Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት

3. እድገቱ

ሉቃ. 2፡ 39-52
39 ሁሉንም እንደ ጌታ ሕግ ከፈጸሙ በኋላ፥ ወደ ገሊላ ወደ ከተማቸው ወደ ናዝሬት ተመለሱ።
40 ሕፃኑም አደገ፥ ጥበብም ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ።
41 ወላጆቹም በያመቱ በፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ነበር።
42የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ፥ እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤
43 ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ፥ ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥ ዮሴፍም እናቱም አላወቁም ነበር።
44 ከመንገደኞች ጋር የነበረ ስለ መሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ሄዱ፥ ከዘመዶቻቸውም ከሚያውቋቸውም ዘንድ ፈለጉት፤
45 ባጡትም ጊዜ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
46 ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም በመቅደስ አገኙት፤
47 የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ።
48 ባዩትም ጊዜ ተገረሙ፥ እናቱም። ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን አለችው።
49 እርሱም፦ ስለ ምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን? አላቸው።
50 እነርሱም የተናገራቸውን ነገር አላስተዋሉም።
51 ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር።
52 ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ስናከብር ነበርን፡፡ በአብዛኛው እንደተደሰታችሁበትና ጥሩ ጊዜ እንደሳለፋቸሁ አስባለሁ፡፡
ብዙውን ጊዜ በዓሉን ለማክበር ስንል በምናደርጋቸው ነገሮች (በምናዘጋጃቸው ዝግጅቶች፣ በምንሠጣቸው ስጦታዎችንና በምቀባላቸው እንዲሁም በምናያቸውና በሠራቸው የማስዋቢያ ስራዎች (ዲኮረቲቭ ዎርክስ) ላይ ብዙ የምንናገር፣ የምናስብ፣ የምንደሰትና፣ ሓሳብ የምንሠጥ፣ በአጠቃላይ ብዙወን ጊዜአችንንና ትኩረታችንን የምንሰጥ እንሆንና ከዋናው ነገር ባዶ እንሆናለን፡፡ ዋናው ብዬ የምናገረው የኢየሱስ ለእኔ ብሎ መምጣትና በሕይወቴ እንዲመጣ የሚፈልገው ለውጥ ነው፡፡
ባለፈው አብረን ለማየት እንደሞከርነው፣ የዘላለም አምላክ በሰው መልክ ወደ ምድራችን የእኛን ልብስ ለብሶ ሊረዳን እንደመጣ ነው፡፡
ስለዚህ እግዚአብሄር የሚደሰትበት እንዴትና በምን ኣይነት ዝግጅትና ድምቀት እንዳከበርነው ሳይሆን፣ እርሱን ማወቃችንና ለአላማው ህይወታችንን በመስጠታችን ነው፡፡ ይህ ደግሞ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ አምነን የዘላለምን ሕይወት እንድናገኝና በእርሱም ጸንተን መኖራችን ነው፡፡
