Sagalicha Dhiigicha Hafuuricha

ቃሉ ደሙ መንፈሱ

Header Image  

The Word the Blood the Spirit

    

 
 
 

 

ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት መማር


የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት
አሁን የገናን በዓል ልናከብር እየተዘጋጀንበት ባለን ሰዓት በብዛት የሚታሰባትና የሚታቀዱት እንዲሁም የሚተገበሩት፣ በዓሉን ስናከብር ስለምንጠቀምባቸው ነገሮች፣ ስለምንሠጣቸው ስጦታዎች፣ ቤታችንን እንደት አድርገን እንደምናሰውብ፣ ወዘተ. ነው፡፡
ድሮድሮ (በሃገር ቤት፣ ትልቁ የገና ዝግጅት በቤተክርስቲያን ምን ዓይነት ዝግጅት ተደርጎ ሰዎችን መሳብ ይችላል፣ ምን ኣይነት ድራማ፣ ግጥም፣ መዝሙር፣ እና የምግብ አገልግሎት ይሰጣል? ነበር፡፡ አሁንም እግዚአብሄር በፍቱ መልካም የሚሆነውን ነገር ለማድረግ ይረዳን፡፡
ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና አገልግሎት ስንመለከት ከመጀመሪያ መጀመሪ አስፈላጊ መስሎ ታይቶኛል፡፡ እስቲ


1. በመጀመሪያ
መጽሃፍ ቅዱስ "በመጀመሪያ›› ብሎ ከዘመናት ቁጥር በፍት ስላለው ጊዜ ይነግረናል፡፡
ዘፍጥ.1፡1 ፤ ዮሃ.1፡1 መመልከት ይቻላል፡፡
ዘፍጥ.1፡1 በመጀመሪያ እግዚአብሄር (ኤሎህም) ሰማይንና ምድርን ፈጠረ፡፡
- በመጀመሪያ-- ምንም ከመኖሩ በፍት፣ አሁን የሚታዩና የሚታወቁ ነገሮች ሁሉ፣ ግዜንና አቆጣጠሩን ጨምሮ ከመሆናችው በፍት ማለት ነው፡፡ ያኔ እግዚአብሄር ብቻ ነበረ፡፡ ለእኛ መገኘትና ለመኖር የሚያስፈልጉን ነገሮች አሉ፡፡ ለእግዚአብሄር መኖር ግን ሌላ ምንም አላስፈለገም ነበር፡፡


ዮሃ.1፡1 በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሄር ዘንድ ነበረ፣ ቃልም እግዚአብሄር ነበረ፡፡ሁሉም በእርሱ ሆነ፣ ከሆነውም ሁሉ ያለ እርሱ የሆነ የለም፡፡
ይህም ማለት የሚታየውና የማይታየው፣ መንፈሳዊውና አካላዊው፣ በየብስ፣በውሃ፣በአየር ያለው፣ አኔና እናንተ፣ ቀንና ሌሊቱ ሁሉ በዚህ ባ ለታሪክ እንደተፈጠሩ ይነግረናል፡፡ ይህ ባለታሪክ በባህርው ምን መሆን አለበት? መለኮት፡፡ እግኢዚአብሄር መሆን አለበት፡፡ ዮሓንስ ስለዚህ ባለታሪክ --ቃል-- ሲናገር ሕይወት በእርሱ ነበረች ይላል፡፡
ስለዚህ ቃሉ ነገሮች ሲጀመሩ የነበረ፤ነገሮች እንዲጀመሩና አንዲሆኑ ዋነኛው ምና ተጫዋች፣ ከእግዚአብሄር ጋር የነበረና ራሱ ደግሞ እግዚአብሄር የሆነ ነው፡፡
በዘፍ.1 26 እግዚአብሄር (ኤሎህም) ሰውን ሲፈጥር፣ በብዙ ቁጥር እንደተናገረ እናነባለን--- ኑ ሰውን መልካችን እንደምሳሌአችም እንፍጠር በማለት፡፡ ከዚያም ፈጠረ ይላል፡፡ ብዙና አንድ አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህም የስላሴን ትምህርት መሠረት በውስጡ ያዘለ ነው፡፡


