Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት

ማርቆስ 1፡14-15 " ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ። ››

ባለፈው (የዛሬ ሦስት ሳምንት ማለትም በፈብረዋሪ8፣2015) የጌታችን ኢየሱስን ሕይወትና አገልግሎት ስናጠና፣ የኢየሱስን ሕይወት በጥምቀቱ ጊዜ፣ በፈተናው ጊዜ፣ የጸሎት ሕይወቱንም ምን ይመስል እንደ ነበር አይተናል፡፡
1. የጥምቀት ጊዜ፡ ጽድቅን ሁሉ የማድረግ አላማ ይዞ አንደመጣ ይናገር ይተግብርም አንደነበር፡፡
a. ራሱን ዝቅ ያደርግ ነበር
b. ጽድቅን ለመፈጸም መደረግ ያለበትን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነበር
c. አባቱም አከበረው
2. የፈተናውን ጊዜ፡ ፈተናን በእግዚአብሄር ቃል እንዳሸነፈ፡፡ የቀረቡለት ፈተናዎች ደግሞ
a. ልጅነቱን አንዲጠራጠር የሚያደርግ
b. ከዓላማው እንዲወጣ የሚያደርገው
c. ከእግዚአብሄር ፈቃድ ጋር እንዲጋጭ የሚያደርገው (ከአባቱ ጋር ለማጣላት የቀረበ) ፈተና ነበር
d. ራሱን አንዲጎዳ የሚጋብዝ ፈተናም እንደቀረበለት አይተን ነበር፡፡ ሠይጣን በእኛ ላይ ማድረስ ለሚፈልገው ማንኛውም አደጋ እኛው ራሳችን ተጠያቅነትን እንድንወስድ አስፈርሞን በእጃችን ልጎዳን ይፈልጋል፡፡

ለኢየሱስ የቀረቡት ፈተናዎች ሁሉ ደግሞ በድካሙ ጊዜ--በመጨረሻው የምድረበዳ ቆይታ ጊዜ የቀረቡ እንደነበርና እኛም የመጨረሻውን የምድረበዳ ኑሮአች ውስጥ ለሚቀረቡልን የመውጫ መንገድ መሳይ ነገሮች መጠንቀቅ እንዳለብ አይተናል፡፡
o ጵላጦስ እንኳን ከስቅለቱ በፊት ያቀረበለት ሃሳብ ነገሮቹን ሁሉ በእርሱ እጅ እንዳለ አድርጎ ነው (ዮሓ 19፡9-12)፡፡ ኢየሱስ ግን ሕይወቱ ያለው በሰው እጅ እንዳልሆነ ጠንቅቆ ያውቅ ስለነበት በዚህ ማባበያና ማስፈራሪያ ቃል ከኣላመው ፍንክች አላለም፡፡
o ነቡከድናጾርም በመጨረሻ ቃሉን ለነሰድራክ ሚሳክና አብድነጎ ሲናገር፣ "ከእጄ ማን ያድናችሃል›› ብሎ ነበር፡፡ አምላካቸውን የሚያውቁት የአግዚአብሄር አገልጋዮች ግን፣ "አምላካችን ያድነናል፣ ባያድነን እንኳ አንተ ላቆምከው ለዚህ ምስል አንሰግድም›› አሉ፡፡ ዳን. 3፡13-18
o
መልካምም ሆነ ክፉ፣ እንደ እግዘአብሄር ፈቃድ ልናልፍበት የወሰነውን ነገር ለማደናቀፍና ከሰማያዊው አባታችን ጋር ሊያጣላን ጠላት በመጨረሻው ሰዓት ከባባድ ፈተናዎችን ሊያመጣብን ይችላል፡፡ በእግዚአብሄር መታመን ግን ያድነናል፡፡

3. የጸሎት ጊዜ፡ ኢየሱስ ቋሚ (ኮንስስተንት) የሆነ የጸሎት ሕይወት አንደነበረውም አይተን ነበር፡፡ አገልግሎት ከመጀመሩም በፊት፣ ደቄ መዛሙርቱን ከመምረጡ በፊት፣ ሲያገልግና ብዙ አድናቂዎች ሲያገኝም፣ ብቻውን ስተውም፣ በመስቀል ላይም ሆኖ ይጸልይ ነበር፡፡