ዛሬ ደግሞ የምንማረው ከልዴት እስከ አገልግሎት ያለውን የኢየሱስ ሕይወት ነው፡፡ ከልደት ቀጥሎ ምን ይመጣል? እድገት፡፡ እድገት በህዴት የሚመጣ ነገር እንጂ በአንድ ቅጽበት የሚመጣ ነገር አይደለም፡፡ እኔ ገና ኦልፍኑን ሲትወለድ፣ እስክትሲመኝ ድረስ፣ ከዚያም ተነስታ እስክትቆም፣ በእግሯ መሄድ እስክትችል…. እጓጓ ነበር፡፡ ዛሬም የሚጓጓባቸው ሌሎች ነገሮች አሉኝ፡፡ ቢሆንም ግን መጠበቅና አስፈላጊውን ግብአቶች ማቅረብ የግድ ይሆናል፡፡ የሚያሳድግ እግዚአብሄር ነው፡፡
እድገት ጊዜንና የተለያዩ ግብዓቶችን የሚፈልግ ህዴት ነው፡፡ በጣም የሚገርመው፣ ሁሉን የሚችል እግዚአብሄር ልጁን ወደ እኛ ሲልክ በአንድ ቀን ተአምር ሰሪ አላደረገውም፣ መጠበቅ ነበረበት፡፡

ምሳሌ፡ አንድ ጊዜ አንድ አባት ልጁን ወደ ኮለጅ ወሰደውና የትምህርት ቤቱን ሃላፊ (የወንጌል ሰባኪም የነበረውን ሰው ነው) እንዲህ አለው ይባላል፡፡ "ልጄ ይህን ሁሉ ኮርሶች ለመውድ አይፈልግምና፣ ቶሎ ብሎ የሚጨርስበትን ሁኔታ ልታመቻችለት አትችልም ወይ?›› ሰባኪውም "ይቻላል! እሬ ቀላል ነው፡፡ ብቻ ልጁ እንዲወጣው የምትፈልገው ነገር ብቻ ይወስነዋል እንጂ፡፡ ትልቅ የዝግባን ዛፍ ለማድረግ ሲፈልግ እንግዚአብሄር አንድ መቶ አመታትን ይወስዳል፣ ቶሎ በቅሎ የሚጠፋ ተክልን ደግሞ ለማድረግ ሁለት ወራት ይበቃዋል›› በማለት አቋራጭ መንገድ ብዙም አለመጥቀሙን ነገረው፡፡
- የእግዚአብሄር ልጅ ኢየሱስ በምድር ላይ ተመላልሶ ሥራውን ጀምሮ ለመፈጸም 33 1/2 ዓመታት ወሰደበት፡፡
እንግዲህ ከልደት ቀጥሎ ያለውን የኢየሰሱስ ሕየወት ብናጠና፡-
- ጌና እንደተወለደ
o ተመሰከረለት (Luk 2:8-14) -- በሰዎች (ሃና፣ ሃናኒያስ)ና በመላእክት፣
o ተሰገደለት (Matt. 2:10-11) -- በክዋከብት ተመራማሪዎች፣
o የሞት አዋጅ ወጣበት (Matt. 2:13-16) ፣ በሮማዊው ሀገረ-ገዥ
o የስደተኛነትን ኑሮን (Luk 2:8-14) ጀመረ (በምሪት--ሔሮድስ እስኪሞት)፡፡
 ይህም በመሆኑ፣ ከዚህች አለም አለመሆኑን መገንዘብ ይቻላል፣ አለም የራሷ የሆኑት ን ትቀበላለችና (Jon 7:7; 15: 18-19 " ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ። ከዓለምስ ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን ይወድ ነበር፤ ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ ከዓለም ስለ አይደላችሁ ስለዚህ ዓለም ይጠላችኋል።")፡፡ "2 Tim.3:12 በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።" አለም ስላልተገባቻቸው….
 ጊዜው ሲደርስ ከስዴት ህይወት ተመለሰ (አሁንም በምሪት)
እነዚህ ሁሉ በሌሎች በእርሱ ላይ የሆነ ነው፣ ውጫዊ አካል እንዲሄድበት የተደረገ ነው፡፡
የእርሱን የግል ህይወትን በተመለከተ ደግሞ
- በሰውና በእግዚአብሄር ፍት ያድግ ነበር--- የተመጣጠነና ሁለንተናዊ እድገት ያሳይ ነበር፡፡ በማዳመጥ፣ አግባብነት ያለውንም ጥያቄ በመጠየቅ፣ በመታዘዝ ፣ ከሌሎች/ከቤተሰቦቹና ከደንበኞቻቸው ጋር ተባብሮ በመስራት(Mrk 6:1-4) ያድግ ነበር፡፡ ይህ ለሁላችን በተለይ ደግሞ ለልጆችና ለወጣቶች በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ወላጆችም ልጆቻቸው የተመጣጠነ እድገት እንዲያድጉ ለማድረግ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸውም ጭምር ያስተምረናል፡፡