ስለዚህ በክርስትና እምነት ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ከስላሴ አንዱ አካል ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ዮሃንስም የሚያስረዳው ቃል--ኢየሱስ እንደሆነ ከምዕራፉ መረዳት ይቻላል፡፡
ቆላ.1፡ 13-18 "እርሱ (እግዚአብሄር አብ) ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። እርሱም (ልጁ ኢየሱስ) የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ(በልጁ) ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል። እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው።››
ዮሃ 1፡.10 እርሱ በዐለም ነበረ፣ ዐለምም አላወቀውም ፡፡
እንግዲህ ቃሉ/ኢየሱስ ከዓለም መፈጠር ፊት ነበረ፣ ከዚያም ዓለምንና በእርሷ ያለውን ከፈጠረ በሃላ በዓለም ነበረ፣ ሆኖም ግን ዓለም አላወቀውም፡፡
ይህንን እውነት ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ንግግር ራሱ መረዳት እንችላለን፡፡
ዮሃ.8:52-58 ኢየሱስ ስለ አብርሃም ስሜትና ልምምድ ተናገረ (ያም ማለት አብርሃምን ያውቀውዋል ማለት ነው)-- ቁ56 "አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው።›› ብሎ፡፡ እነርሱ ግን ገና 50ዓሜት ያልሞላው ሰው በመሆኑ፣ ሊያምኑት ባልቻሉ ጊዜ ኢየሱስ፡- ቁ58 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም (በ1900 ዓ.ዓ ገደማ የኖረ) ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ነገሩ ግራ ስለአጋባቸው ሊወግሩት ድንጋይ አነሱ፡፡ ያንንም ያደረጉበት ምክንያት ከአምላክ ጋር ራሱን ስላስተካከለ ነው ምክንያቱም እርሱ ያለው "አለው›› ነው እንጂ " ነበርሁ›› አልነበረም እና፡፡ ዘፀ. 3፡14 "ያለና የሚኖር››
በዮሃ. 17: 5 ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- "አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።›› ይህም የሚያሳየው ሰው ሆኖ ከመወለዱ በፍት ኢየሱስ በአብ ዘንድ እንደነበርና ክቡር እንደሆነ ነው፡፡ አሁን ግን በሥጋ ወራቱ፣ ሰው በመሆኑ ከአብ ያንስ ስለነበር፣ ይህንን ፀሎት ይፀልያል፡፡
ይህ ብቻ ደግሞ አይደለም፣
ዮሃ.3፡13 "ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።›› ይህንንም በማለት ተልኮ ይዞ ከሰማይ የመጣ መሆኑን ተናገረ፡፡


በዮሓ.1 ቁ.14፡ ላይ "ቃልም ስጋ ሆነ፣ ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ በእኛ አደረ፡፡›› ይላል፡፡ ዮሓንስ በመጽሀፉ ውስጥ እንዴት ቃል ስጋ እንደሆነ በዝርዝርና በጥልቀት አላያስረዳውም፡፡ ይልቁንም በዋና ተልኮው ላይ ትኩረትን ሠጠ፡፡ ማቴዎስና ሉቃስ ደግሞ በዚህ እውነት ላይ -- ማለትም እንዴት ቃል ሥጋ እንዴሆነ -- ከዮሃንስ የበለጠ ሰፋ ያለ ምስክርነት ሰጥተዋል፡፡ ይህንን ወደ ልደቱ ስንመጣ እናየዋለን፡፡
ዮሓንስ ስለተልኮው ሲናገር፡
-የዓለምን ሓጢአት ለማስወገድ የመጣ የእግዚአብሄር በግ ሆኖ ነው--- ለመሰዋት--ዮሃ.1፡29
- ሰዎች በእርሱ በኩል የዘላለምን ሕይወት እንዲያገኙ ለመርዳት ነው፡፡


2. ልደቱ
ወደ ልደቱ ስንመጣ፣

ኢሳይያስ 7፡14 "ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።››

ኢሳይያስ .9፡6 "ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።"