ማንኛውም ኣይነት በሕይወቱ ያለፈባቸው ነገሮች የጸሎት ሕይወቱን ከቦታው አላጠፉትም ነበር፡፡

ህያው ሲሆን አንደ ፀሎት የሚያስደስም፣ በሕይወታችን ላይ ለውጥ የሚያመጣም የህብረት ጊዜ የለም፡፡

የአባቱን ደስታ ያስቀድም እንደነበር ፡፡

በቃሉና በጸሎት ፈተናን ሁሉ ማሸነፍ ስለሚቻል--- እነርሱን ሁልጊዜ አጥብቆ መያዝ ያስፈልገናል፡፡ ጸሎት መነጋገር ነው፣ ቃሉም ፈቃዱን የምናውቅበት መሆኑን ከኢየሱስ ሕይወት እንማራለን፡፡
ዛሬ ደግሞ፣ የምናያቸው፡-

4. የስብከትና የማስተማር ጊዜው፡ የእግዚአብሄርን መንግስት ወንጌል በመስበክና በማስተማር ያገለግል ነበር
a. በዚያን ዘመን ሰዎች የሚያውሩአቸው ብዙ ነገሮች አንደነበሩ የታሪክ መዝጋቢዎችና ተመራማሪዎች ይመሰክራሉ፡፡ የፖለትካው፣ የኢኮኖሚው፣ የአከባቢው፣ የፍልስፍናው፣ የሌሎችም፡፡
b. ኢየሱስ ግን ከሁሉም በተለዬ መልኩ ስለእግዚአብሄር መንግስትና በንስሓ ወደ እርሱ ስለመግባት ያስተምር ነበር፡፡
ቀደም ቢለው የነበሩ ሰባኪዎችና አስተማሪዎች በብዛት በሕግ መተላለፍ ስለሚመጣው መዓት ይሰብኩ ነበር፡፡ ኢየሱስ ደግሞ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በማለት ስብከቱን ጀመሬ፡፡

ማርቆስ 1፡14-15 " ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ። ››
c. በአብዛኛው ሰው ሁሉ ራሱን ንጹህ አድርጎ ማሳየት ይፈልጋል፡፡ ራሱን ለማንጻትም ጥፋተኛ አድርጎ መውንጀል የተለመደ ነው፡፡ (ከአዳምና ከሄዋን ተነስተን ማየት እንችላለን)
d. ዛሬም ቢሆን አንኳ ሰው ስለ ንሰሓ የሚደረግ ስብከት መስማት አይፈልግም፡፡ በተቻለ መጠን የተሳሳቴ መንገዱንና አስተሳበቡን ጥሩ ምክንያት ሰጥቶበት አንዳልተሳሳቴ አድርጎ የሚያሳየውን የፍልስፊና ስብከት/ ሰባኪ ይፈልጋል፡፡
e. ከዚህ የተነሳ ደግሞ፣ ለሓሰተኞች ሰባኪዎች፣ አስተማሪዎችና ነቢያት፣ እንዲሁም ክርስቶሶች የተመቻቸ ሁኔታ ተፈጥሮላቸዋል፡፡ ያ ማለት ሰው "ተሳስቻለሁ›› ማለትን አይፈልግም፡፡ ያንን የሚለው ዝናንና ገንዘብን፣ ሌላ ኣይነት ጊዜያዊ ጥቅም የሚያመጣለት ከሆነ ብቻ ነው፡፡
f. ንስሃ ማለት በጥፋታችን/ስህተታችን መጸጸታችንን ብቻ ለእግዚአብሄ መንገር ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን "ወደ እግዚአብሄር መመለስ›› ፣ "የሃጢአትን ይቅርታ ማግኘት››ንና "ድነትን ማግኘት››ን ያካትታል፡፡
g. ለዚያ ነው ኢየሱስ፣ "ንስሃ ግቡ፣ በወንጌልም እመኑ›› ብሎ የተናገረው፡፡ በወንጌል ማመን ማለት፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድነት ማግኘት መላት ነው፡፡ ስለዚህ "ይህ አይነቱ እምነት፣ በአምላክ መኖር፣ በእርሱ ፈጣሪነት ማመን ብቻ ሳይሆን፣ ኢየሱስ ሊያድነን እንደ መጣ አምኖ በዚህ እምነት ወደ እግዚአብሄር መመለስ ነው፡፡

አንድ ፊልጵ ሄነሪ የሚባለ በ 17ኛው ክ/ሀ (1680) ወንልን ይሰብክ የነበረ ሰው እንዲህ እንዳል የነገርለታል፡- "በመድረክ ላይ መሞታ ካለብኝ ንስሃን እየሰበክሁ፣ ከመድረክ ወርጄ መሞት ካብኝ ደግሞ ንስሃን እየተለማመድኩ መሞት እመኛለሁ›› ፡፡
h.