o ሰውም እግዚአብሄርም ያስፈልጉናል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት
- አንድ አይውዳዊ ልጅ ማለፍ ባለበት ሁሉ አለፈ (ሉቃ 2፡39)፡፡
o ከግሪዛቱ በፍት ስም ወጣለት-- ቀድሞውኑ በተነገረለት ስም ፈፊቺለሌ ተጠራ
o በስምንት ቀኑ፣ የእግዚአብሄር የመሆኑን ምልከት--ግዝረት በሥጋው ላይ ተቀበለ
 (ሉቃ 2፡21 ልክ ዛሬ በአንዳነድ አብያተ-ክርስቲያናት ሕጻናት እንደሚጠመቁት ዓይነት)
o 12 ዓሜት ሲሆነው ወደ መቅደስ ሄዴ--
 በዚህ እድሜው እንኳን ስለእግዚአብሄር ቃልና አገልግሎት ይጠይቅ፣ ቻሌንጅ ያደርግም ነበር፡፡
- ይታዘዝ ያገለግልም ነበር-- ለማሪያምና ለዮሴፍ
- የእግዚአብሄርን ጊዜ ይጠባበቅ ነበር (በውንድሞቹ ሲዘበትበትም፣ በእናቱ ሲነዘነዝ)
- ለአገልግሎት ራሱን ያዘጋጅ ነበር-- በጸሎት፣በጥምቀት/ጽድቅን መፈጸም፣
o እድገቱ አቁአራጭ ሳይሆን ጊዜውንና ህዴቱን የጠበቀ ነበር፡፡
o ቁጭ ብሎ ተአምር ብቻ በሕየወቱ እንዲሆን አልጠበቀም፣ ማጥናት ያለበትን አጠና፣ መስራት ያለበትን ሠራ፣ መጠየቅ ያለበትን ጠየቄ፣ መናገር ያለበትን ተናገረ፡
o ሉቃ 2፡46-47 ሲሰማ፣ ሲጠይቅ፣ የተጠየቀውንም ሲመልስ እንደነበር ተመስክሮለታል፡፡ ያንን ሁሉ ሲያደርግ ደግሞ በፍቅርና በመልካም መንፈስ እንደነበር መረዳት እንችላለን፡፡
 ዛሬ ብዙ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ለመስማት ግዜ የለውም፡፡ በቤተ/ያን ሆኖ እንኳን ሓሳቡ ሌላ ጋ ነው ያለው፡፡
 ለሚሰማው ነገር ደግሞ ትኩረት ስለማይሠጥ ልክ መሆኑንና አለመሆኑን፣ የራሱ ድርሻ ምን እንደሆነ፣ ከእግዚአብሄር ምን መጠበቅ እንዳለበትና እግዚአብሄር ደግሞ ከእርሱ ምን እንደሚጠብቅ አያውቅም፡፡
 አብዛኛው ሰው በግሉ ከቃሉና ከእግዚአብሄር ጋር ጊዜ ስለሌለው ለሚጠየቀው ጥያቄ አግባቢነት ያለውን መልስ መመለስ አይችልም፡፡
• ምሳሌ፡-አንድ ጊዜ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለው አንድት መምህርታችን መሬት ባራሷ ዛቢያ ላይ ትዞራለች›› ብላ አስተማረችን፡፡ እኔና ሃሳቡ ያልገባቸው ጓደኞቼ፣ "ታዲያ መሬት የሚትዞር ከሆኔ፣ እኛን እንዴት አናየውም ›› በማለት ጠየቅን፡፡ በወቅቱ ያንን ጥያቄ መመለስ ስላልቻለች፣ ለተንኮል እንደጠየቅን በመውሰድ በጣም ተቆጣችን፡፡ የትምህርቱ ሓሳብ ለእኔም በሓላ ገባኝ፡፡
• የእግዚአብሄር ቃል" ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።1Pet 3:15-16 ይለናል፡፡
• ኢየሱስ ልጅም ሆኖ እያሌ የተጠየቀውን ይመልስ ነበር፡፡
 ሌላው ደግሞ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ህብረት ጥሩ ካልሆነ፣ ከእርሱ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ አይተጋም፣ በዚየው ልክ ደግሞ ፍቅሩ እየቀዘቀዘ ይሄዳል፡፡ ኢየሱስ " በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንደሚገባኝ አላውቃችሁምን?›› አለ፡፡ ይህም ማለት፣ በቤቱ ጊዜን ማሳለፉ ደስታ ይሠጠዋል ማለት ነው፡፡ እኛን ወደ ቤተ/ያን መሄድ፣ ወደ ጸሎት ቦታ መሄድ፣ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት ያለበት ቦታ መሁድ፣ ሰውች ተሰብስበው ስለእግዚአብሄር ነገር በሚነጋገሩበት ቦታ መገኘት ደስታ ይሰጠን ይሆንን?
