጋቸውን አስቀድሞ ይሰጣቸዋል፡፡
- እኛም እግዚአብሄር በሕይወታችን ቅድሚያ እንድሰጠው ለሚፈልገው ለነፍሳችንና ለሌሎ ነፍስ ቅድሚ መስጥት አንድንችል ጌታ ይርዳን፡፡

እግዚአብሄር ይርዳን!



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?