ከብዙ ክ/ዘመናት በፊት ከድንግል ከይሁዳ ከተሞች አንዷ በሆነችው በቤተልሄም እንደሚወለድ በትንቢት ተነገረ፡፡ ሚክያስ 5:2-5a
ከመጽሃፍ ቅዱሳችን እንደምንረዳው ቤተ-ልሄም ከሌሎች ከተማ በሚታየው ነገር ያነሰች ብትሆንም እግዚአብሄር ግን ልቡ የሚደሰትበትን የሚያገኝበት ከተማ ሆና ተነግራለች፡፡ ዳዊት የተወለደው እና የተቀባው በዚያ ሲሆን ኢየሱስም የተወለደው በዚያው ነበረ፡፡ ስለሁለቱም አገልግሎት እግዚአብሄር ደስ እንደተሰኘባቸው መስክሮላቸዋል፡፡
ብዙ ጊዜ እኛ ስለትንሽነታችን/በብዙ ነገር ማነሳችን ልናስብና ልንጨነቅ አንችላለን፡፡ እግዚአብሄር ግን በዚህ ሳይሆን ለእርሱ በምናቀርበው ነገር፣ በእውነተኛ አምልኮና አገልግሎታችን፣ ከፈቃዱ ጋር የሚስማማ ነገር ማድረጋችን፣ ለእርሱ ክብር በመኖራችን አንጂ በትንሽነታችን ወይም በግዙፍነታችን አይደነቅም፡፡
የማቴ.1፡
18 የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።
ሉቃ 2
23 የማገልገሉም ወራት ሲፈጸም ወደ ቤቱ ሄደ።
24-25 ከዚህም ወራት በኋላ ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰችና። ነቀፌታዬን ከሰው መካከል ያስወግድልኝ ዘንድ ጌታ በተመለከተበት ወራት እንዲህ አድርጎልኛል ስትል ራስዋን አምስት ወር ሰወረች።
26 በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥
27 ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ።
28 መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።
29 እርስዋም ባየችው ጊዜ ከንግግሩ በጣም ደነገጠችና። ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው? ብላ አሰበች።
30 መልአኩም እንዲህ አላት፦ ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።
31 እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።
32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤
33 በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።
34 ማርያምም መልአኩን። ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው።
35 መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።
36 እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤
37 ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።
38 ማርያምም። እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች። መልአኩም ከእርስዋ ሄደ።
ማቴ 1
19 እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ።
20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።
21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።