እንግድህ የኢየሱስ ትልቁ ጥሪ ሰዎች ሁሉ ወደ እግዚአብሄር መንግሥት እንዲገቡ ነው፡፡ ይህ ዓላማው ዛሬም ቢሆን አልተቀየረም፣ እርሱ ወደ ሰማይ ከአረገ በሃላም እንኳ እንደ እነ ጳውሎስ ያሉትንና ሌሎችንም ለዚሁ አገልግሎት ነበር የሾመው፡፡
ራሱ ወንጌልን አስተማረ፣ ሌሎች ህደው እንዲያስተምሩ ላኬ፣ ዛሬም እየላኬ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ ይፈልጋል፡፡
i. ኢየሱስ ወንጌልን ያስተምር ነበር ብሎ መጽሃፍ ቅዱስ ሲነግረን፣ አሁን በእጃችን ያሉትን የአድስ ክዳን መጽሃፍትን በእጁ ይዞ ከእነርሱ ያስተምራል ማለት ሳይሆን፣ ሃጢያተኞች የሚድኑበትን መልካም ዜና ከአብ የሰማውን፣ ሊያደርግም የመጣውን የሚስራች ብሎ ይናገር ነበር ማለት ነው እንጂ፡፡ የዚህ መልካም ዜና/ወንጌል ይዘቱ፡-

የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል። የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድ ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል። ከጥንትም ጀምሮ ባድማ የነበሩትን ይሠራሉ ከቀድሞ የፈረሱትንም ያቆማሉ ባድማ የነበሩትንና ከብዙ ትውልድ በፊት የፈረሱትን ከተሞች እንደ ገና ይሠራሉ። መጻተኞችም ቆመው በጎቻችሁን ያሰማራሉ፥ ሌሎች ወገኖችም አራሾችና ወይም ጠባቂዎች ይሆኑላችኋል። እናንተ ግን የእግዚአብሔር ካህናት ትባላላችሁ፥ ሰዎቹም የአምላካችን አገልጋዮች ብለው ይጠሩአችኋል የአሕዛብን ሀብት ትበላላችሁ፥ በክብራቸውም ትመካላችሁ። በእፍረታችሁ ፋንታ ሁለት እጥፍ ይሆንላችኋል፥ በውርደታችሁም ፋንታ ዕድል ፈንታችሁ ደስ ይላቸዋል ስለዚህ በምድራቸው ሁሉ እጥፍ ይገዛሉ፥ የዘላለምም ደስታ ይሆንላቸዋል።›› ኢሳ 61፡1-7
"…የእግዚአብሄር መንግስት ቀርባለች ንስሃ ግቡ በወንገልም እመኑ››
- እምነት በጣም ወሳኝ ቅድሜ ሁኔታ ነው፡፡ ሰው ለመዳን ማመን አለበት፡፡
- ዮሃ. 1፡11-12 ‹11 የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።
- 12 ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤›
ዮሃ.3፡16-17" ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል። በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል። "፤
ሮሜ 3፡20-15ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና።
አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥
እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤
በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።
እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥
እንግዲህ የንስሃም ሆነ የእምነት ዋናው ኣላማ ወደ እግዚአብሄር መንግስት ለመግባት ነው፡፡
አንዳነድ ግዜ ይህ እውነት ይረሳና፣ ሰዎች ክርስቲናን/በቴክርስቲያንን ለሌላ ነገር ሊጠቀሙበት ይፈልጋሉ፡፡
መንግስቱ ዋነኛና ትኩረት ሊሠጠው የሚገባ ነገር ነው፡፡
ኢየሱስ ስለ መንግስቱ ስናገር (ማቴ.13፡44-47) "
44 ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፥ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ።
45 ደግሞ መንግሥተ ሰማያት መልካምን ዕንቁ የሚሻ ነጋዴን ትመስላለች፤
46 ዋጋዋም እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ በአገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ገዛት።››



ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?