 ዳዊት፣ አቤቱ፥ የቤትህን ስፍራ የክብርህንም ማደሪያ ቦታ ወደድሁ። Psa.26:8" ወደ እግዚአብሄር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ›› ይላል፡፡ " ሌላ ቦታ ሽህ አመት ከመኖር፣ በእግዚአብሄር ደጅ መጣል ይሻለኛል›› 84:10 "…እንድት ነገር ብቻ ለመንሁ፣ እርሷንም እሻለሁ፣ በእግኢብሄር ቤት ለዘላለም እኖር ዘንድ 27:4-6
 84:1-2,10 " የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ ማደሪያዎችህ እንደምን የተወደዱ ናቸው! ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትወድዳለች ትናፍቅማለች ልቤም ሥጋዬም በሕያው አምላክ ደስ ተሰኘ። 10 ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ" ››
ስለዚህ ዛሬ ከኢየሱስ የልጅነት ጊዜ የምንማረው፣ " አግባብነት ያለው ጤናማ እንዲገት ማደግ እንዳለብን ነው፡፡›› ይህ ደግሞ በሰውም በእግዚአብሄርም ፊት መሆን አለበት፡፡

ሓዋሪያወ ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ሲመክር፣ "
10 ይህን (እግዚአብሄርን መምሰልን--ለሁሉም የሚጠቅመውን ቁ.8) ለማግኘት እንደክማለንና፥ ስለዚህም እንሰደባለን፤ ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው።
11-12 ይህን እዘዝና አስተምር። በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው።
13 እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር ለማስተማርም ተጠንቀቅ።
14 በትንቢት ከሽማግሌዎች እጅ መጫን ጋር የተሰጠህን፥ በአንተ ያለውን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።
15 ማደግህ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ ይህን አስብ፥ ይህንም አዘውትር። ››
የዕብራዊያን ፀሃፊ ደግሞ 5
11 ስለ እርሱም የምንናገረው ብዙ ነገር አለን፥ ጆሮቻችሁም ስለ ፈዘዙ በቃል ልንተረጕመው ጭንቅ ነው።
12 ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።
13 ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅምና፤
14 ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉውን ለመለየት በስራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው ለፍጹማን ሰዎች ነው።
"…አስተማሪዎች መሆን ሲገባችሁ…›› በማለት ይተቻቸዋል፡፡ አስተማሪ ሲል ለሌሎች ጥሩ ምሳሌ መሆን፣ መንገድን ማሳየት የሚችል ማለት ነው እንጂ ክላስ/ፑልፔት ይዞ ቆሞ የሚያስተምር ማለት ብቻ እንዳልሆነ እንድንረዳው እፈልጋለው፡፡
Col 2:2-3
እግዚአብሄር ሁላችንንም ይርዳን!
በመጨረሻም " እኔ በክርስትና ህይወቴ ማደግ እንዳለብኝ ዛሬ ገብቶኛልና ቆም ብዬ ራሴን ማየት እፈልጋለው፣ ምርጫዎቼንም አስተካክላለው›› የሚል ሰው ካሌ ደግሞ ተነስቶ ከእኔ ጋር እንጸልይ፡፡
መዝሙር፡፡