22 በነቢይ ከጌታ ዘንድ።
23 እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።
24 ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፤ እጮኛውንም ወሰደ፤
25 የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።
ቅንነት ይፈለጋል፡፡
ጌታችን ወደዚህ አለም እንዲመጣ መንገድ የሆነችው ማሪያም በእግዚአብሄር ዘንድ ጸጋ ያገኘች፣ በእግዚአብሄር የተመረጠች፣እግዚአብሄርን የሚትፈራ፣ ክብረ-ንፅህናዋን የጠበቀች ሴት ልጅ ነበረች፡፡
ስለእርሷ መጽሃፍ ቅዱስ ሲነግረን ብዙ የተማረች፣ ብዙ የታወቀች፣ ከትልቅ በቴሰብ የተወለደች፣ የሃብታም ልጅ የሆነች አድርጎ አይደለም፡፡
ምናልባትም በብዙ ነገር የሚትፈተን፣ ልቧ ብዙ ሓሳብ ያለባት፣ ምናልባትም ስለሠርጓ፣ ምናልባትም ከዮሰፍ ጋር ሊኖራች ስለሚችል የወደፊት የትዳር ሕይወት፣ ምናልባትም ቤተሰቦቿ የሮምን ንጉስ ለመገበር ስለሚቸገሩበት ግብርና ከግብር ጋር በተያያዜ በሕዝቧ ላይ እየደረሰ ስላለው እሮሮ ስታውጠነጥን ሊሆን ይችላል መልአኩ ገብርኤል ወደ እርሷ የሄደው፡፡ አርሱም ከላይ የሆነውን ሠላም አወጀባት፡፡ ሠላምታውም እርሷ የተለማመደችው ዐይነት (በጆሮ ብቻ የሚሰማ)ሠላምታ አልነበረም፡፡ በሕይወቷ ውስጥ ለውጥንና ልዩነትን የሚያመጣ የእግዚአብሄር ሠላም ያዘለ ነበር፡፡
ጌታ ኢየሱስ እኔ የሚሰጣችሁ ሠላም ዓለም እንደሚሠጠው አይደለም፡፡ ብሎአል፡፡
በዚህ ታሪክ ውስጥ በጣም አስተማሪ የሆኑ ነገሮችን ማየት ይቻላል፡፡
ሀ. ከዮሴፍ ብንጀምር፡- እግዚአብሄርን የሚፈራና የፍቅር ሰው ነበረ፡፡
በሚወዱን መሃልና ለሚታመኑልን ሰዎች መካከል የፍቅር ሰው ሆኖ መገኘት ይቀላል፡፡ በማይታመኑትና የካዱን በሚመስሉት መሃል ግን እጅግ ከባድ ነው፡፡ ኢየሱስ በሃለኛው የምድር ላይ ኖሮው ይህንን በተግባር በመስቀል ላይ ሆኖ አሳየን፡፡ ጌታ ሁላችንንም ይርዳን፡፡
ዮሴፍም የፍቅር ልብ ነበረው፡፡ ከእጮኛው ጋር በመተጫጨት ህዴት ውስጥ እያሉ የጋብቻቸውን ጊዜ ይጠባበቁ ነበር፡፡ ካሳየውም ባህሪይ እጮናወን በጣም ይወዳት እንደነበር መረዳት ይቻላል፡፡ ሆኖም ግን እርሷ በድንገት አርግዛ ተገኘች፡፡ የዚህ ኣይነቷ ሴት ደግሞ በድንጋይ ተወግራ እንዲትሞት በነበረው ባህልንና ልምምድ ይፈረድባት ነበር፡፡ ያንን ክስ ለማቅረብ ለመመስረት ደግሞ ባለመፍቱ ራሱ ዮሴፍ ነበረ፡፡
እርሱ ግን ይወዳት ስለነበር፣ ላለማግባት ቢወስንም እንኳ መሞቷን ግን አልፈለገምና በስውር ሊተዋት አሰበ፡፡ በኃላ ላይ የተጻፈው "ፍቅር ይታገዛል፣ ቸርነትንም ያደርጋል›› የሚል ነው፡፡ ይህ ግን በእኛ ጊዜ እንጂ በእርሱ ጊዜ ተጽፎ አይገኝም ነበር፣ ይልቁንም እርሱ ያነበበው ስታመዝር የተገኘች ሴት ተወግራ ትሙት የሚል ነበር፡፡ በዮሴፍ ልብ እግዚአብሄርን መፍራት ስለነበር፣ ያልተጻፋን እንኳ ከፍቅር የተነሳ ያደርግ ነበር፡፡ ጌታ ይርዳን፡፡ በኦቦ ኤርገጤ ሲያስተምሩን (ቆሮንጦስን ሲያስጠኑን)፣ ሁሉ ተፈቅዶአል ሁሉ ግን አይጠቅምም ስለሚለው የጳውሎስ አገላለጽ በስፋት አስረድተውን ነበር፡፡ እንግዲህ በዚያን ጊዜ፣ መግደል ተፈቅዶ ነበር፣ ዮሴፍ ግን እንደማይጠቅመው አውቆ ተወ፡፡