በፍቅር አሳድገኝ ጌታ ሆይ በፍቅር በከንቱ መታበያችን ይቅር በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር፡፡

4. ኢየሱስ የአገልግሎት ሕይወት
ባለፉት አብረን ጊዜያት (ከእኔ ጋር የእግዚአብሄርን ቃል ስናጠና፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወትና አገልግሎት ጀምረን ነበርን፡፡ የዛሬው የጥናቱ 3ኛ ክፍለ-ጊዜ ነው፡፡
በመጀመሪያዉ ክፍለ-ጊዜ
1. ስለ በመጀመሪያ ስለነበረው የኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ለመዳሰስ ሞክረናል፡፡ ከዚያም
2. ስለ ኢየሱስ ልዴት አይተናል፡፡
በሁለተኛው ክፍለ-ጊዜ
3. ስለ ኢየሱስ እድገት አየን
ኢየሱስ እንዴት አድርጎ በሰውና በእግዚአብሄር ፊት ሲያድግ እንደነበር አይተናል፡፡ እንደ ማንኛውም አይውዳዊ ልጅ የሚፈለግበትን ሃላፍነት እየተወጣ (ለወላጁ እናትና ለሕጋዊ አባቱ እየታዘዘ፣ ዮሴፍ ይሰራ የበረውን የአናጥነት ስራ እየሰራ፣ የእግዚአብሄርን ህግ/ቃል እየተማሬ፣ በሰማያዊው አባቱ ቤት መገኘትን እንደግዴታ (ተገብነት እንዳለው ነገር፣ ቅድምያ ሊሰጠው እንደሚገባው ነገር) እየቆጠረ እንዳደገ አይተን ነበር፡፡
ዛሬ ሶስተኛው ክፍለ-ጊዜ ነው--
4. ስለ ኢየሱስ የአገልግሎት ሕይወት እናያለን ----ወደ ዋና የወንጌል አገልግሎቱ እንዴት እንደመጣና አንዴት ያደርገው እንደነበር እናያለን፡፡
- የጥምቀት ጊዜ፡
o ኢየሱስ ምንም እንኳ ፍጹም ሰው ቢሆንም፣ ሓጢአትን ባለማድረጉ ግን ከሌሎች ሰዎች የተለየ ነበር፡፡ ዕብ.4:15-16
 "እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ። ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም። እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።"
o ስለዚህ ሲጠመቅ፣ "ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ዮሐንስ ግን። እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር። ኢየሱስም መልሶ፦ አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት። ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ። " Matt3:13-17
ሌሎች ሰዎች ሓጢአታቸውን እየተናዘዙ ሲጠመቁ፣ እርሱ ግን "ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባኛል›› ቢሎ ነበር የተጠመቀው፡፡ ያም ማለት ጽድቅ ፍጹም የሚሆንበትን ስራ ሁሉ መስራት ይገባናል ማለቱ ነው፡፡
o ራሱንም ዝቅ በማድረግ ነበር በዮሃንስ እጅ የተጠመቀው ትህትናን ሊያስተምረን ነው፡፡
o እግዚአብሄር አብና መንፈስ ቅዱስ በአንድ ላይ መገኘታቸውን በማሳየት መሰከሩለት፡፡
 እንደምታወቀው አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በመለኮት አንድ ሲሆኑ በአካል ግን ሦስት ናቸው፡፡
 ሲለዚህ ልክ ወዳጆች በበዓሎቻችን ላይ ተገኝተው ከእኛ ጋር ለመደሰት እንደሚወዱ ሁሉ፣ በኢየሱስ ጥምቀት ላይ እግዚአብሄር በመለኮትና በአካል በመገኘት ደስታውን ገለጠ፡፡ የደስታው መሠረት ግን ኢየሱስ ነበር " በእርሱ ደስ የሚለኝ የሚወደውም ልጄ ይህ ነው›› ቢሎ መሰከረለት፡፡
o እግዚአብሄር ወደ ምድራችን ሲመለከት ከሓጢአት የተነሳ የሚያስደስተው ነገር አልነበረውም፡፡ እግዚአብሄር ሓጢያትን ይጸየፋል፣ ለሓጢአተኛ ግን ይራራል፡፡ ሲለዚህ ኢየሱስ ደግሞ ራሱ ያለ ሓጢአት ሆኖና ለሓጢአተኞች መዳን ራሱን በማዋረድ ሲመጣ ይህ የአብና የመንፈስ ቅዱስ ትልቅ ደስታም ነበር፡፡
 "ወዲያውም ከውኃው በወጣ ጊዜ ሰማያት ሲቀደዱ መንፈስም እንደ ርግብ ሲወርድበት አየና። የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ። ወዲያውም መንፈስ ወደ ምድረ በዳ አወጣው።" Mark 1:10-12; Matt.17:5
o ዛሬም ቢሆን ከኢየሱስ የተነሳ ብቻ የእግዚአብሄርን ደስታ እናገኛለን፡፡
- የፈተናው ጊዜ፡
o እግዚአብሄር ያለ ሓጢአት በኖረው ወጣት ተደስቶ ሲናገር ሠይጣን ደግሞ ለክርክር መቅረቡ አልቀረም፡፡ እንዲህ ባይጻፍም ምናልባት፣ " ይንን ነገር ቢታይበት አይሻል ወይ በእርግጥ በቂ ፈተና አጋጥሞት ማሸነፉን በምን አወቅህ ›› በማለት፡፡ ልክ ስለ ኢዮብ እንደተከራከረው፡፡
 ስለዚህ እግዚአብሄር አብ አንዲፈተን ፈቀደለት፣ መንፈስ ቅዱስም ወደ ፈተናው ቦታ (ወደ ምድረ በዳ) ወሰደው፡፡
 ከዚያም ሠይጣን እስኪደክው ጊዜ ጠበቀው፡፡ በደከመው ግዜ፣ እጅግም በተራቤ ጊዜ፣ የምድረበዳ ኑሮ ባሰለቸው ጊዜ በሰማይና በአለማችን በመጣላቸው በታወቁ ከባባድ የፈተና አይነቶችን ይዞ ወደ ኢየሱስ ቀረበ፡፡ በፈተና ሕይወት ውስጥ የመጨረሻዋ ሰዓት ከባድና አደገኛ ናት፡፡ ይህችን የመጨረሻ ሰዓት ጠላት በሚገባ መጠቀም ይፈልጋል፡፡
o ኢየሱስ የተፈተነበት ፈተና
 በምድራችን ላይ የሚታዩትን ብዙ ዓይነት ችግሮችና ወንጀሎችን ስፖንሰር ያደረገ --- ከረሃብ ማምለጥ፣ የመጥገብ ፍለጋ፣ የፈለጉትን የማግኘት ጥማትን፣ ዛሬ እኔና እናንተ የወደቅንበትና ደግሞም ልንውድቅበት የምንችል ነገርን ለኢየሱስ አቀረበ፡፡
 ሠይጣንን ራሱ ከሰማይ የጣለው ዓይነት--- የታላቅነትና የክብር ፍለጋ
• ብዙ ታላላቅ የተባሉትንም እንዲወድቁ እንዲዋረዱ ያደረጋቸው ነው (ምሳ. ነቡከድናጾርን፤ ሄሮድስን)
 አዳምንና ሄዋንን ከገነት ያስወጣ አይነት ፈተና ----የታላቅነትና የክብር ፍለ
 ብዙ ቅዱሳንን ለጉዳት ያደረጋቸው ዓይነት ፈታና አቀረበለት፡፡ --- ራስህን ወርውር
 ኢየሱስ ግን ለቀረበለት ፈተና ሁሉ አልወደቀም፣ ግን የእግዚአብሄር ቃል (የእግዚአብሄር ፈቃድ) ለእያንዳነዳቸው ምን እንደሚናገር በመጥቀስ አሸነፈው፡፡
• "ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው (ለሰዱቃውያን)፦ መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ስለዚህ የምትስቱ አይደለምን?" mark 12:24
- በጸሎት/በጾም--ከአባቱ ጋር በመነጋገር ያገለግል ነበር
o ለአርባ ቀን ተለይቶ --- ከመረበሽ ሁኔታ ራሱን አስወጥቶ---- እኛ እንዳለንበት ጊዜ ቢሆን ምናልባት ቤቱን ዘግቶ፣ ሲልኩን ዘግቶ፣ ቲቪውንና እንተርነቱን ሙዚቃውንና መዝናኛውን ሁሉ ዘግቶ ማለት ነው፡፡
o ኢያገለገለም ቢሆን ሌሊት ሌሊት ከደቀመዛሙርቱ ተለይቶ ይጸልይ ነበር፡፡ ከአባቱ ጋር ይነጋገር ነበር፡፡