በእርግጥ ዮሴፍና ሌሎችም እንዳሰቡት ደግሞ አልነበረም፣ ማሪያም ባለመታመን ሳይሆን በእግዚአብሄር በመመረጥና ከእርሱ ጸጋን በማግኘት ነበር የጸነሰችው፡፡
ለ. ሁለቱም ዮሴፍና ማሪያም፣ ከእግዚአብሄር የሚሰሙና በማይመስል ሁኔታ ውስጥም ቢሆን የሚታዜዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ መስማትና መታዜዝ ለአንድ የእግዚአብሄር ሰው ትልቅ ስከት ነው፡፡ ምክንያቱም እንዲህ አይነቱ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር መስማማት ይችላል፡፡ ከእርሱ ጋር መስማማት ከቻለ ደግሞ ከእርሱ ጋር መሄድ ይችላል፡፡ አካሄዱ ከእርሱ ጋር የሆነ ሰው ደግሞ ለሞት አይገኝም፡፡ "ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሄር ጋር አደረገ፣ እግዚአብሄርም ስለወሰደው አልተገኘም› ዘፍ.5፡21-24፡፡
እስቲ ፋቃደኞች ከሆናችሁ፣ "አካሄዴን ከእግዚአብሄር ጋር አደርጋለሁ ለሞትም አልገኝም›› እንበል? ይህንን በእውነት የምንፈልግ ከሆነ፣ ለመስማትና ለመታዘዝ ሁሌ እንዘጋጅ፡፡
ማሪያም-- ወንድ ሳታውቂ ትጸንሳለሽ ሲትባል፣ እሺ እንደቃልህ ይሁንልኝ አለች፡፡
ዮሴፍም -- እጮኛህን ማሪያምን ውሰዳት ሲባል፣ አርግዛም እያያት እሺ ብሎ ወሳዳትና ሊያገለግላት ጀመረ፡፡ ልጁንም እስኪትወልድ ድረስ ግን አላወቃትም ነበር፡፡
ሐ. የእግዚአብሄር ጸጋ ለምንፈለግበት አገልግሎት በቂ ያደርገናል፡፡ ማሪያም ለዚህ ታላቅ አገልግሎት፣ ቃል በእርሷ ውስጥ ስጋ ሆኖ አንዲመጣ፣ ከእግዚአብሄር ዘንድ ጸጋን አገኘች፡፡ ጻጋ ያስችላል፣ ጸጋ ያድናል፣ጸጋው ይበቃናል፡፡ ስለዚህ፣ የፈለገ መልካም ነገር ማድረግ እንኳ ብንችል፣ በጸጋው መታመን አስፈላጊ ነው፡፡
መ. በእግዚአብሄር የተመረጠ ሰውም የሚያልፍበት የተግዳሮት ህይወት ይኖራል፡፡ ዓለም የራሷ የሆኑትን ለመቀበል ዝግጁ ናት፡፡ የጌታን መንገድ የሚከተሉ ሰዎች ግን ለጊዜው ሊቸገሩ ይችላሉ፡፡ በቤተሊሄም ማሪያምንና ዮሴፍን ከማሪያምም ሊወለድ የደረሰውን ሕጻኑን ኢየሱስን ተቀብሎ ለማስተናገድ፣ ወደ ቤቱ ሊቀበለው የሚችል፣ አልጋ ሊያነጥፍለት የበቃ ሰው/ቤተሰብ አለነበረም፡፡ ሁሉም አላወቁትም፡፡ ያ ግን ኢየሱስን በመንደራቸው ውስጥ ከመወለድ አልከለከለውም፡፡ እግዚአብሄር ያለው ይሆናልና፡ አንዳነድ ጊዜ ሁኔታዎ ሳይመቻቹ ሲቀሩ፣ ሰዎች ሳይቀበሉን ሲቀሩ፣ በተቻለ መጠን ትተን ለመሄድ/አቮይድ ለማድረግ/ እንሞክራለን፡፡ ኢየሱስ ግን ቃሉ መፈጸም ሲላለበት፣ በበረት ተወልዶም ለዚያች አላቃቂዋ መንደር በመላእክት ደስታ እንዲነገር አደረገ፡፡
ይህ ብቻ ሳይሆን የሮማው ገዢ ደግሞ ኢየሱስ ተወልዶም እንዲያድግ ስላልፈለገ፣ እርሱን ለማግኘት ስባል ከሁለት ዓመት በታች ያሉትን ሕጻናት በሙሉ አስጨረሰ፡፡ ኢየሱስ ግን ከማሪያምና ከዮሴፍ ጋር ስደተኛ ሆኖ ወደ ግብጽ ወረደ፡፡
የስደትን ኖሮ በልጅነቱ ያለፈበት ኢየሱስ ለስደተኞች ይራራል፡፡




ተክሉ ተ. ጉታ

ቃሉ ደሙ መንፈሱ የወንጌል አገልግሎት

 

E-mail: [email protected]

 

 
 

Waaqayyo si jaallata
Waaqayyo si jaallata

Ati Eessa?
Ati Eessa?