 እኔና አናንተ ብዙውን ጊዜ በሓጢአት የምንመላለሰው/የምንሸነፈው ይህንን የህበረት ህይወታችንን ሲላላሳደግነው ነው፡፡
 ከእግዚአብሄር ጋር በአግባቡ ዘወትር መነጋገርን የተለማመደ ሰው ለሚመጣበት ማንኛውም አይነት ጥያቄና ውሳኔ መልስ ከመስጠቱ በፍት ያማክራል፡፡ ከእግዚአብሄርም ይሰማል፡፡ ስለዚህ የሚመልሰው መልስና የሚወስደው ውሳኔ ወጥመድ አይሆንበትም፡፡
 ከእግዚብሄር ሰምተን በምንወስደው እርምጃ ውስጥ ለሚደርስብን ነገር ሁሉ እግዚአብሄር ይሳተፍበታል፡፡
o መጽሓፍ ቅዱስ ሳታቋርጡ ጸልዩ ቢሎ ሲነግረን የሃይማኖተኝነት ሥራን ለማድረግ ራሳችሁን የህግ ባሮች አድርጉ ማለቱ ሳይሆን፣ ከእግዚአብሄር ጋር የማያቋ ርጥ ህብረት አድርጉ፣ ያለማቋረጥም ከእርሱ ጋር ተመካከሩ ማለቱ ነው፡፡
o ጸሎት እንዴ ስራ ሲሆን በጣም ያደክማል፣ የህይወታችን አካል ከሆነልን ቀላል ነው፡፡ ልክ እንመተንፈስና መብላት ማለት ነው፡፡
 ምሳሌ፡ እስቲ አንድ አማካሪ ወዳጅ አንዳለችሁ አስቡና፣ በአንድ ሁኔታ ውስጥ እንዲታልፉ ይመክራችሃል፡፡ ያንን ህዴት ሲትሄዱ፣ የሚሞሉ ፎሞች ካሉ ምን ማለት እንዳለብን፣ አማራጭ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን የትኛው እንደሚሻል፣ ወዘተ. እየደወልን እንጠይቃለን፡፡ በህዴቱ ውስጥ የሚደረጉ ነገሮችን እንዴሲራ ብንወስዳችውም አንከከኳ ደውለን የምናናገርበትን ጊዜ አንደ አንድ አድካሚ ሲራ አንቆጥረውም፡፡ መደወሉ ግን አንዴ ወሳኝ ነገር አናየዋን፡፡
 እኛ ክርስቲያኖች የዘላለም ሕይወት ጉዞን ጀምረናል፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ የማምለጥ ሩጫዎችንም እንሮጣለን፣ ከክፉው መንግስት አገዛዝና አስራር፡፡ በዚህ ህዴት ውስጥ ብዙ አማራጮች፣ ብዙ አድካሚ ሁኔታዎች፣ ብዙ ዉሳኔዎች፣ ብዙ ጥያቄዎች ያጋጥሙናል፡፡ በአብዛኛው ከመንገዱ ሊያስወጡን፡፡ እንዲህ ባለው ሁኔታ ከእግዚአብሄር ጋር በመነጋገርና ከእርሱ ጋር ያለንን ህብረት በማጠናከር አናሸንፋለን፡፡
o እንግዲህ ኢየሱስ የጸሎት ሕይወቱ ከባድና አድካሚ ቢመስሉም ለእሱ ግን ወሳኝና ወዶት የሚያደርገው ነበር፡፡ በጸሎቱም ሓይል በሌሎች አገልግሎቱ ስከት ነበረው፡፡
 ከአብ ጋር ተስማምቶ ከመናገሩና ከመስራቱ የተነሳ፣ "እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።" John 5:30፤ በተጨማሪም 8፡29 እያለም ይናገረል፡፡ የሚያደርጋችውንም ነገሮች ደግሞ ከአባቱ ፈቃድ ጋር የተያያዙ ናቸው፣ ስለዚህም በድፍረትና በስልጣን ያደርጋቸው ነበር፡፡
• እኛ በየቀኑ በምናልፍባቸው ነገሮችና ሁኔታዎች የምንፈራውና የምንጨነቀው፣ የጌታነ ፈቃድ ለይተን ማወቅ ባለመቻላችን ነው፣ ይህ ደግሞ ከእርሱ ጋር (በጸሎትና በቃሉ ኣማካይነት) ጊዜ ስለማናጠፋ ነው፡፡ ስለዚህ ነገሮች በአጋጣሚ እንዲከናወኑል፣ ነገሮችንም በአጋጣሚ የምናልፍ ባቸው አድርገን ስለምናስብ የትኛው መሆን እንዳለበት አናውቅም፡፡ ይህ ደግሞ ያስጨንቃል፡፡ በድፍረትና በሥልጣን መቅረብ ያቅተናል፡፡
 ኢየሱስ ግን የሚያደርጋቸውን ሁሉ ከአባቱ ፈቃድ ጋር የተያያዙ ከመሆናቸው የተነሳ በድፍረትና በስልጣን ያደርጋቸው ነበር፡፡

 




ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?